ትኩረት ለማስቀየስ/ለመንፈግ እየተሞከረበት ያለው የሀገሪቷ መጻኢ የኢኮኖሚ ሁኔታ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው። የአማራው ተጋድሎ ከተነሳ በኋላ የውጭ ኢንቨስትመንት በ20በመቶ ቀንሷል። በአንዳንድ አካባቢዎች የተነሳው ድርቅ ከቀጠለ በ10 ዓመታት ውስጥ በሃገሪቷ ታይቶ የማይታወቅ ድርቅ ይከሰታል ተብሎ ይገመታል። በመሰረታዊ ፍጆታዎች ላይ የዋጋ ግሽበቱ በጣም ከፍተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የመካከለኛ ገቢ ነዋሪ ተብሎ የሚመደበው የሃገሪቷ ህዝብ ለመኖር ወደሚከብድ ደረጃ የሚሸጋገር ይሆናል። በደመወዝ ለማስተካከል እየተሞከረ ቢሆንም ግሽበቱን ከማባባስ ውጭ የሚፈይደው ነገር የለም። በቅርብ ከሚጽድቀው የአሜሪካን የውጭ ጉዳይ በጀት በ37% መቀነስ ጋር ተያይዞ የወያኔ መንግስት የሚያላውስ ገንዘብ ከትራምፕ አስተዳደር ያገኛል ተብሎ አይገመትም። ያለው አማራጭ የሃገሪቷን መተማመኛና የችግር ጊዜ መውጫ ተቋማቷን በማስያዝ ከቻይና መበደር ይሆናል። ግን እስከመቼ? በዚያ ላይ ሁሌም አፋቸው ተከፍቶ የሚኖረው ሙሰኞቹ ባለስልጣናት ምን ያህሉን ወደ ህዝቡ ያደርሱታል የሚለው ጥያቄ ነው። ስለዚህ ዞሮ ዞሮ የማይመለስ አመጽ የማይቀርነው። መጽሐፉ እንዳለው የሰው ልጅ በረሃብ ከመሞት በጥይት መሞትን ይመርጣልና ለማይቀረው መዘጋጀት ይበጃል። ጥያቄው ከሪቮሉሽኑ በኋላ ምን ይፈጠራል? የሚለው ነው። ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ግን ወያኔ ወይም ጀሌዎቹ መልሶ ለመፈንቅለ መንግስት መዘጋጀታቸው የማይቀር መሆኑ ነው። ብልህ አንዴ ነውና የሚሸወደው ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ ሲወርዱ እንደሆነው እንዳይፈጠር ሁሉም መሳርያውን በመያዝ መጠባበቁ ነው የሚበጀው።
©ዐምደ ጽዮን