የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ጋዜጣዊ መግለጫ

Standard

ለሃያ ስድስት አመታት የዘለቀው የህወሃት / ኢህአዴግ ጨቋኝ አገዛዝ በወገኖቻችን ላይ ያደረሰውና እያደረሰ ያለው ግፍና መከራ ቅጥ ያጣ መሆኑ ለሁላችንም ግልጽ ከሆነ ቆይቷል። ዕለት ተዕለት በወገኖቻቻን ላይ የሚደርሰው የማዋረድና የሰቃይ ገፈት በተለያየ መልኩ ለስርአቱ ታማኝ በሆኑ የጸጥታ የፖሊስና የሚሊሽያ ኃይሎች ይፈጸማል። ይህ ህዝብን ያለማቋረጥ የማሰቃየትና የመበደል ስራን ዋነኛ ሙያው ያደረገው ዘረኛ ስርአት በአደባባይ በጠራራ ጸሃይ ወገኖቻችንን በጥይት መቁላት አልበቃ ብሎት ዛሬ ደግሞ የሰርአቱ ግፈኞች ጠግበው በሚጥሉት የቆሻሻ ናዳ ህጻናት ሴቶች ወንዶች አዛውንትና ወጣቶች ለሞትና ለአካል ጉዳት እንዲዳረጉ እያደረገ ነው። ወገኖቻቻን የሚልሱት የሚቀምሱት አጥተው በረሃብ ሰቆቃ በሚሰቃዩበት በዚህ ወቅት “ታላቅ የኢኮኖሚ እድገት” አስመዝግቤአለሁ እያለ ያለማሰለስ የሚያቅራራው የህወሃት/ ኢህአዴግ መንግስት ለከፍተኛ የአመራር አባላቱና በሙስና ለተዘፈቁ ጥቂት አድርባዮቹ የቅንጦት ደሴት ፈጥሮ በወገኖቻቻን ላይ የበደልና የመከራ ቀንበር በመጫን በአገራችን ታሪክ ወደር  የሌለው የግፍና የሙስና ስርአት ገንብቷል። ይህ የህወሃት/ኢህአዴግ የፖለቲካ የኢኮኖሚና ማሀበራዊ በደል ያስመረራቸው ወገኖቻችን ቀጣይነት ባለው ህዝባዊ እምቢተኝነት ለነጻነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ መከበር የሚያደርጉት ትግል በተፋፈመበት በዚህ ወቅት ስርአቱ የሚያደርሰው በደል እየከፋ እንደሄድ ብዙም የሚያከራክር አይደለም። የኢዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ በዚህ ባለፈው ሳምንት ከአዲስ አበባ ወጣ በሎ በሚገኘው የቆሻሻ መጣያ ዙሪያ የሚኖሩና ከዚያ ቆሻሻ በሚገኝ ልቅምቃሚ የአሳር ኑሮአቸውን በሚገፉ ወገኖቻቻን ላይ የደረሰው አሰቃቂ የሞትና የመቁሰል አደጋም የስር አቱ አምባገነናዊ የፖለቲካና የኢኮኖሚ መርህ ውጤት ነው ብሎ ያምናል።
“የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ወገኖቻችን በህወሃት/ኢህአዴግ  የተዋረደው ክብራቸውን አስመልሰው በክብርና በነጻነት ሊኖሩ የሚችሉት ይህ ስርአት በአስቸኳይ ተወግዶ በዲሞክራሲና በህግ የበላይነት ላይ የቆመ ስርአት ሲመሰረት ብቻ ነው ብሎ ያመናል። ለዚህ የነጻነት ትግል መሳካትም በአራቱ ማዕዘን ያሉ ወገኖቻችን የትግል ክንዳቸውን አስተባብረው ይህ የመከራ ዘመን እንዲያበቃ  መታገል አማራጭ የሌለው ስልት መሆኑን ተረድተው በአዲስ መንፈስ እንዲነሳሱ ጥሪ እናቀርባለን።  በእኛም በኩል ትግሉ የሚጠይቀውን መስዋእትነት ለመክፈልና ትግሉም ከታለመለት ግብ እንዲደርስ የድርሻችንን ለመወጣት ዝግጁ መሆናችንን ዳግም እናረጋግጣለን።” ሲሉ ዶክተር ዲማ ነጎ የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ገልጸዋል። በመጨረሻም ይህ አስቃቂ የሞትና የመቁሰል አደጋ  ለደረሰባቸው ወገኖች መጽናናቱን እንዲሰጣቸው ክልብ  እንመኛለን።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.