በመላ ሀገሪቱ በተነሳበት ህዝባዊ አመፅ በሃይል ለማርገብ በተለያየ ጊዜ ና ቦታ የሚያሰፍራቸው ወታደሮች ለትራንስፖርት ነዳጂ ፣ለካምፕ ተከላ ፣ ለምሽግ ስራ ፣ ለመንገድ ጠረጋ ፣ለቅድመ ጥናት ፣ለጊዜያዊ ሰፈራ አካባቢያዊ የምግብ ፍጆታ በአካባቢው አየር ጋር የሚቀያየር የወታደራዊ አልባሳት ወዘተርፈ መሰል ጉዳዩች ወታደራዊ ሃይሉን ከማንቀሳቀስ ጋር ብቻ ከበጀቱ በተጨማሪ በ6.5 – 7 ሚሊየን ብር የሚገመት ወጭ አድርጓል።ይህም ከደረሰበት የካምፕ ግምጃ ቤት ቃጠሎ፣ የጦር መሳሪያ ምርኮ፣ ሌሎች የባከኑ ነገሮች ጋር ሳይጨመር ነው። ሌላው በወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕች በውጭ እርዳታ የሚያሰለጥኑ የውጭ ሃገር ወታደራዊ መኮንኖች ወደ ሃገራቸው በመመለስ ላይ ናቸው ። እንደምክንያት የቀረበው ደግሞ የሰልጣኝ ምልምል ወታደር መጠን አለመሟላት የሚል ሁኗል። ወደ ውጭ ሀገራት ለስልጠና የሚላኩ የህወሓት ከፍተኛ መኮንኖች ለጉዞና መሰል ተጨማሪ ጉርሻወች ከገንዘብ እጥረት ጋር ተያይዞ እንደተቆራረጠ እየተነገረ ነው ።በቅርቡ ጥር ወር የታወጀው የደሞዝ ጭማሪ ወታደሩን አለማካተቱና ተጨማሪ ጥቅማጥቅሞች (የንፅህና መጠበቂያ፣የስልጠና የትምህርት ዕድል ልዩ ዕረፍትን የጨመረ) ተመርጦ ለትግራይ ባለማዕረግ ወታደሮች መሆኑ ና ለተራው ምስኪን ወታደር የሚደረግለት የጥቅማጥቅም ጉርሻ እየተቀናነሰና እየቀረ መሆኑ በአንዳንድ የጦር ክፍሎች የውስጥ አመፅን ቀስቅሷል። ከዚህ በተጨማሪ በሚከዱና በሚሰወሩ ወታደሮች ምክንያት በየጊዜው ወታደራዊ ዘመቻ ዕቅድና አጠቃላይ ስምሪት ለመቀየር ተገዷል።ከህዝባዊ እምቢተኝነቱ በኃላ ዛሬ 5ኛ ወሩን የደፈነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጂ ከታወጀ ወዲህ በተለይ በሰሜን ጎንደር ደባርቅ ፣ዳባት ፣ወገራ ፣በጎጃም ጃዊ እንዲሁም በኦሮሚያ የተወሰኑ ቦታወች ያሰፈራቸውን ወታደሮች በግማሽ ያክል እያስወጣ ቢሆንም በምትኩ ሌላ ወታደሮችን ለማስፈር የዝውውር ስራ እየሰራ እንደሆነ እና አጠቃላይ በየክፍለጦሩ የሃይል አሰላለፍ የፕወዛ ስራን እየሰራ እንደሆነ ተሰምቷል። ለዚህ የገዛ ወታደሩን ባለማመን በሚፈፅመው የእውር ድንብር ተግባሩም ከፍተኛ ወጭ ጋር እየተሽመደመደ የሚገኘው የህወሓት ገቢ ኢኮኖሚ የወታደራዊ የሃይል ሚዛን ማመጣጠን እንዳልቻለ የዘርፍ ባለሙያወች ይናገራሉ።
@እንቅዩጳዝዩን