ከት/ቤት በመቅረት ብቻ ሳይሆን ፥ት/ቤትም ተገኝተው ባለማስተማር የመምህራን አድማ ቀጥሏል

Standard

           በአብዛኛው ጎጃም የተጀመረው የመምህራን አድማ ከት/ቤት በመቅረት ብቻ ሳይሆን በመገኘትና ባለማስተማር ቀጥሏል። መምህራን ተማሪወችን የአድማው ተካፉይ ለማድረግ ት/ቤት በመገኘትና በክፍለጊዜ በመግባት ባለማስተማር በዚያ ፈንታ ስለአድማውና የህወሓት ወያኔ ቡድን በህዝቡ ላይ ስለሚያደርሰው ግፍ በመንገር ተማሪወችን የትግሉ አጋር ለማድረግ ብዙወች መምህራን አድማውን በመቀላቀል ቆርጠው ተነስተዋል።
የመምህራን አድማ እየተስፉፉ ባለበት በዚህ ውቅት አድማውን ይመራሉ የተባሉ መምህራን እየታደኑ በየቤታቸው እየታፈኑ እየታሰሩ ይገኛል።በሀገሪቱ ብቁ ዜጋን ከመፍጠር ጋር ተያይዞ የመምህራን ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ቢታመንም በአብዛኛው የሁለተኛና ከፍተኛ መሰናዶ ት/ቤት ርዕሳነ መምህራንን ቀንደኛ የህወሓት አባል በማድረግ የመምህራንን በምልፈንና ቅስም በመስበር፣የሙያወች ሁሉ መሰረትነታቸው ተንቆ በባለጊዜወች በመጨቆን ከስራ ገበታቸው ያለአግባብ ሲሰናበቱ ፣ደሞዛቸው በተለያየ ስም ሲቆራረጥ መቆየቱ ይታወቃል። በእርግጥ ዛሬ ከትምህርት ቤት ቀሩ እንጂ ቀድሞኑም ከትምህርት ቤት ተገኝተው በህወሓት ግፊት ምክንያት ትክክለኛውን ት/ት ለትውልድ ቀረፃ እንዳይሰጡ የተደረጉም ሞልተዋል።

መምህርነት የሁሉ መሰረት ነው !!

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.