​የቆሻሻው መደርመስ ምስጢር ሲወጣ

Standard

ከቆሻሻው መደርመስ 6 ሰዓታት ቀደም ብሎ አንድ የመንግስት የወታደር ኦራል በአካባቢው ቆሞ እንደነበር እና በግምት ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት አካባቢ  (አንድ ቀን ቀደም ብሎ)  በቦታው የሚያልፉ ሰዎችን መንገድ ቀይረው እንዲሄዱ ትዕዛዝ ይሰጡ እንደነበር ፥ ድርመሳው ከመከሰቱ ቀደም ብሎ የኦራል መኪናው ፖታውን ለቆ እንደሄደ ፥ ወደ ምሳ ስዓት ላይም ሌላ ፒካፕ በፖታው እንደነበር ፥  አንድ ታማኝ ምንጭ አሁን ጉዳዩን ከአዲስ አበባ ደውሎ አስረድቶኛል ። እንደ ታማኝ ምንጫችን ዘገባ ከሆነ ፥  መንግስት ምናልባት ለህንፃ ማፍረሻነት የሚሆን ቦምብ ተጠቅሞ ፥ ይህንንም ቦምብ በጥልቀት ከቆሻሻው ክምር መሰረት ላይ በመቅበር ሆን ብሎ ሊያደርገው እንደሚችል ፥ ይህንንም የሚያመልክቱ አንዳንድ ፍንጮች እንዳዩ ፥ ነገሩን አይተዋል የሚባሉ የተወሰኑትን  የአካባቢው ልጆች አፍነው በመውሰድ ፥ በቆሻሻ መደርመስ ህይወታቸውን ያጡ በማስመሰል መንግስት እያወራ ሲሆን ፥ እንደ ወዳጃችን ዘገባ ከሆነ ፥ ይህም የተደረገበት አደጋው ከተፈጠረ በኋላ በፍጥነት ነዋሪውን ከዚያ አካባቢ በማስነሳት ፥ የማይረባ የቦታ ካሳ በመክፈል ቦታውን ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለ ነገር ሊሆን እንደሚችል ዘግቧል ! 

በሌላ ጎኑ መብራት ስለመጥፋቱ ፥ እሳት ከስሩ ስለመለኮሱ እና ከዚያ ቀደም ብሎ ባካባቢው የሚኖሩ ሰዎችን በታ ስለማስለቀቅ የነበሩ ሂደቶች ጠቋሚ ሊሆኑ እንደሚችሉም ወዳጃችንን ነግሮናል ። የፍንዳታ ድምፅ አለመሰማቱ ፥ ምናልባት ቡምቡ በጥልቀት ከሆነ የተቀበረው ፥ የመደርመስ ድምፁ ጋር በአንድነት ስለሚወጣ እና የህንፃ መደርመሻ ቦንብ ደሞ ድምፁ የተጋነነ እንዳልሆነ አስረድቶኛል ! 
መረጃዎችን ለመመርመር እና ይፋዊ ዘገባ ለመስጠት እንዲያስችል ተጨማሪ መረጃዎችን ጠይቀን በመጠባበቅ ላይ ነን !
©ኄኖክ የሺጥላ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s