ወያኔ እና ተላላኪዎቹ

Standard

የሰው ልጅ ደደብ ተብሎ ባይሰደብም ቅሉ አንዳንድ ደደብ ግን የወያኔን ገዳይነት ፣ አሳሪነት ፣ ጨቋኝነትና አምባገነንነት ስትነግራቸው በመሳደብ ሊደብቁለት ሊከላከሉለት ሲዳዳቸው ታያለህ፡፡ እነዚህ የወያኔ ቡችላ ባንዳዎች ወያኔ ለሚወረውርላቸው ፍርፋሪ ሲሉ ብቻ ህሊናቸውን የሸጡ ቱሪናፋዎች ናቸው፡፡ ለወያኔም ሆነ ለነዚህ ህሊናቸውን ሽጠው ለሆዳቸው ያደሩ ርካሽ ባንዳዎች እንዲያውቁት የሚገባው ነገር ኢትዮጵያ በታሪኳ እንደወያኔ አይነት ገዳይ ፣ አሳሪ፣ ሌባ ፣ ውሸታም ፣ ዘረኛ ፣ ጨቋኝ ፣ ግፈኛ ፣ የመሀይም ጥርቅም ፣ ሀገር ሻጭ ፣ የለየለት የወንበዴ ስብስብ እና የመጨረሻው አምባገነን ስርዓት አይታም አጋጥሟትም አያውቅም ለወደፊቱም እንደዚህ አይነት ሰይጣን ኢትዮጵያን አይገዛም፡፡ ለእነዚህ ባንዳዎች ማለት የምፈልገው፦

ኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲያዊ መንግስት እንደሌለ እና የዜጎች ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እየተጣሱ ለመሆኑ ዓለም ያወቀው ሀቅ ነው፡፡ እያንዳንዱ ዜጋም ጠንቅቆ የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡ ለሕዝቡ መብት የሚታገሉና ፤ መብቱ እንዲከበር በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ ያቀረቡ ፓርቲዎችን በማፍረስ ፣ በማዳከም ፣ ብሎም መሪዎቻቸውን እና አባሎቻቸውን ያለፍትህ በማሰርና በተንዛዛ የፍርድ ሂደት በማንገላታት እውነተኛ ተቃዋሚ ፓርቲን በማጥፋት ሁሉንም በሞኖፖል ተቆጣጥሮ የማይለወጥ የማይገረሰስ ገዢ ሆኖ ለመቆየትም የአስቸኳይ ጊዜ አወጀ ዛሬ ግን የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጁ ተነሳም አልተነሳም ሕዝቡ ለመብቱ የሚያደርገው ትግል አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

©Keta

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.