የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ ህውሃት በኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች መካከል ተፈጥሮ የነበረውን ከህውሃት ነጻ የመውጣት ፍላጎት ሙሉ በሙሉ መደፍጠጡን እያየን ነው

Standard

           ባለፈው አመት የነበረውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በኦህዴድና በብአዴን አካባቢ ራሳቸውን ከህውሃት ቀንበር ነጻ ለመውጣት ፍላጎት የሚያሳዩ፥ የወያኔን ፍጹማዊ የበላይነት በግልጽ የሚተቹ፥ አልፎ አልፎም የአቅማቸውን ያህል የህዝቡን ተቃውሞ ለመደገፍ ሙከራ የሚያደርጉ ካድሬዎች ብቅ ብቅ ማለት ጀምረው ነበር።

         ለምሳሌ አባይ ጸሃይ ራሱ እንደመሰከረው የኦህዴድ የዞንና የወረዳ ካድሬዎች ከህዝቡ እኩል የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እንዳይተገበር እንቅፋት ሆነዋል ሲል ኮንኗቸው ነበር። በወቅቱ ምንም እንኳን እነዚህን ካድሬዎች “ልክ እናስገባለን” ተብሎ ቢፎከርም ልክ የገቡት ግን ፎካሪዎቹ እንደነበሩ እናስታውሳለን።

           በአማራ ክልልም ቢሆን የወልቃይትን የማንነት ጥያቄ ተከትሎ በተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ አቶ ገዱና ለእሳቸው ቅርበት የነበራቸው ብዙ ካድሬዎች የህዝቡን ጥያቄ ፍትሃዊነት ተቀብለው እንደነበር አንዘነጋም። በወቅቱ እነ አቶ ገዱና በርካታ ካድሬዎች በአንድ ወገን የአባይ ጸሃይ ፈረሶቹ በረከት ስምኦን፥ አዲሱ ለገሰ ካሳ ተክለብርሃንና አለምነው መኮንን በሌላ ወገን ሲሆኑ ደመቀ መኮንን ደግሞ በልጅነቱ ያመለጠውን ዥዋዥዌ ይጫወት እንደነበር የምንዘነጋው አይደለም (ደመቀ አቶ ገዱን ሲያገኘው የህዝቡ ጥያቄ ፍትሃዊ ነው እያለ ከእነበረከት ጋር ሲሆን ደግሞ የጸረ ሰላም ሃይሎች ጥያቄ ነው ይል ነበር)።

         እነ አይጋ በብአዴን ውስጥ ተፈጥሮ የነበረውን መነቃቃት እንደ ትልቅ ድፍረት በመቁጠር “ጄላቲ እያስላስን ያሳደግነው ህጻን እንዴት ቢደፍረን ነው” በሚል አይነት እብሪት በትግሉ ወቅት የብአዴን ሚና ግጥም ማንበብ እንደነበረ ጽፈው እንዳስነበቡን የምንዘነጋው አይሆንም።

       ዛሬ ግን ብአዴንም ሆነ ኦህዴድ ለህውሃት መገበራቸውን በመግለጫዎቻቸው እየተናገሩ ናቸው። ኦህዴድ አስተዳድረዋለሁ በሚለው ክልል ውስጥ ከሶማሌ ክልል የመጡ ታጣቂዎች ያሻቸውን ሲያስሩ፥ ያሻቸውን ሲገድሉ፥ ያሻቸውን ያህል ሴት እህቶቻችንን ሲደፍሩ እያየና እየሰማ እንዲህ አይነት ግፍ በህዝብ ላይ አለመፈጸሙን ያለሃፍረት ሲያስተባብል እየሰማን ነው። ብአዴን ደግሞ የወልቃይት የማንነት ጥያቄ የጸረ ሰላም ሃይሎችና የትምክህተኞች ጥያቄ እንጂ የህዝቡ አይደለም ሲል ሰምተናል። ነገ ደግሞ ከህዝቡ የተውጣጡ የአገር ሽማግሌዎችና የክልሉ ካቢኔ አባላት የትግራይ ክልልን ይቅርታ ለመጠየቅ መቀሌ ገቡ የሚል ዜና ሪፖርተር ላይ እናነብ ይሆናል።

        በተቃውሞው ጎራ ደግሞ የጎንደር ህዝብ በኦሮሚያ የሚፈሰው ደም የእኛም ደም ነው በማለቱ ተፈጥሮ የነበረ የተጠቂዎች መተሳሰብ (victims solidarity) ከኦሮሚያ የነጻነት ቻርተር በኋላ ወደነበረበት ተመልሶና ከትቢያ በታች ገብቶ ጎራ ለይተን እየተፏከትን እንገኛለን። እኛ የቱንም ያህል የተለያየ ራእይ፥ የተለያየ የፖለቲካ ግብ፥ የማይቀራረብ ትርክት እንዳለን አምነን ብንሻኮትም ለወያኔ ግን ያው አንድ አንድ ነን። ጠላቶች። ለወያኔ ፕሮፌሰር ብርሃኑም፥ ዶ/ር መረራም ኦቦ ጀዋርም ጠላቶች ናቸው። እንደው ሌላው ቢቀር ይህን መራራ እውነት እንኳ ተረድተን እንዴት መተሳሰብና መተባበር ያቅተናል? ወይስ የጎንደር ህዝብ ዳግም ካልነገረን የማይገባን ደንቆሮዎች ነን?

©Muluneh Eyoel Fuge

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.