ቆሼን የናደው ወያኔ ነው

Standard

በአ.አ በተለምዶ ቆሸ ተብሎ የሚጠራው የቆሻሻ ተራራ ተደርምሶ እስከ ዛሬ ምሽት 12:00 ሰዓት ድረስ ድብቅ የህዋህት ሴራ መሆኑን እያወቀ ግን ርካሽ በወገን ላይ የእልቂት ዘመቻ ያወጀው የከተማ አስተዳደሩ አፉን ሞልቶ 34 ሴት እና 12 ወንድ በድምሩ 46 እስካሁን ሒወታቸው አልፏል አለ፡፡ የሞት መጠኑም በጣም እንደሚያሻቅብ ይጠበቃል በማለት ከ100 በላይ የሟች ቁጥር እንደሚሆን እያወቀ ድሪባ ኩማ የሀዘን አዋጅ እንደታወጀ እንኳ ሳይናገር ቀረ። ለማንኛውም የሟቾች ሚስጥር የእውነት ከአዳጋው የተረፉ እናቶች እያለቀሱ ትናንት አርብ በኤክስካቫተር እና ሌሎች የግንባታ ማሽኖች እየዛቁት ስናይ እኩል መሀሌ ተሰነጠቀ። እኛም እባካቹህ ልጆች ይህ ተራራ ተንዶ እናልቃለን አልናቸው። የማሽን ኦፕሬተር ሾፌሮችም የከተማ አስተዳደሩ አስገድዶን ነው የሚያሰራን ብለዋል። የሚደርሰውንም አደጋ ጠንቅቀው ያውቃሉ። ቦታው እንደሚፈለግ እና መልቀቅ እንዳለባቹህ ህገ ወጥ ግንባታን በስር ነቀል መልኩ ለማስቀረት የተወጠነ እንደሆነ መልስ ሲያገኙ ወጣቶች ደግሞ በቁጭት ሰብሰብ ብለው ወያኔ ፈጀን እያወቁ ሆን ተብሎ ነው በማለት አንዳንዶቹ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይናገራሉ፡፡ በስፍራው በብዛት የተሰማራው የከተመዋ ፖሊስም የወጣቶችን የቁጭት ድምፅ እየሰሙ እንደልሰሙ ያልፏቸው እንደነበር አየሁ፡፡
ሌላው የሚገርነው ደግሞ እኮ አይደለም በአፋጣኝ ሌላው የሀገሪቱ ዜጋ ጉዳታችን ሰምቶ ሊደርስልን ቀርቶ የቅርቡ የአ.አ ህዝብ እንኳ በውል በለመስማቱ ከተመዋ ሞቅ ብላ በተለመደው እንቅስቃሴዋ ነው የዋለችው፡፡ ምክንያቱም የሀገሪቱ የመገናኛ አውታር ተብየው እንኳ ጉዳቱ ከደረሰ ከ16 ሰዓት በኃላ ነው ለዜና ያበቃው፡፡ ህዝብ ተረባርቦ ካተረፈን የወያኔ ሴራ ስለሚከሽፍ፡፡ ፈጣሪ ፍረድ። ዘገየህ ምነው አምላካችን በማለት እናት እና አባቶች መሬት ላይ ያለቤተሰብ እንደቀሩ በሲቃ ይንከባለሉ እንደነበር አየሁ፡፡

ይህን መሰል የተጠና ተግባርም የዝቋላን ገዳም ከፍተኛ ጥቅጥቅ ያለውን ተፈጥሮአዊ ደን በእሳት በመለኮስ ማህበረሰቡ ያቅሙን ለማጥፋት ሲጥር ሄልኮፋተር በዝቅታ በመብረር ለማጥፋት በሚመስል ሁኔታ ማህ- ድንጋጤ ውስጥ ገብቶ አብዛኛውን አወደሙት፡፡ ለምን? ለሚለው ወያኔ ለሚሰጋባቸው ታጋይ ሽፍታ የሀብት ምንጭ ወዘተ እንዳይውል ስጋት፡፡ ስለዚህ ወያኔ ከዚህ በላይ ገና የበርካቶችን ምስኪን የግል መኖርያ ቤት ሳይቀር ማቃጠሉ እንደማይቀር ወገራ እንቃሽ ጎንደር አይተናል ፡፡

ለዘወትር ተባባሪ የአይን እማኝ ሪፖርተር እናመሰግናለን።ይሄንን መልእክት አንብበው ሲጨርሱ ከሚረዱት ፍሬ ነጥብ መሀል አንዱ በሀገራችን መረጃ የመለዋወጥ አቅማችን ምን ያህል የወረደ እንደሆነ ነው !!! ለዚህም ትልቁ ማሳያ ለቆሼ ሰፈር ነዋሪዎች እዛው ፊት ለፊታቸው ያሉት ወገኖቻቸው በተገቢው መንገድ ሊደርሱላቸው አለመቻላቸው ነው ፤ እናም ወዳጆቼ መልእክቶችን ሼር በማድረግ መረጃዎችን በፍጥነት እናዳርስ !!

መረጃ ሀይል ነው ! መረጃ ሒወት ነው !

መረጃ ከሚያንሰን ደም ይጠረን !

©Asnakew Abebe

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s