​እነሆ ትናንት አለፈ ዛሬ የባሰ ሆነ !!

Standard

የኢትዮጵያ ህዝብ ስለካንሰር ፣ ስኳር ፣ ደም ግፊት በሽታ ስጋት የሚያሳድርበት ረጅም እድሜ ድረስ አይኖርም ። በዚህም መሰረት የሌላው አለም  ህዝብ የሚያሳስቡት የእርጅና በሽታዎች ኢትዮጵያውያንን አያሳስቡንም። ኢትዮጵያ ውስጥ በእግዜር ፈቃድ በታጣቂ ጥይት ለጥቂት ብትተርፍ ፣ በእስርቤት በእሳት መጋየት ይጠብቅሃል ።ከእሳቱ ብታመልጥ በስደት ስትኳትን የውሃ እና የአሳ ነባሪ እራት ለመሆን ትጠባበቃለህ ። ከዛ በተአምር የተረፈው ህዝብ ከእነ ህይወቱ የቆሻሻ ተራራ ተንዶበት ይቀበራል ። ይሄን ሁሉ ችለህ ስትኖር ጥጋባቸውን መቆጣጠር ያቃታቸው የገዥው ብሄር ካድሬዎች ሞትህንና ስቃይህን መሳለቂያ ያደርጉታል ። የአንተ ስቃይ የእነሱ መዝናኛ  ኮሜዲ ጄነር ይሆናል ። ለእነሱ የህዝብ ስቃይ Horror Comedy  አይነት ፊልም እንደ መመልከት ነው። ባለፈው አንዱ የገዥው ብሄር ሰው “የአዲስ አበባ ህዝብ እንደ መቀሌ ህዝብ ቆሻሻውን ቢሰበስብ ኖሮ አይሞትም ነበር ” ብሎ ተሳለቀ  ።የእሱን መሳለቅ ተከትሎ አንዱ የበገነ ሰው (Hamid ) …” መቀሌ በኢትዮጵያውያን ደም የታነፀች የግፍ ከተማ ናት፡፡ ቀን ጽዱ ልትሆን ትችላለች ሌሊት ግን የዱካኮች መናኸሪያ ነች፡፡ሴጣን የሚፈነጭባት ደም የጠጣች ከተማ ።” ብሎ መለሰለት ። እውነቱን ነው ። ኢትዮጵያ ውስጥ ሰው ሰራሽ ሞት ለማምለጥ ከፈለግህ ወደ ትግራይ በስደት መሄድ ይኖርብሃል።አውሮፓ ሂትለርን አፈራች ኢትዮጵያ መለስ ዜናዊን ሰጠችን ። ለሺህ አመታት ነፃነቷን ጠብቃ የቆመች አገር በ25 አመታት ውስጥ መቃብሯን እየቆፈረች ራሷን ወደ እንጦሮጦስ እያወረደች ነው። በዚህ ከቀጠልን ኢትዮጵያ የምትባል እውነት አገር አትኖረንም ።የኢትዮጵያ ችግሮች ዘርፈ ብዙ ነው ። የባሰው ግን ዘር መድሎ ፣የኢኮኖሚ ፣ የስግብግብነትና የራስ ወዳድነት ነው።  አንድ በዘረኝነት አስተሳሰብ የተጠመደ ፣በተሳሳተ አቅጣጫ የተመራ ህዝብ ሀገር መጨረሻው እንደት አስፈሪ ሊሆን እንደሚችል መገንዘብ ይቻላል።የኢትዮጵያ ህዝብ ለ 25 አመታት አያሌ የፍትህ መጓደል ቢያጋጥመውም በመሰረቱ እስካሁን ትሁት ነው ፣ ጨዋ ነው። ብዙ ጊዜ ስልጣን አይጋፋም። አለቃ ወይም መሪ ሆኖ ለሚመጣበት ሁሉ በሚያስገረም ፈቃደኝነት ይታዘዛል። እህሉ ቢወደድበት ፣ልጆቹ ቢሞቱበት ፣ መሪዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ቢበድሉት እኛ ኢትዮጵያውያን ያለ አንዳች ተቃውሞና አቤቱታ ኑሯችንን እንቀጥላለን ። ወያኔ ሆን ብሎ በለኮሰው እሳት ብንተርፍም ምንም እንዳልተፈጠረ ለደቂቃዎች ተንጫጭተን እንረሳዋለን ። ቀጣዩን ትራጄዲ እንጠብቃለን  ። በሚያምን በሚያስቸግር ሁኔታ ሁላችንም ምንም እንዳልተፈጠረ ወደ ተለመደው አሰቃቂ ኑሯችን እንመለሳለን ። የጨቋኝ ተጨቋኝ ድራማው ይቀጥላል::ዛሬ በአበኢትዮጵያ ነፃ ምርጫ ህልም ነው። በቢሊዮን የሚቆጠር ዘረፋ ደንታ አይሰጠንም ።መሪ የሚቀየረው ሲሞት ወይም በመፈንቅለ መንግስት ነው። የአገሪቱ ኢኮኖሚ ተንኮታኩቶ መሰረታዊ የሆኑት ዳቦና እንጀራ ጠፍቶ ጥቂቶች በምቾት ይሰቃያሉ። በ IQ ምጣኔ ” ደደብ”  ነው ማለት የሚቻለውና ቀልዱ እንጨት እንጨት የሚለው የአገሪቱ ጠቅላይ ሚ/ር  “50 ቢሊዮን ብር ከሰርን ! ፣ የኮንዶሚኒየም ህንፃዎች ጠፉብን ፣ 100 ሚሊዮን የካሳ ብር ባለስልጣኖች ተከፋፈሉት! ” እያለ ሲናገር እንደ ጅል እየገለፈጠ ነው ። መርፌ እንደጠፋው ህፃን እንኳን ድንግጥ አይልም ። ሰሞኑን ፎርብስ መፅሄት አገሪቱ በእርዳታ ያገኘችውን 30 ቢሊዮን ዶላር ተመልሶ በባለስልጣናት ወደ ውጭ ወጥቶ የሸሸባት አገር ነች ።እኛ ኢትዮጵያውያን ስለወያኔ ዘረኛ  አገዛዝ ብንሾካሾክም አገሪቱን ያጥለቀለቀው የጆሮ ጠቢዎች መንጋ በመፍራት በግልፅ አንናገርም ። ደፍረው ለመናገር የሞከሩት ከጥይት የተረፉት ቤታቸው ከርቸሌ ሆኗል ።  ዛሬ በኢትዮጵያ ከትናንት የባሰ ነው ። ጠንከር ብለን ለውጥ እንድመጣ ካላደረግን  ነገ ደሞ ታዋቂው ፈላስፋ ማክስ ዌበር እንዳለው በብረት አጥር ውስጥ ታጥሮ እንደሚኖር አራዊት ነን።

“The future is an Iron cage “

by (ቬሮኒካ መላኩ)

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s