ሰላማዊ ትግሉ

Standard

“ከኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ጋር አስር ጊዜ ተገናኝቻለው፥ ኢንፎርማሊ ፥ ተው ኢትዮጵያን አታውቋትም ብዬው ነበር” ። ይህን ንግግር በሸራተን በተካሄደው የታዋቂ ፓለቲከኞች ፣ መሪዎች ፣ እስፓርተኞች ፣ ባላሃብቶች እና ሃይሌ ገብረስላሴን የመሳሠሉ የወያኔ አሸርጋጆች በተገኙበት አቦይ ስብሃት በውስኪ ሞቅታ ያወሯት ትልቅ ምስጥር ናት። የኢትዮጵያ ፓለቲካ ከትላንት ዛሬ ይሻላል ብንል ፥ በባሰ መልኩ ፓርቲ አፍራሾችና ድብቅ እጀንዳ ባላቸው የፓለቲካ ፓርቲ መሪዎች እኩይ ሴራ ምክንያት ህዝባዊ ትግሉ ወደ ውድቀቱ እያመራ ነው። (የዚህ ፅሁፍ ባለቤት ለደህንነቱ ሲል ይህን ፅሁፍ የፃፈው በፌክ አካውንት መሆኑ ይታወቅ)

1. ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት

ይህ ሰው በብዙሃኑ የአገራችንን ፓለቲካን የሚያውቁ ሰዎች የሚያውቁት እነ ፕሮሬሠር መስፍን ወልደማርያምን ጨምሮ አሁን ፓርቲውን በህጋዊ መልኩ በነ ይልቃል ረቂቅ ይሁንታ በመሪነት የያዙትን እነ የሺዋስ አሰፋን እንዲሁም አሁንም በጓዳዊ ስሜት አብረውት ያሉትን አቶ ስለሺ ፈይሣና፣ ከአየር መንገድ ስራቸው የተፈናቀሉትን አቶ ወሮታው ዋሤን በማስተባበር ከአንድነት ፓርቲ “መርህ ይከበር” በሚል እውነተኛ በሚመስል ሌላ ዓላማ ባነገበ ጥያቄ አንድነት ፓርቲን በማፍረሡ ነው። ይህ ድብቅ አጀንዳውን ከጊዜም በኃላ በተረዱት ባያስብልም በጠረጠሩት ፕሮፌሠር መስፍን ወልደማርያምን ፣ ዶ/ር ያዕቆብ ሃይለማርያም ፣ የሺዋስ አሠፋ ፣ ዳንኤል ሽበሺና ሌሎች ትላልቅና አንቱ የተባሉ ፓለቲከኞች ጥርስ የገባው ይሄኔ ነበር። የደብረወርቅ ህንፃን በሼር ባለቤትነት ከእጁ ያስገባው ይኼው ግለሠብ” በፓርቲ ፓለቲካ ህዝቡ ተስፋ ቆርጧል ! አሁን ሥርዓታችንና ያለን የመንግሥትነት ይዞታ እስትንፋሥ ዘርቶ ሊቆይ የሚችለው ሰማያዊ ፓርቲን በጎን ለሌላ ወገን አሥተላልፈን እኛ ተገፊ ሆነንና ህዝባዊ ካባ ደርበን ወደ ህዝቡ ሠርገን በድብቅ ያሉ ሴሎችን መበጣጠስ ሥንችል ነው” በሚል መርህ ላይ ተስማምቶ የህዝብን ህዝባዊ ትግልና መሪዎቹን በድብቅ እንዲያገኟቸው በማመቻቸትና አድኖ በማስያዝ ትግሉ ስርዓት ይዞ እንዳይቀጥል በቅርቡም እንዳይመለስ አድርጎ ለመቅበር ነው። ይህን ረቂቅ ተግባር ሰማያዊ ባህር ዳር ላይ በተጠራው ሠልፍ በድብቅ ከወልቃይት ኮሚቴዎች ጋር ይደረግ የነበረው የውሥጥ ለውስጥ ስራ አንዱና ዋነኛው ዓላማ ነበር! (ባይሣካም)። ይልቃል ጌትነትም ፓርቲዬ ተቀማ በማለት ህዝባዊ ተቀባይነት ለማግኘት እያደረገ ያለው ለዛ ነው። በጠቅላላ ጉባኤው ተወዳጅነት እያለው፣ ቢሄድ እንደሚመረጥ እያወቀ ለምን ቀረ?!!! መልሱ ቀላል ነው። ትንሽ ማሰላሰል ነው የሚጠይቀው ባይ ነኝ ::

2. ወ/ሮ ምዕራፍ ይመር

ይች ሴት የህወሃቱ ሠላይና በአሁኑ ወቅት የአረና ፕሬዝዳንት አይተ አብርሃ ደስታ ድብቅ እጮኛ ናት። በድሮ ሥራዎ በቴሌ ውሥጥ የሠዎችን መረጃ መቀምር ነበር። አብርሃ ደስታ ማእከላዊ እያለ እየተመላለሰች ትጠይቀውና መረጃ ታቀብለው ነበር። እሱም ውስጥ ስላለው ጉዳይ ያወራት ነበር። ይህ የሚሆነው የማዕከላዊ ታች ያሉት ሰዎች እንኳን እንዳይጠረጥሩ ነው። ምክንያቱ አብርሃ ከሌሌች እስረኛ በተለዩና ከማዕከላዊ ውጭ ባሉ ደህንነቶችና ግለሠቦች ከተጎበኘ ጥርጣሬ እንዳይፈጥር በሚል። ወ/ሪት ምዕራፍ ይመር ትግሬ ብትሆንም መታወቂዋ ላይ አማራ በሚል የምትንቀሳቀስ ሰላይ ናት። ከትላልቅ ሰላዮች ጋር እህቷ ቤት በሚደረጉ ስብሰባዎች ትዕዛዝ በመያዝ ከነ ይልቃል ጌትነት ፣ አዲሱ ጌታነህ እና ይድነቃቸው አዲስ ጋር ትመክርበታለች።

3. አቶ ይድነቃቸው አዲስ

የ2007ን ምርጫ ተከትሎ ፓርቲውን የተደባለቈው ይኸው ግለሠብ ገና የሀዋሣ የዩነቨርሥቲ ተማሪ እያለ በሰላይነት ተመልሞሎ በብጣሽ ወረቀት ወደ አዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ ተቀይሮ ድግሪውን በኢኮኖሚክስ ከአ.አ ያገኘ ሩህሩህ መሣይ አውሬ ነው። ይልቃል ወደ ስራ አስፈፃሚነት ሊያመጣውና የወጣቶች ጉዳይ ሃላፊ ሊያደርገው የነበረ የሠማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት አባል ነበር። ይህን ሃላፊነት ይዞ ወደ ግንቦት ሠባት የሚሄዱ ሠዎችን መመልመልና በጎን ማስጠልፍ ዓላም ያነገበ ተልዕኮ እንዲኖረው ነበር የታለመው። መንግስት ISISን ለማውገዝ በጠራው ሠልፍ ላይ በማያውቁትና እታች ባሉ የደህንነት ሠዎች ከሰማያዊ ፓርቲ የጥናትና ስትራቴጂ ክፍል ሃላፊው ጋር ተይዞ፥ እነ ብሌን መሥፍን ፣ ናትናኤል ያለምዘውድ (ያልተለቀቀ) ፣ ምሥኪኗ ወይንሸት ሞላ ፣ አርበኞች ግንቦት ሠባትን የተቀላቀለችው ሜሮን ፣ ንግስት ወንድይራድ ፣ ማቲያስ መኩሪያ ፣ተዋቸው ዳምጤ ፣ ቴዎድሮስ አሥፋው ፣ ኤርሚያስ ፣ ዳንኤል ፣ ፍሬው እና ሌሎችም በወራቶች ታስረው ሲለቀቁ ፣ እሡ ባስተባበረበት ሠልፍ ላይ እታች ባሉ ደህነቶች ቢያዝም ማታ ሲመሻሽ እቤቱ ድረስ በቶዮታ ኮሮላ ተሸኝቷል። አብሮት የነበረው ከአ.አ ዩኒቨርስቲ የማስተርስ ምሩቁና የUN ሠራተኛ የነበረው እስክንድር ጥላሁንን ለማስቀረትና ለማሠር ቢፈለግም ይድነቃቸውን ፈቶ እስክንድርን ማስቀረት ጥርጣሬን ይፈጥራል በማለት ወዲያው አብሮት ተፈቷል። ካልታመንኩ ISIS ን ለማውገዝ በተጠራው ሠልፍ ላይ የተያዙ ሠዎች ዜና ሲሠራ አብሮ ስም ዝርዝሩ በኢሳትም ሆነ በተለያዩ ድህረ ገፃች እንዲሁም ሣተላይት ሬዲዮኖች ላይ መሠራቱ ትዝ ይለናል።ቆራጦቹን የሠማያዊ ልጆች ዮናታን ተስፋዬ፣ እያሥፔድ ተሥፋዬና፣ ዮናሥ ከድር እንዲባረሩ አባላቶችን ሠብስቦ በምክር ቤት ክሥ እንዲመሠረት አሥተባብረል። ሌላው ሠኔ መጨረሻ 2008 ላይ ባህር ዳር ሄደው ሲታሠሩ ዓላማው የገባቸው የአሁኖቹ የሠማያዊ እውነተኛአመራሮች የተቃወሙት እውነቱ ገብቷቸው ይመስለኛል። እዛ ድረስ ሄደውና ታስረው እውነተኛ ታጋዮች ቢሆኑ በዋስ ይፈቱ ነበር ወይ የሚለውን አንባቢ ይመልሠው። ይኽው ግለሠብ ከዚህ ዕኩይ ድርጊቱ ሣይቆጠብ በባህዳር ከሠማያዊ ፓርቲ እውቅና ውጭ በጥቂቶች የማፍያ ሥራ ጥቂቶችን አሣምነው ህዝብ በጅምላ ለማስፈጀትና የወልቃይት ኮሚቴዎችን ማንነት በድብቅ በድጋሚ ለማወቅ ህገ ወጥ ሠልፍ በነሃሤ 1/2008 ዓ.ም የጠሩ ጊዜም ሄዶ ሠልፍ እንዲጠራ ስለሺ ፈይሣ ጋር ሄዶ ፈርሟል ፣ ሥለሺንም አሥፈርሟል። በማግሥቱም ከ200 ሠው በላይ በአጋዚያን በዚሁ እነሡ በጠሩትና ፣ በፈጠሩት ሃሣብ ሊሞት ችሏል። ሠልፉ እንዲጠራ በእነርሡ ቀጭን ትዕዛዝ ሲያስተባብር የነበረው አቶ ማሩ በአሁን ሠዓት ታስሮ ባህር ዳር ባለ እስር ቤት እየተሠቃየ ነው። ሌላው አሥተባባሪ የነበረው አቶ መልክይሁን ተይዞ ታስሯል ( አሁን የት እንዳለ እንኳን አይታወቅም! ) ። ሌሎችም አባሎች ባህር ዳርን ለቀው ተሰደዋል። በወቅቱ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር የነበሩት ቆራጡ ታጋይ አቶ ነገሠ ተፈረደኝ በቅርቡ ከእብሥተ መና ካፌ የመያዛቸው ምክንያት ከዚሁ ግልሠብ እየተቀበሉ በ #Voa እና ሌሎች የመገናኛ አውታሮች ላይ ይናገሩ ስለነበር ነው። በአሁን ሠዓት እኝህ ቆራጥ ታጋይ የት እንዳሉ እንኳን ማወቅ አልተቻለም።በዚኹ ጉዳይ ላይ ስለሺ ፈይሣን ይዞ ይድነቃቸውን መተው ጥርጣሬን ይፈጥራል በመባሉ እንዳይያዝ ተደርጓል። በምርጫ 2007 ላይ ፓርቲውን ወክሎ በቴሌቭዥን በሚተላለፈው ምርጫ ክርክር በውጭ ጉዳይ ላይ ክርክር እንዲያደረግ በወቅቱ በነበረው ደልዳይ ኮሚቴ ቢመረጥም ፣ በሥመጨረሻ ከደህንነት መስሪያ ቤት በደረሣቸው ቀጭን መልዕክት ይልቃል ጌትነት እንዲሄድ ሆኗል። ይኽው አውሬ በትግል ስም የቀሩትን ቆራጥ ታጋዮች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስለቀምና ለማሥጨረሥ ከጠበቃው አዲሱ ጌታነህ ጋር በመሆን አዲስ ፕሮጀክት ጀምረዋል።

4. አቶ አዲሱ ጌታነህ

የይልቃል ሰማያዊ ፓርቲ የህግ ጉዳይ ሃላፊ የነበረው አዲሱ ጌታነህ ድግሪውን በህግ ከባህር ዳር ዩንቨርስቲ ያገኘ ሲሆን በቆይታውም በዩንቨርስቲው ውስጥ በነበረው የብአዴን ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ ላይ የጎላ አስተዋፅኦ የነበረው ግለሠብ ነው።ከተራ የብአዴን አባልነት ከተማ ቁጭ ብሎ ዲፕሎማቶችንና በውጭ አገር ያሉ እንቅስቃሴዎችን ሲያስፈልግ እዛው ድረሥ በመሄድ ወዳጅ መስሎ በሚሰልለውና በቤተሠብ ጋብቻ በተዛመደው ኢንጅነር ይልቃል ተመልምሎ ወደ አዲስ አበባ የገባው በ 2008 ዓ.ም ነው። አዲሱ ጌታነህ በቅርቡ ከአራት ወራት የማዕከላዊ የእስር ቆይታና የስለላ ስልጠና በኃላ መሣሪያ በማንገብ የእሳት እራት ለማድረግ ካሠቧቸው ከነ ስልሺ ፈይሣና ሎሎች የሰማያዊ ወጣቶች ጋር ቢሮ ድረስ በመሄድ እነ የሺዋስ አሠፋን በሠደፍ ደብድቧል። በዚሁ እውነተኛ የሠማያዊ ፓርቲ አመራሮችን በመደበደብ ተልእኮ የአሁኑ የፓርቲው ሊቀመንበር የሺዋሥ አሠፋ፣ የፅፈት ቤት ሃላፊው ዕንደሻው ዕመሻው ፣ የጥናትና ሥትራቴጂ ሃላፊ የነበረው ኢነጅነር ጌታነህ ባልቻ ፣ ኢነጅነር ስሜነህና አቶ ብስራት ጥቂቶቹ ናቸው። ማዕከላዊ እያለ እነ ስንታየሁ ቸኮልን ጨምሮ ሌሎች ታጋዮችን ሲሠልል ሰንብቷል። እሱን ከአራት ወራት ቆይታ በኃላ ለቆ ስንታየሁ ቸኮልን ወደ ቂሊንጦ መላክ ያስጠረጥረዋል በማለት ስንታይሁ ቸኮልም ከማዕከላዊ እንዲወጣ ተደርጓል።ከዚህ በፊት ከአራት ወር የማዕከላዊ ቆይታ በኃላ ማን ተፈቶ ነበር ካላችሁ ☞ ስለሺ ሓጎስ ..። እነ ዶ/ር መራረ ጉዲና ፣ አቶ በቀለ ገርባ እና ሌሎችም አንጋፋ ፓለቲከኞች ሲታሠሩ የደብረወርቁና የብርሸለቆው ድብልቅ ተኩላ ይልቃል እንደዛ እየወረደባቸው የማይታሠረው ለምንድነው ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል። ከአራት ወር የማዕከላዊ ቆይታ በኃላ አዲሡና መሣዮቹ ሲፈቱ ሌላው ለስቃይ ለምን ወደ ቅሊንጦ ፣ ዝዋይ ፣ ቃሊቲና ሸዋሮቢት ለምን ይላካል ብሎ መጠይቅ ያስፈልጋል።መልሱ ☞ ☞ ☞ ☞ የድብቁና በጌታቸው አሰፋ የሚመራው የከፍተኛው የወያኔ የስለላ ማህበር አባል ስለሆኑ ነው። እንግዲህ አነፍናፊዎቹ ደርስውብኝ ካልገደሉኝ አልያም ካላሣሠሩኝ በቀጣይ በማስረጃ እመለሣለው። ይህ ሁሉ ሲሆን ካጠገባቸው ምን እየተከናወነ እንኳን የማያውቁትና አምነዋቸው አብረዋቸው በጓዳዊ ስሜት እስከ ቀራኒዮ ብለው የማሉትንስለሺ ፈይሣን ፣ ወሮታው ዋሤን ፣ ወ/ሮ መዓዛ መሀመድን ፣ ቅን ሓሣቢው እስክንድር ጥላሁንን ፣ ትንሹና እውነተኞች መስለውት ካገኘው ጋር አምባ ጓሮ ከሚፈጥረው ቆራጡ ታጋይ ስለሺ ደቻሣን፣ ቴዎድሮሥ ፣ ጠና ይታየው ፣ አወቀ ተዘራ ፣ እና በየጊዜው ከስራቸው ስለማትጠፋ የእፎይታ ጊዜ እናግኝ እያሉ በደህንነት ትዕዛዝ የሚያሣስሯትን ወይንሸት ሞላንና እንዲሁም ለመጥቀስ ብዙ የሆኑ ቆራጥ የሆኑ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት አባላትን አሁንም ቢሆን ከጎናቸው በማሠለፍ ነው። ወገኖቼ እባካችሁ እራሳችሁን ከነዚህ አውሬ ጠበቁ!

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.