​በዘመናችን ዲያብሎሶች እጅ ተይዞ ከሞት የተረፈ 

Standard

የጀግንነት መስፈርትን የምታሟላ የሃገር ኩራት ። ሰው አክባሪ። ለሃቅ አንገቱን የሚሰጥ። ለቆመለት አላማ ግቡን ሳይመታ የማይተኛ ለመምራት ብቃት ያለው።  የኢትዮጵያን ህዝብ ከባርነት ቀምበር ለማውጣት ሌት ተቀን ቀና ደፋ ሲል በዘመናችን ዲያብሎሶች እጅ ተይዞ ከሞት የተረፈ ። በወጣትነት እድሜው ለሀገር ስለሀገር ተሟጋች። “እመነኝ” ብሎ ሲናገር የሚታመን ። ጥሩ አባት እና ጥሩ ባል ሆኖ ቤተሰቡን የሚያስተዳድር ። የአሁኑ ዘመን ወጣት እንደ አርአያ ሊከተለው የሚገባው ቢከተለውም የሚኮራበት ። ይህን አይነት የኢትዮጵያውያን ኩራት የሆነ ወጣት ወያኔዎች በእስር ቤት ያደረሱበትን ኢሰብአዊ እንግልት ከእራሱ አንደበት ከሰማሁ በኋላ እንቅልፍ ነሳኝ ። ሀብታሙ አያሌው በአሁኑ ሰአት በወያኔ እጅ አይገኝም ነገር ግን   የእሱን አይነት ስቃይ የተቀበሉ እና እየተቀበሉ ያሉ ወጣቶች ስንት ናቸው። የሃብታሙ አያሌው ስቃይ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ስቃይ መሆን ይገባዋል ። ወያኔ ይህን አይነት ጦርነት ያወጀው በጥቂት ግለሰቦች ላይ ብቻ ሳይሆን ለመላው ኢትዮጵያዊያን ስለሆነ ማንኛውም ሰው ይህን አረመኔያዊ የዲያቢሎስ መንግስት በአስችኳይ ከስሩ ፈንቅለን መጣል የዜግነት ግዴታችን ነው።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s