በሰሜን ጎንደር የወያኔ ጦር ሽንፈት ገጠመው

Standard

የጀግናው አርበኛ ጎቤ ጦር በሰሜን ጎንደር ዞን ዛሬ መጋቢት 5 ቀን 2009 ዓ.ም. ረፋድ 3.30 ተኩል ጀምሮ ከወያኔ ትግሬ መከላከያ ጋር ባደረገው እልህ አስጨራሽ ውጊያ ድል ቀንቶታል፡፡ እስከ እኩለ ቀን ድረስ በቆየው ጠንካራ ውጊያ የጀግናው አርበኛ ጎቤ ጦር 13 የወያኔ መከላከያ ሠራዊት አባላትን የገደለ ሲሆን አንድ የወያኔን ጦር ደግሞ አቁስሎ ማርኳል፡፡ 

በአርበኛ ጎቤ እግር ተተክቶ ጦሩን ሲመራ የነበረው አርበኛ ሻንቆ ‹‹የመሪያችን ሞት በሚገባ ተበቅለናል፤ ተጋድሎአችን እስከ ያለምንም ጥርጥር ያሸንፋል›› ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡ የዐማራው ጦር የተማረከውን ወታደር ጨምሮ የ14 ወታደሮችን ሙሉ ትጥቅ የማረከ ሲሆን ከባለፈው ወር ወዲህ የተገኘ ታላቅ ወታደራዊ ድል እንደሆነ ተገልጧል፡፡ 

የዐማራ አርበኞችን ለማጥቃት የመጣው ጦር መሣሪያውን በዱር እየጣለ ወደ አቅራቢያ ከተማ የሸሸ ሲሆን የአካባቢው ገበሬዎች በዱር የወዳደቀ ብዙ መሣሪያ እየያዙ እንደሄዱም ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

(ማሳሰቢያ፤ በአርበኞቹ ጥያቄ መሠረት ጦርነቱ የተካሔደበትን ቦታ ከመግለጽ ተቆጥበናል)

©Muluken Tesfaw

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.