አሜሪካ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያላትን ግንኙነት ታቋርጥ ሲሉ የአሜሪካ ምክር ቤት አባላት ጠየቁ

Standard

ኢሳት (መጋቢት 1 ፥ 2009)ዩ ኤስ አሜሪካ ከጨቋኙ የኢትዮጵያ መንግስት ጋር ግንኙነቷን ታቋርጥ ሲሉ የአሜሪካ ምክር  ቤት አባል ኮንግረስ ማን ክሪስ ስሚዝ ጥሪ ሲያቀርቡ ሌላው የምክር ቤት አባል ኮንግረስ ማን ዳና ሮራባከር  ዩ ኤስ አሜሪካ አናሳዎችን ብቻ ከሚወክለው የኢትዮጵያ መንግስት ጋር የነበራት ግንኙነት ስህተት መሆኑን ተቀብላ ለሁለቱ ሃገራት ጥቅም የኢትዮጵያን ህዝብ መሰረት ያደረገ ግንኙነት እንድታደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ አደጋ ውስጥ ወድቋል በሚል ርዕስ በአሜሪካ ም/ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የአፍሪካ የጤናና የሰብዓዊ መብት ንዑስ ኮሚቴ ሃሙስ ማርች 9 2017 ባዘጋጀው መድረክ የተለያዩ ወገኖች በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ምስክርነት ሰጠዋል።

የንዑስ ኮሚቴው ሊቀመንበር ክሪስ ስሚዝ መድረኩን ምስክርነት ለሚሰጡ ሰዎች ከመልቀቃቸው በፊት ባቀረቡት ንግግር እስላማዊ አክራሪነትን እንዋጋለን በሚል ሰበብ ከጨቋኙ የኢትዮጵያ መንግስት ጋር የቀጠለው ግንኙነት ማብቂያው አሁን ነው ሲሉ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በሚወክሉ ኢትዮጵያውያን በመድረኩ ተገኘተው ምስከርነት ሰጥዋል።

በዚሁ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ በአሜሪካ ም/ቤት በተዘጋጀው መድረክ ሌላው የአሜሪካ ም/ቤት አባል ዳና ሮራባከር  በኢትዮጵያ ያለው መንግስት የሚወክለው አናሳዎችን ነው በማለት ጠቅሰው ይህንን ጨቋኝና ሙሰኛ ቡድን ስትደግፍ በመቆየቷ አሜሪካ መሳሳቷን በይፋ ማስታወቅና፣ ከአናሳው ቡድን ጋር የነበረው ጉዞ ትክልል እንዳልነበር መቀበል አለባት ብለዋል።

ወዳጅነታችን ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንጂ ከተወሰነ ቡድን ጋር መሆን አይገባውም ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። የአሜሪካም ሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ መብትና ጥቅም በሚጠበቀው ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ማዕከል ያደረገ ግንኙነት ስንመሰርት ነው በማለት የካሊፎርኒያ ኮንግሬስ ማን ዳና ሮራ ባከር ጥሪ አቅርበዋል። በምርጫ 1997 በኢትዮጵያውያን ላይ በደረሰው ጥቃት የአሜሪካ ወታደራዊ ቁሳቁዎች ስራ ላይ መዋላቸውን አስታውሰው የኢትዮጵያ መንግስት ከአሜሪካ መንግስት የጦር መሳሪያዎች እንዳይገዛ እንዲታገዱ ጥሪ አቅርበዋል።

በዚሁ መድረክ ላይ የቀረቡት በሂውማን ራይትስ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ፊሊክስ ሆርን አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምትከተለውን የውጭና የትብብር ፖሊሲ በማስተካከል ለሰብዓዊ መብት መከበር ቅድሚያ እንድትሰጥ ጠይቀዋል።

በወቅታዊ የሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ላይ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት እንዲሁም የኢትዮጵያ የማህበረሰብ ተወካዮች ሃሙስ ለአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች የምስክርነት ቃል አሰምተዋል። በዚሁ መድረክ ሰፊ ሪፖርትን ያቀረበው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች አባላት ለዚሁ የፖሊሲ ማስተካከያ ተግባራዊነት ትርጉም ያለው ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባ አስነብቧል።

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ከአመት አመት መባባስን እያሳየ እንደመጣ ያስረዳው ሂውማን ራይትስ ዎች አሜሪካ በኢትዮጵያ የምትከተለውን ፖሊሲ የማሻሻያ ጊዜው አሁን መሆኑን በአጽንዖት ገልጿል።

ለዚህ የፖሊሲ ማሻሻያ ተግባራዊነት የምክር ቤቱ አባላት በገሃድ በኢትዮጵያ መንግስት በመፈጸም ላይ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰትና ረገጣ ማውገዝ እንደሚጠበቅባቸውም ሂውማን ራይትስ ዎች በመድረኩ አሳስቧል። የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች አባላት በኢትዮጵያ በእስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጥሪን እንደሚያቀርቡም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ጠይቋል።

በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል ሲካሄድ ከቆየው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተገናኘ ለእስር የተዳረጉትን አቶ በቀለ ገርባና ዶ/ር መረራ ጉዲናን በዋቢነት በመጥቀስ ጥያቄውን ያቀረበው ሂውማን ራይትስ ዎች ተመራማሪ ሚስተር ፊሊክስ ሆንር በአሁኑ ወቅት መብታቸውን በመጠየቃቸው ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለእስር ተዳርገው እንደሚገኙም አመልክቷል።

በእስር ላይ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን አባላት ከእስር ይለቀቁ ሲል የጠየቀው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ገዢው የኢትዮጵያ መንግስት ለአፈና መጠቀሚያነት ተግባራዊ ያደረጋቸው የተለያዩ ህጎች የማስተካከያ ዕርምጃን እንደሚወስድባቸው አሳስቧል።

የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች አባላት የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን ጨምሮ ሌሎች ተመሳሳይ ተቋማት በኦሮሚያና አማራ ክልሎች በመንግስት የተፈጸሙ ግድያዎችንና የጅምላ እስራት በገለልገኝነት የማጣራት ስራን እንዲሰሩ ድጋፋቸውን እንዲያደርጉም ሂውማን ራይትስ ዎች ጠይቋል።

በዚህ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ በሚገኘው የህዝብ ተወካዮች መቀመጫ ከተካሄደው የምስክርነት መስማት ስነስርዓት ጎን ለጎን በርካታ ኢትዮጵያውያን በመሰባሰብ የአሜሪካ መንግስት አምባገነን ላሉት የኢትዮጵያ መንግስት ድጋፍን ከማድረግ እንዲቆጠብ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምትከተለውን ፖሊሲ እንድትፈትሽና የሰብዓዊ መብት መከበርን ቅድሚያ እንድትሰጥ የሚጠይቅ ውሳኔ ሃሳብ በኮንግረስ አባላት ዘንድ ከቀረበ በኋላ በርካታ አለም ቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ድጋፍ እየሰጡ እንደሚገኝ ታውቋል።

የተለያዩ አካላት በተገኙበት ሃሙስ ከሰዓት በኋላ በተካሄደው በዚሁ የምስክርነት መስማት መድረክ በተለይ ባለፈው አመት በኦሮሚያ ክልል ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ግድያ ሰፊ ትኩረትን አግኝቷል።

ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የመጡ ኢትዮጵያውያን አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዘርፈ-ብዙ ግንኙነት ተጠቅማ በሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት እንዲከበር ተፅዕኖ እንድታደርግ አሳስበዋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s