አቶ ተገኘሁ ተሻገር ዜብራ ክሮስ ላይ ሰው ገጭቶ ገደለ

Standard

በሃይለኛ የስካር መንፈስ ውስጥ ሆኖ ሲያሸከረክር የነበረው የአማራ ክልል አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አቶ አገኘሁ ተሻገር በእግረኞች ማቋረጫ መንገድ ወይም “ዜብራ ክሮስ” ላይ ጋሻው የተባለውን ወጣት ገጭቶ ከገደለው በሁዋላ፣ በእለቱ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ቢወሰድም በማግስቱ የተለቀቀ ሲሆን፣ ኢሳት ዜናውን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ግን ተመልሶ እንዲታሰር መደረጉን ምንጮች ገልጸዋል። ድርጊቱ የከተማው ህዝብ መነጋገሪያ ርእስ መሆኑን የተረዱት ፖሊሶች ባለስልጣኑ ለጊዜው በእስር ቤት እንዲቆይ አድርገውታል። ፖሊሶች ሃዘን ቤት ድረስ በመሄድ አደጋው በተፈጸመበት እለት ከነበሩ ወጣቶች መካከል አንዱን ቃሉን እንዲሰጥ የነገሩት ሲሆን፣ የቃል አሰጣጡ ሂደት ፈታኝ እንደሚሆንበትም አስጠንቅቀውታል። የአይን እማኞች እንደሚሉት ትሪፊክ ፖሊሶች ሆን ብለው አደጋው ከደረሰበት ከእግረኛ ማቋረጫው መንገድ 50 ሜትር ባለ ርቀት ላይ ሲለኩ መታየታቸውን ባለስልጣኑ በወንጀል እንዳይከሰስ ለማድርግ ነው። አንድ አሽከርካሪ ሰው ገጭቶ ቢገድል ከ15 እስከ 25 ዓመታት እንደሚታሰር ህግ ወጥቶ እያለ፣ በሚሊዮን የሚቆጠር ብር የሚፈጅ መኪና በስካር መንፈስ እያሽከረከሩ ሰዎችን የሚገድሉ ባለስልጣናትን ምሽት ላይ አስሮ ጠዋት ላይ መልቀቅ በአገሪቱ ያለውን የፍትህ ስርዓት መበላሸት ያሳያል ይላሉ። ነዋሪዎቹ የፖሊሶች ሁኔታ ባለስልጣኑ ቶሎ ይለቀቃል ብለው እንዲያምኑ እንዳደረጋቸው ይገልጻሉ።

Advertisements

​ኢትዮጵያዊው ከጠላህ በቁምህ ትሞታለህ

Standard

በቅርቡ ቀን የቴዲ አፍሮ ዘፈን በሙዚቃ ባለቤቶች ሳይሆን በመርካ ነጋዴዎች 15ሚሊዮን ብር እንደተገዛ ሰማን ብዙዎቹም ያንስበታል እንጂ አይበዛበትም ሲሉ ተደምጠዋል ሰው ሲወድህ እንዲህ ነውና ። ታዲያ ከዚህ ዜና ጋር ተያይዞ ሌላው ብቅ ያለው አስገራሚው ዜና ንዋይ ደበበ የሙዚቃ አልበሜን አዘጋጅቼ ስፖንሰር ባለማግኘት ገበያ ላይ ላወጣው አልቻልኩም ይለናል ። ታዲያ የኛም መልስ የት ሄዱ ወያኔዎችህ ለክፉ ቀንህ እንኳን መድረስ አቃታቸው ወይ። አየህ አሁን ትግሬ አለመሆንህን እርገመው ትግሬ ብትሆንማ ኖሮ አይደለም ስፖንሰር ልታጣ ይቅርና ሙዚቃህ በማርሽ ሁሉ ይታጀብ ነበር እንደነ ኤደን ገብረስላሴ አልበምህን የሚገዛህ እንኳን ባይኖርህም ነገር ግን አንተ እነሱን አይደለህምና ስፖንሰር እንኳን አጣህ እናም ወዳጄ ንዋይ ይህ ያንተ የምጥህ መጀመሪያ ነው ። አንቅረህ የተፋኸው ህዝብህ አንቅሮ ተፍቶሃል ወዳጆችህ ወያኔዎችም እንደ ሸንኳራ አገዳ አላምጠው ተፍተውሃል ገና ወደፊት ቡና የሚያጣጣህም ታጣለህ ።እናም እንደ ወንድም ሆኜም ስመክርህም ብትችል መቐሌ ግባና ትግሪኛ ተለማመድና ቢያንስ ቢያንስ የዛኔ የዚህ ስርዓት መጨረሻው እስኪደርስ ድረስ እንኳን እየጠሉህም ቢሆን ብና ያጣጡሃል አልያም ደግሞ ያው ከዚህ በፊት ገንዘብ የደጎመህ ያ የምትላላከው ማን ሙዲን ነው የሚሉት ካሴቱን ለግሉ ሽጥለትና እዛው አዝምርለት እልሃለሁ እውነቴን ነው የምልህ ምክሬን ሳትንቃት ተጠቀምባት እልሃለሁ ።ከዚህ ምስኪን ህዝብ ጋር የተጣላ መጨረሻው ይህው ነው ።

ተከታይ ተረኛ የወያኔ አዝማሪዎችም ተዘጋጁ ።

​በወያኔ ላይ አዲስና የተቀነባበረ ጥቃት እየተፈፀመ ነው ተባለ

Standard

በአማርውና በሆሮሞ ህዝቦች ተጀምሮ የነበረው የፍትህና የዲሞክራሲ ጥያቄ መልኩን ቀይሮ የህወሀት አገዛዝ እንዲያበቃ በከፋኝ ሀይሎችና በአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ከፍተኛ ተጋድሎ የተደረገ እንዳለ ይታወቃል ። ሁለገብ የሆነ ትግል እያራመዱ ያሉት የነፃነት ሀይሎች በተጨማሪ ለየት ባለ መልኩ በህወሀት ወያኔ ንብረት በሆኑት ድርጅቶች ላይ ጥቃት ያደረሱ ነው ተብላል።በዚህም በዛሬው ለት ብቻ የህወሀት ንብረት በሆኑት በአዲስ አበባ ልዩ ስሙ ጃክሮስ በሚባል አካባቢ በሚገኘው እጅግ ግዙፍ በሆነው የወያኔ ኤፈርት ሁሉን አቀፍ አስመጪና ላኪ መጋዘን እና ፋብሪካ ክፍል በተቀነባበረ ሴራ በተለኮሰ እሳት በትንሹ እስከ 40 ሚሊዎን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙ ሲነገር በሰሜን ጎንደር ሁመራ ንብረትነቱ የህወሀት የነበረ የተከማቸ 440 ኩንታል ጥጥ መቃጠሉም ተነግራል  ::በተመሳሳይ ቀን በዚህ ሰሃት በባህርዳር አመልድ የሚባል የብሀዴን ንብረት የሆነ ድርጅት በመቃጠል ላይ መሆኑን በዚህም ምክኛት ባካባቢው ከፍተኛ ቶክስና ግርግር መኖሩ ተሰምታል።ይህም ጥቃት የነፃነት ሀይሎች በወያኔ ላይ የወሰዱት ያለ አዲስ ጥቃት ነው ተብሎ የነገራል።

በአሰግድ ታመነ

​የወጣት ማስተዋል እና የአምባሳደር ሀለቃ ፀጋይ ሙግት

Standard

ማስተዋል ጥላሁን በእስራኤል ነው የሚኖረው። ሰሞኑን ሀብታሙ አያሌው በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የአማርኛው ክፍለ ጊዜ ላይ ቀርቦ በእስር ቤት ውስጥ በእሱና በሌሎች ታሳሪዎች ላይ ስለሚፈጸመው ግፍ ሲናገር ውስጡ በከፍተኛ ቁጣና ንዴት የተሞላው ማስተዋል፤ ቀጥታ ቴላቪቭ ወደሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በመሄድ በጽህፈት ቤቱ በር ላይ ተሰቅሎ የነበረውን ባለኮከቡን ባንዲራ አውርዶ በማቃጠል ነው ከቁጣው ለመብረድ የሞከረው። ይህን የተመለከቱት ቀደም ሲል የትግራይ ክልል ርዕሰ ብሔር፣ ከዚያም የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የጸጥታና ደህንነት አማካሪ የነበሩት አዲሱ የእስራኤል አምባሳደር ሀለቃ ፀጋይ በርሃ በእስራኤል ፍርድ ቤት ማስተዋል ላይ ክስ ይመሰርታሉ። “የደህንነት ስጋት አለብኝ”በማለትም ለፍርድ ቤቱ አቤት ይላሉ።ከዚያም ፍርድ ቤቱ ማስተዋልን ለምን ድርጊቱን እንደፈጸመ ሲጠይቀው ምክንያቱን ይናገራል።ግራና ቀኙን ያደመጠው የእስራኤሉ ፍርድ ቤት በመጨረሻም ወጣት ማስተዋልን በነጻ አሰናብቶታል።ሃለቃ ፀጋይም “የደህንነቴንስ ጉዳይ?” በማለት ደጋግመው አቤት በማለታቸውም ማስተዋል ከኤምባሲው እስከ 500 ሜትር ባለው ርቀት እንዳይጠጋ ፍርድ ቤቱ በውሳኔው አካቷል።“ቀጥ ብላችሁ ዐያችሁን” ብለው በጥይት ግንባር ግንባርን ሲቀሉና ሲያስቀሉ፣ እንዲሁም ከላይ ሆነው በሚያሽከረክሯቸው ፍርድ ቤቶች በንጹሀን ላይ እንደፈለጉ በትዕዛዝ ሲያስፈርዱ የቆዩ አምባገነኖች ፤ተዘልፈውም፣ ተዋርደውም ፍትሕ ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንዲህ ሲያዩ እንዴት ደስ ይላል!

ጋዜጠኛ ደረጀ ሀ/ወልድ

ከ440 ኩንታል  በላይ ጥጥ ወልቃይት ላይ በእሳት ወደመ

Standard

በወልቃይት የስኳር ፋብሪካ እሠራለሁ በማለት ገበሬዎችንና ከፊል የዋልድባ ገዳምን ያስለቀቀው የትግራይ መንግሥት ፋብሪካው ዕውን ሊሆን ባለመቻሉ ከፍተኛ የጥጥ ምርት እየተመረተበት እንደሆነ የገለጹት ምንጮች ተለቅሞ ሊጫን የተከዘነ 440 ኩንታል በላይ ጥጥ ሙሉ በሙሉ በእሳት ወድሟል፡፡የእሳት ቃጠሎው የደረሰው መጋቢት 12 ቀን 2009 ዓ.ም እኩለ ቀን ሲሆን እንደሆነ የነገሩን የዐይን ምስክሮች በሌሎች የወልቃይትን ሕዝብ ሀብት እየተቀሙ ባፈሯቸው ንብረቶችም ላይ ተመሳሳይ ጥቃት ሊቀጥል እንደሚችል አስታውቀዋል፡፡ 

ድርቁ

Standard

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሁለት ወራት ውስጥ ባወጣቸው ተከታታይ ሪፖርቶች ምስራቅ አፍሪካ የከፋ ድርቅ መከሰቱንና ዓለም የዕርዳታ እጆቹን ለአገራቱ እንዲዘረጋ በተከታታይ ሪፖርቶቹ ተማጽኗል፡፡ እንደ በዘገባው ከሆነ ድርቁ የከፋባቸው ተጠቃሽ አገራት ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኬንያና ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ ከኢትዮጵያ ውጭ የተጠቀሱት መንግሥታት ለዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ የዕርዳታ እጃቸውን በመዘርጋት፤ በተባበሩት መንግሥታት በኩል የአውሮጳ ህብረትና ሌሎች ለጋሾች በከፋ ድርቅ ላይ ለሚገኙት አገራት ዕርዳታ እየሰጡ ናቸው፡፡ በተባበሩት መንግስታት ሪፖርት መሰረት አገራቱ በእርስበርስ ጦርነት የሚታመሱ እና በውስጥ ችግራቸው የፖለቲካ አለመረጋጋት የሚታይባቸው የመልካም አስተዳደር እጦት፣ ሙስናና ብልሹ አሰራሮች የነገሰባቸው ናቸው፡፡ በመሆኑም ድርቁ ዜጎቻቸውን ለስደት ከመዳረግ አልፎ አገራቱን ለከፋ ማህበራዊ ቀውስና ለውስጥ አለመረጋጋት እየዳረጋቸው እንደሆነ ሪዘገባው ያመለክታል፡፡ “(ረሃቡ) በራስ አቅም የሚፈታ ችግር ነው” ህወሃት ከዜጎች ችግር በላይ ለአገር ገጽታ ግንባታ የሚጨነቀው ህወሃት/ኢህአዴግ ኃላፊነት በሚሰማዉ መልኩ ከዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ጋር በመንቀሳቀስ ድርቅ በተከሰተባቸው የኢትዮጵያ ክልሎች ተገቢ ድጋፍ ከማድረግ ይልቅ ችግሩን “በራስ አቅም የሚፈታ ችግር ነው” በሚል ባሳየው ዳተኝነት ድርቁ ወደ ረሀብ እንዲያድግ ከማድረግ ውጪ ይህ ነው የሚባል መፍትሄ ሲሰጥ አልታየም፡፡ ከህወሃት/ኢህአዴግ ፍላጎት ውጪ ቢሆንም አዲሱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ፤ ኢትዮጵያ የተረጋገጠባትን ድርቅ እንድትቋቋም ዓለአቀፉ ማኅበረሰብ በጋራ እንዲቆም በተደጋጋሚ ጥሪ አቀርበዋል፡፡ ያም ሆኖ ዕርዳታው በሚፈለገው መጠን ሊገኝ አልቻለም፡፡ ለዜጎች ስቃይ ደንታ ቢስ የሆነው የህወሃት አገዛዝ በዓለምአቀፍ መድረኮች የእርዳታ ጥሪ ከማቅረብ ይልቅ፤ የአገሪቱ “አዳኝ መሲህነቱን” መስበኩን ተያይዞታል፡፡ ውጤቱም የዜጎችን ነገ በማጨለም የረሀብ ቤተሰብ የሆነ ተስፋ የለሽ ትውልድ ማፍራት ሆኗል፡፡ “ልማት የረሃብ አደጋን ያጠፋል” (መለስ፣ 1887)፣ “ራሱን የቻለ በራሱ የሚቆም ከልማት ጋር ያልተቆራኝ የረሀብ ማጥፋት ፖሊሲ ያስፈልገናል” (መለስ፣ 1992)፣ “ዕድገታችን የረሀብ አደጋን ቀንሶልናል” (መለስ፣ 2004)፣ “ማንኛውንም ድርቅ ለመቋቋም የሚያስችል አቅም መገንባት ችለናል” (ኃይለማርያም፣2008)፣ … እየተባለ በህወሃት/ኢህአዴግ ሲስተጋባ የኖረው ፕሮፓጋንዳ በእዉን የማይጨበጥና የማይዳሰስ መሆኑን እየታዘብን ነዉ፡፡ በአገሪቱ “አለ” የተባለዉ “ዕድገት”ም በምግብ እህል ራስን ለማስቻልም ሆነ ከዉጭ እርዳታና ድጎማ ለማላቀቅ የቻለ አይደለም፡፡ የመንገድ እና የፎቅ ግንባታውም የድሃውን ጉሮሮ የሚዘጋ የዕለት ጉርስ ወደመሆን ሲቀየርና ህይወቱ ሲያሻሽል አልታየም፡፡ የተለመደው የድርብ አኻዝ “ዕድገት” ግን አሁንም ይደሰኮራል፡፡

​በህዉሃት አፋኝ ቡድን የሞባይል ስልኮች እንዴት እየተጠለፉ ነው?

Standard

መጀመሪያ የምንጠቀምበትን ስልክ ቁጥር ያውቃሉ ከዛም በኢትዩ ቴሌኮም የክትትል ሲስተም ውስጥ incode ይደረጋል። ከዚያም ምን አይነት የስልክ ቀፎ እና የቀፎውን መለያ ቁጥር ( IMEI (International Mobile Equilment Identity number which is a 15 digit Number) ይለያል። በመቀጠል በስልኩ እያንዳንዱን የምትቀባበላቸውን የመረጃ ልውውጦች ( Signaling informations) Centrally በተዘጋጀው ሲስተም ይታያል። በዚህም የጥሁፍ፣ የድምጥ እንዲሁም፣ የInternet Data እንዲሁም ከማን ጋር እንደሚደዋወሉ እና የመሳሰለትን የኢንፎርሜሽን ግኑኝነቶች ሰነድ በቀላሉ ይታያሉ። ከላይ የተገኘው መረጃ ተይዞ በተጨማሪ የ Mobile network System በመጠቀም Target የተደረጉ ሰዋች እንቅስቃሴ ይከታተላሉ። በዚህም የት አካባቢ እንደሚውሉ፣ እንደሚያድሩ እና የመሳሰሉትን መረጃዎች ያውቃሉ። በመጨረሻም ወደ አደን ስራ ይሄዳሉ። Target የተደረገው ሰውየ የሚውልበት እና የሚያድርበት አካባቢ የሚያገለግሉ የሞባይል ጣቢያዋች ለእያንዳንዱ የሞባይል ተጠቃሚ የሚጠቀምበትን የ መመስጠር ሲስተማቸውን Encryption system እንዲጠፋ(Disable) ይደረጋል። ከዚያም በታወቀው የሞባይል ጣቢያ የሚገለገሉ ተጠቃሚዋች በቁጥራቸው አማካኝነት ስልካቸውን በመጥለፍ ተፈላጊው በትክክል የት ቦታ እንዳለ እና እያንዳንዱ የስልክ ቃለ ምልልስ ይሰማል። ስለዚህ ይሄን እንዴት መከላከል ይቻላል??

መፍትሄ

1: ለተልእኳችን የምንጠቀምባቸው የስልክ ቁጥሮች እና ቀፎዋች ከህቡዕ ቡድኑ ውጭ ለማንም ይፋ እንዳይሆን ማድረግ። ሁሉም አባላት ማድረግ አለበት። ለዚህም ስራ ለማህበራዊ ግንኙነት ከምንጠቀመው የተለየ ስ.ቁ ማዘጋጀት አለብን። በተቻለ መጠን ስ.ቁን በኛ ስም ሳይሆን ከኛ ውጭ የምንተማመንበት ሰው ከ ሱቆች ቢገዛልን ይመከራል።

2: የጥሁፍ መልዕክት በተቻለ መጠን የተመሰጠረ( Encrypted/ Coded ) ቢሆን ይመርረጣል። ምክንያቱም ከአባላቱ ውጭ ማንም ሊረዳው አይችልም።

3: ስልካችን መጠለፉን እና በህውሃት ማፍያ ቡድኑ ክትትል ላይ እንዳለን ፍንጭ ካየን ሲም ካርዱን ብቻ ሳይሆን ቀፎውንም ከጥቅም ውጭ ማድረግ አለብን።

4: ከተልእኮ ጋር የተያያዙ ማንኛውንም የስልክ ጥሪዋች ማድረግም ሆነ መቀበል በምንፈፅምበት ጊዜ ከማደሪያ ቦታችን እርቀን( ቢያንስ 3 ኪ.ሜ) ራቅ ብለን ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀስን መሆን አለበት። ስንጨርስ ስልካችንን በመዝጋት ወደ ማደሪያ ቤታችን መሄድ አለብን። ከምናድርበት ቦታ በፍፁም ስልክ መክፈት የለብንም።

5: የ IMEI ቁጥራቸው በቀላሉ መለወጥ( Edit) መደረግ የሚችሉ የስልክ ቀፎዋችን መጠቀም ቀፎውን ከመቀያየር ይታደገናል። ምሳሌ: የማንኛውም ብራንድ copy ስልክ. በተለምዶ ፎርጅድ የሚባለው አይነት። ከ China የሚመረቱትን። መርካቶ ሞልቷል። ይሄን ካደረግን የ ህውሃት ዘራፊ እና ወንበዴ ቡድን የ Mobile Technology ተጠቅሞ በቁጥጥር ስር ሊያውለን አይችልም።

በ ምስጋናው