የመምህራን የደምወዝ  ጭማሬ ጥያቄ ቀጥሏል

Standard

      ​ከመጋቢት 4 እስከ 8 ለአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት የስራ ማቆም አድማ በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች እንዲደረግ  ታምኖበታል ። በመሆኑም ስራ የማቆም አድማው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ደሞዝ እንደሌላው ሰራተኝ እስካልተጨመረ የሚቀጥል ይሆናል ። በመሆኑም መምህር የሆነ አካል ሁሉ መረጃውን በሚመቸው መልኩ ለሁሉም ያዳርስ። እየሰሩ መጠየቅ የሚል የወያኔ ፈሊጥ ፈፅሞ ተቀባይነት አይኖረውም። ይህ ፍፁም የሆነ መረን የለቀቀ ንቀት ነው ።

      በሌላ ዜና በአማራ ክልል የመምህራን እስር ቀጥሏል በዛሬው እለት በወራኢሉ አጠቃላይ እና መሰናዶ ትምህርት ቤት ያስተምሩ የነበሩት መምህር ጀማል አደም የኬምስትሪ መምህር መምህር ሁሴን አሊ የሲቪክስ መምህር እና መምህር የሺዋስ አጥሌ የእንግሊዘኛ መምህር ታስረው ይገኛሉ።

       የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት የደመወዝ እርከን ማሻሻያው መምህራንን ያካተተ እንዲሆን ለማድረግ ከትላንት ጀምሮ ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ። ይህ ውይይት በአፋጣኝ ተግባራዊ እንዲደረግ እየጠየቅን ሌሎች ክልሎችም ተመሳሳይ ድርጊት እስኪፈፅሙ ድረስ ትግላችን ይቀጥላል።

“” ክብርና ሞገስ ለመምህራን!!!!!””

©ከታ ማኛ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.