“ማይክል ዳቦን” ማን አጠፋው?

Standard

የ1977 ሀገር አቀፍ ድርቅ ተከትሎ የደርግ መንግስት ወደ ጣሊያን ሉዑካን በመላክ የዳቦ ማሽኖችን ከ20 ሚሊየን ብር በላይ እንዲገዛ ያደርጋል። ማሽኖቹ ሳር ቤት፣ ሚኒሊክና ራስ ደስታ ሆስፒታል ይተከላሉ። ማሽኖቹ ከተተከሉ በኋላ ከ600 በላይ ሰራተኞች እንዲቀጠሩ ይደረጋል።

በደርግ ባለስልጣናት የተተከለው የዳቦ ማሽን በአንድ ጊዜ ማሽን ውስጥ አስገብቶ የሚያስወጣው ዳቦ 6500 ያህል ነበር። ይህን ያህል ዳቦ ለማምረት የሚፈጀው ጊዜ ከግማሽ ሰዓት በታች ነበር። በወቅቱ የአዲስ አበባ ህዝብ ፍጥነቱንና መጣፈቱን በመመልከት “ማይክል ዳቦ” የሚል ስያሜ ሰጠው። ማይክል ዳቦ በከተማው ነዋሪ ይበልጥ ተወዳጅና ከመደበኛ የምግብ ማዕድ የማይጠፋ ሆነ።

እናም ህወኃት አዲስ አበባን ሲቆጣጠር ዓይኑ ካረፈባቸው ቦታዎች አንዱ ይህ የዳቦ ፋብሪካ ሆነ። በግማሽ ሰዓት ውስጥ 6500 ዳቦ የሚተፋ ማሽን ነቅሎ ለመውሰድ ቋመጠ። ፋብሪካው በ3ቱም ቅርንጫፎቹ ያጠራቀመውን ከ20 ሚሊየን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ለመውረስ እንቅልፍ አጣ። በሌላ በኩል ጉሮሮው እየተዘጋበት ያለው የአዲስ አበባ ህዝብ ባልጠበቀው ሁኔታ ተቃውሞውን እንዳያቀጣጥል ፍራቻ አደረበት። ህሊናው የቆሰለ ህዝብ ሆ! ብሎ ለመነሳት ትንሽ ነገር እንደሚበቃው ጠንቅቆ ያውቃሉ።

በመሆኑም ህወኃት የወሰደው እርምጃ ህዝቡ ቀስ እያለ “ማይክል ዳቦን” የሚረሳበትን ሁኔታ መፍጠር ነው። ለዚህ ውሳኔ እንዲረዳ ለዳቦ ፋብሪካዎች የሚቀርበው ዱቄት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ ተደረገ።

የሰራተኛው ሞራል የስራ ዋስትና እንዲቀንስ ወርሃዊ ደመወዙና ጥቅማ ጥቅሙ በከፍተኛ ሁኔታ ቀነሰ። በሂደት “ማይክል ዳቦ” ከገቢያው እየጠፋ ሄደ። ከአይን የራቀ ከልብ ይርቃል እንዲሉ የአዱገነት ነዋሪዎች “ማይክል ዳቦን” ወደ ትናንትና ትዝታቸው መውሰድ ጀመሩ። ይህን የተገነዘበው ህወኃት የዳቦ ፋብሪካውን ሰራተኞች ሙሉ በሙሉ አባረረ። ማሽኖቹን ደግሞ ከሳር ቤት፣ ሚኒሊክና ራስ ደስታ በመንቀል ወደ ትግራይ አጋዘ።…”

©ኤርሚያስ ለገሰ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.