​ለሥልጠና ወደ አድዋ የተወሰዱ የወልቃይት ዐማሮች በድብደባ ጉዳት ደረሰባቸው

Standard

የ10ኛ ክፍል ትምህርታቸውን የጨረሱ የወልቃይት ወጣቶችን አሰልጥኜ ሥራ አስይዛችኋለሁ በማለት ነበር ሕወሓት ወደ አድዋ የወሰዳቸው፡፡ ከወልቃይትና ጠገዴ አካባቢዎች ተመልምለው የተወሰዱ ወጣቶች አድዋ ሲደርሱ ግን የጠበቁትን ሥልጠና አላገኙም፡፡ አብረዋቸው በሚማሩ የትግራይ ተማሪዎችና አስተማሪዎች ‹‹ስለምን ዐማራ ነን አላችሁ፤ ትግሬ የተጠላው በእናንተ ምክንያት ነው!›› የሚል ወከባና ጥያቄ ይደርስባቸዋል፡፡ ከዚያ ወጣቶቹ ‹‹ታዲያ ምን ልንል ነው፤ እኛ እኮ ዐማራ ነን›› የሚል የማያወላዳ ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ ትናንት መጋቢት 5 ቀን 2009 ዓ.ም ለሥልጠና የሔዱት ሁሉም ወጣቶች ያለምንም ረዳት በሰው አገር የተደበደቡ ሲሆን ሐጂ የተባለ ወጣት ከፍተኛ የአከርካሪ ጉዳት ደርሶበታል ተብሏል፡፡ በድብደባው ጉዳት የደረሰባቸው ዐማሮች እስካሁን ምንም ዓይነት ሕክምና ካለማግኘታቸውም በተጨማሪ ወደ ወልቃይት እንዳይመለሱ ከፍተኛ ጥበቃ እየተደረገባቸው ነው ተብሏል፡፡ ወደ ወልቃይት ከተመለሱ ለበለጠ አደጋ እንደሚጋለጡና እንደሚታሰሩም ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡
©መሉቀን ተስፋው

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s