የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ የትጥቅ ትግሉን በማስፋፋት ላይ መሆኑ ተገለጸ

Image

የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቱ የተከበረበት የኢኮኖሚ  ብልፅግናና ማኅባራዊ ፍትህ የሚያገኙበት የዜጎች ህይወት ደህንነትና ጥቅም የተከበረበት ሃገር እንዲኖረው ለማድረግ የሚታገለው ድርጅቱ ይህንን በወገኖቻችን ላይ  ሚደርሰውን ግፍና በደል ለመስቆም የተጀመረውን ትግል በተለያዩ የሃገሪቱ  ክፍል ላይ የትጥቅ ትግሉን መሰረት በመጣል በማስፋፋት ላይ
መሆኑ ተገልጻል።
በመላው ኢትዮጵያ ከተጀመረው ትግል አካል የሆነው በሰሜኑ  የሀገሪቷ ክፍል በተለያዩ ቦታዎች በተደረጉ ማጥቃቶች ድል  የቀናው የአርበኞች ግንቦት 7 ሠራዊት አሁንም የተጀመረውን  የትጥቅ ትግል በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በማስፋፋት ላይ  መሆኑን የድርጅቱ ድምጽ የሆነው የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ  ሬድዮ ገልጿል። የተጀመረው የትጥቅ ትግል በተለያዩ ከተሞች ማለትም  በጎንደር ፡ በጎጃም እንድሁም በወሎ ሲሆን ትክክለኛ መሰረት  ላይ ቆሞ በተደራጀና ሚስጥርነቱ በተጠበቀ አኳሃን  በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑ ድርጅቱ አክሎ ገልጿል።ይህንንም ተከትሎ በአማራ ክልል የህወአት ጉዳይ አስፈጻሚ  ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩ ብዛት ያላቸው የብአዴን አባላት  በተለያዩ መስሪያ ቤቶች የሚሰሩ ወደ ህሊናቸው በመመለስ  የተጀመረውን የትጥቅ ትግል አጋርነታቸውን በማሳየት ላይ ሲሆኑ  ይህን ተከትሎ በአማራ ክልል ህውአት አጣብቂኝ ውስጥ  ገብቷል።ከምን ግዜም በላይ ህወአት በአማራ ክልል መውደቂያው  መድረሱን አመልካች መሆኑን የተለያዩ የፖለቲካ ተንታኞች  በመግለጽ ላይ ናቸው።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.