​ሀዘኑ አይበቃም ወይ 

Standard

አገራችንን ኢትዮጵያ የወያኔ አምባገነን ስርዓት ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ አገሪቷ ሃዘን ተለይቷት አያውቅም እንዲያውም ኢትዮጵያ ውስጥ ሃዘን ከመብዛቱ የተነሳ ሀዘኑን መልመድ ጀምረናል ውለን ባደርን ቁጥር አዲስ ሃዘን መስማት የቀን ተቀን ውሎአችን ሆኗል ዛሬ ዛሬ በሃዘን ሳይሆን የምንደነግጠው በደስታ ሆኗል ኢትዮጵያ ውስጥ ደስታ ከመጥፋቱ የተነሳ የሰው ልጅ ደስታን በሰማ ቁጥር ትልቅ ነገር ሆኗል ።

አገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ባህልና ሃይማኖት ባለቤት ሆና ህዝቦቿ ግን እነዚህን እሴቶቿን ለማክበር እንኳን ያልታደሉ በአመት ጥቂት ቀናቶችን እንኳን መደሰት ያልቻሉ ሆነዋል በዓል በመጣ ቁጥር ህዝብ ካለበት የኑሮ ውድነት በሌማቱ እንጀራ መጥፋቱ በድስቱ ወጥ ያለመኖሩ ሳይሆን የሚያስጨንቀው የበዓሉ መምጣትና በሰላም በዓሉ ማለፉ ሆኗል ከበዓሉ በኋላ የበዓሉን መልካምነት ከመናገር ይልቅ የበዓሉ በሰላም ማለፍ መጠያየቅ የተለመደ ነገር ሆኗል በአላቶች እንደ ቀደምቶቹ ዘመናት ከተሞች በዓል በዓል ከመምሰል ይልቅ የጦርነት ከተማ ይመስል ከቀላል እስከ ከባድ መሳሪያ ተደቅኖባቸው ከመዋላቸው በላይ ይህንን አትልበስ ይህንን አትናገር እየተባለ ማስጠንቀቂያና ዛቻ የሚነገርበት በመሆኑ ምክንያት ህዝብ በዓልን ሲመጣ ከማየት ይልቅ በዓል እንዳይመጣ መመኘትን መርጧል ።

ሆኖም ግን የቱንም ያክል ህዝብ ለመኖር ሲል አንገቱን ቢደፋና ቢያጎነብስ ያን የሚመኛትን ሰላም ሳይሆን ወጥቶ መግባቱን ሊያገኛት ፈፅሞ አልተቻለውም ዛሬ ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ከቆመ በታች ከሞተ በላይ ሆኖ መኖር እንደ ፅድቅ ሆኖ መቆጠር ከጀመረ ሰንብቷል ለዘመናት ሲኖርበት ከነበረው ቀዬውና ቤቱ በልማት ስም ያለምንም መተኪያ ተባሮ ሲወጣ ማየት ተለምዷል ነገር ግን ወጥቶም እንኳን ከመንገድ ዳር ለመኖር ያልተቻለበት ዘመን ላይ ተደርሷል የቀድሞው ሰይጣን መለስ በሞተ ጊዜ እኛ እንደ ቀልድ ያየናት ነገር ግን የጎዳና ተዳዳሪዎች የገባቸው ነገር ስለነበር ነው ለካ እርሶን ተማምነን ነበር ጎዳና የወጣነው አሁን ማን አባት ይሆነናል ያሉት ለካስ ይህ እንዲመጣ አውቀው ነበር እናም ወገን በየሄደበት መሞት ተራ ነገር ሆኗል ።

ታዲያ ይህ ሃዘን መቼ ነው የሚበቃው ፅዋውስ መቼ ነው የሚሞላው ወይስ በሃዘን መደሰት ለመድን አዎ አሁን ወገንን የሚገድለው ወያኔ አይደለም ወገንን የሚያሳድደው ወያኔም አይደለም በወገን ሞት ከእንግዲህ ወዲያ ተጠያቂው እኔና እናንተ ነን አይተን እንዳላየን እየሆንን ያለነው ሃዘኑ ውስጣችን ያልገባ ላይ ላዩን ብቻ የምናስመስል ዛሬን ብቻ እስከምናልፍ የምንቆጭ ለነገ ግን ለወገኔ በቃኝ አምርሬያለሁ ማለት ያቃተን ሆነናል ።

ወገኔ የወገኖቻችን ነፃነት እና ሞት በእኔና በእናንተ እጅ ነው ያለው በእውነት ስለወገን ሞትና ስደት መከራና ስቃይ ይብቃ ብለን ከተነሳን ዛሬውኑ እንባችንን ማድረቅ እንችላለን ። ለዚህም ከእኛ ብዙ አይጠበቅብንም በምናምንበትና በተደራጀንበት መንገድ ይህንን የአፓርታይድ ስርዓት ከስሩ መንቅለን ለመጣል ዛሬ ነገ ሳንል መሬት ላይ ወርደን እንታገል መታገል ካልቻልንም በምንችለው አቅማችን ለሚታገሉት ታጋዮች ስንቅና ትጥቅ በማቀበል የታጋዮቻችን ደጀን እንሁን ይህንን እስካላደረግን ድረስ ግን ገዢዎቻችን እኛንና ቤተሰቦቻችንን ከማሰቃየትና ከመግደል ወደኋላ አይመለሱም ዛሬ ከቆመ በታች ከሞተ በላይ መኖር ያልተቻለበት አገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት ስለዚህ ወገኔ ሃዘን ላይ ሳይሆን ትግል ላይ አምርር ነፃነት ለማግኘት አምርሮና ቆርጦ መታገል ግድ ነውና ስለዚህ ሃዘኑ በኔ ይብቃ ብለን እንነሳ ።

የወገንህ ሃዘን ውስጥህ ገብቶ ልብህን ካደማው ለቅሶህን አቁምና አምርረህ ታገል ።

©ዘነበ ዘ ቂርቆስ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.