በቤንሻንጉል ለተሰናበቱ ወታደሮች ጥሪ ቀርባል

Standard

በቤንሻንጉል ጉሙዝ በአሶሳ ከተማ በ7 ዓመት ወይም በ10 ዓመት አገልግሎት ከሰራዊቱ በክብር የተሰናበቱ የቀድሞ ወታደሮች ለሰላም ማስከበር ግዳጅና ለብሄራዊ ተጠባባቂ ሃይል እንዲመዘገቡ የሚጠይቁ ማስታወቂያዎች ተለጥፈዋል። እድሜው ከ42 ዓመት በታች የሆነ ወይም የሆነች፣ በተለያዩ አግባብ ከሰራዊቱ የተሰናበተ፣ በ7 ወይም 10 ዓመት አግልግሎት ጨርሶ በክብር የተሰናበተ፣ በጸረ ሰላም ሃይሎች እንቅስቃሴ ያልተሳተፈና ያልወገነ እንዲሁም በሰላም ማስከበር ተሰማርቶ ግዳጅ መጸፈም የሚያስችል ጤንነትና አካላዊ ብቃት ያለው በየቀበሌዎች እየሄደ መመዝገብ እንደሚችል በማስታወቂያው ላይ ተመልክቷል። የቀድሞ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን መልሶ ለመቅጠር የተፈለገው፣ ባለፉት 2 ዓመታት አዳዲስ ምልምል የመከላከያ አባላትን ለመቅጠር የተደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ በመክሸፉ እንዲሁም በአገሪቱ የሚታየው የጸጥታ ችግር አድማሱን እያሰፋ በመምጣቱ መሆኑን ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ሰዎች ይናገራሉ። በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የሚታየውን የሃይል ትግል ለማስቆም ተደጋጋሚ ሙከራ ቢደረግም፣ ሙከራው ውጤት አላመጣም። በህዝቡ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በመቃወም እንዲሁም በዘረኝነትና ተስፋ በማጣት በርካታ የሚከላከያ ሰራዊት አባላት በየጊዜው ይጠፋሉ።

Advertisements

የቴላቪቭ ወጣት ከክሱ በነፃ ተሰናበተ

Standard

እስራኤል በቴላቪቭ ከተማ የሚገኘው የወያኔ ኢምባሲ በር ላይ ሲውለበለብ የነበረውን ባለኮከቡን ባንዲራ አውርዶ በንፁህ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ የተካው ወንድማችን ፍርድቤት ተከሶ ቀርቦ ነበር ነፃ ቢለቀቅም ከተደረደረበት 6 እና 7 የሀሰት ክሶች ውስጥ አንደኛው አምባሰደሩን እገድልሀለው ብሏል የሚል ነው  ልጁ ተከፍሎት ነው፣ከጀርባው ሀይሎች አሉ፣ ግ7 የሚባል አሸባሪ ድርጂት አለ አገርቤትም ሆነ በየትኛውም ቦታ ሴሎች አሏቸው፣ እዚህም እስራኤልም አሏቸው፣ ይሄ ልጅም ከነሱ ጋር ይሰራል የሚል ነበር! ስለ አግ7 በእስራኤል ፍርድቤት ችሎት ላይ ስሙ እንዲጠራ እና እንዲተዋወቅ ስላደረጉት አምባሰደሩ ምስጋና ይገባቸዋል! የሚገርመው እስራኤልን አለማወቃቸው ነው! በሽብር ጥቃት ከሚሰቃዩ አገሮች አንዷ እስራኤል ናት! ሽብር እና ሽብርተኛ ማን እና ምንአይነት እንደሆነ አብጠርጥራ ታውቃለች! አንድን ምስኪን ወገን በሽብርተኛ መፈረጅ እነሱን እራሱ ያስጠይቃል! ዝም ብሎ የሰው ስም ማጥፋት ዋጋ ያስከፍላል! አገር ቤት ወጣቱን፣ ተማሪውን፣ አስተማሪውን፣ የሀይማኖት መሪወችን፣ ጋዜጠኛውን እንደው ሳር ቅጠሉን ሁሉ አሸባሪ እያሉ እንደሚያሸማቅቁ እና ከርቸሌ አስገብተው በነፍስና በስጋቸው እንደሚጫወቱባቸው ሁሉ እዚህም የሚደረግ መሰላቸው!?!የሆነው ሆኖ በቀረበበት የሀሰት ክሶች በሁሉም ነፃ በመሆኑ በተያዘ 12 ሰአት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ፍርድ ቤት ቀርቦ ጉዳዩ ከታዬ በኋላ በነፃ ተለቋል!ይሄ ድርጊት የተፈፀመው አገር ቤት ሆኖ ቢሆን ኖሮ በዚህ ወንድም ላይ ምን ሊደርስ እንደሚችል ግልፅ ነው! በአንድ በኩል ጭካኒያቸውን፣ ክፋታቸውን፣ ተንኮላቸውን እና ውሼታቸውን ለፍርድቤቱ ምን አይነት ሰወች እንደሆኑ በግልፅ አሳይተውልናል!አግ7 እንኳን ተግባራችሁ ስማችሁ ብቻ ወያኔወችን በቁም የሚያቃዥ መሆኑን በተረዳን ጊዜ ነፍሳችን ሀሴት አደረገች! በርቱ!

በ Hirut Hailu

​በባሕር ዳር ከ300 በላይ ቤቶች ፈርሰው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተበትነዋል

Standard

ከመጋቢት 12 እስከ 14 ቀን 2009 ዓ.ም በወታደሮች በታገዘ የቤት አፍራሽ ግብረ ኃይል በባሕር ዳር በተለምዶ ይባብ በሚባለው አካባቢ ከ300 በላይ ቤቶች ፈርሰው ከአንድ ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች ያለመጠለያ ቀርተዋል፡፡ማክሰኞ መጋቢት 12 ቀን እንደተጀመረ የሚናገሩት የዐይን እማኞች እስካሁን ድረስ 300 የሚሆኑ ቤቶች እንደፈረሱና ሌሎች ወደ 1000 የሚጠጉ ተጨማሪ ቤቶች ሊፈርሱ የ‹X›ምልክት በቀይ ቀለም ተደርጎባቸዋል ብለዋል፡፡ከበሌ 14 ነኝ የሚል አንድ እማኝ እንደገለጸልን ከሆነ ወላጆቹ ታስረው ብቻውን ቤት በሚፈርስበት ወቅት ከውስጥ መኖሩ ያልታወቀ አንድ ሕጻን ሕይወት ማለፉን የገለጸ ቢሆንም ከሌላ ገለልተኛ ወገን ወይም ግለሰብ እስካሁን ማረጋገጥ አልቻልንም፡፡ቤታችን ለምን ይፈርሳል ብለው የተቃወሙ ባለቤቶች በብዛት የተደበደቡ ሲሆን ከ50 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ታስረዋል ተብሏል፡፡ ከታሰሩት መካከል በአካባቢው ባለው የቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያ አገልጋይ ካሕናት የሚገኙ ሲሆን ጥቂቶቹ ትናንት ተፈተዋል ብለዋል፡፡ በባሕር ዳር ፈለገ ሕይወት ሆስፒታል እና በጤና ጣቢያዎች በርካታ በድብደባ ብዛት ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች እንደሚገኙም ለማረጋገጥ ችለናል፡፡

በ ሙሉቀን ተስፋው

የሳምራዊት ክህደት

Standard

እንዴት አንድ ግለሰብ ድርጅትን ካደ ተብሎ እንዲህ ገኖ እንደመሚወራ አይገባኝም ። ከድርጅት አልፎ ሀገርንስ ሲከዱ አላየነም ወይ ?!! ለእኔ የሚደንቀኝ ነገር ግን ሳምራዊትን ከዚህ በፊት ስሟን እንኳን ሰምቶት የማያውቀው ሁሉ ግንቦት ሰባትን እሷን ተመርኩዘው ለማዳከም በሻገተ ሀሳባቸው ሲንደፋደፉ ማየቴ ነው ። ለእኔ እስከገባኝ ደግሞ ግንቦት ሰባት የተሻለ ደረጃ ላይ መሆኑንና ወያኔም በመንቀጥቀጥ ፍራቻውን እየገለፀ ያለበትን ሁኔታ እየተመለከትኩኝ ነው ። ከወያኔ ወደ ነፃነት ሃይሎች በየጊዜው የሚቀላቀሉትን በመቶ የሚቆጠሩ የተለያዩ አካላትን ባልሰማ እያለፈ ስለ እነሱ ምንም ያልተነፈሰው ተቃዋሚ ነኝ ባይ አሁን ከአመታት አንዴ በጥቅም የተደለለን አቋም የለሽ ለአንዲት አስመሳይ ግለሰብ ቦታ ሰጥቶ ወሬ በማሞቅ የግንቦት ሰባትን የደህንነት ክፍል የተቀዛቀዘና ክፍት አድርጎ ለማሳየት መሞከር ውሃ የማይቋጥር ወሬ ነው ! የሳምራዊት አይነት ክህደትና ሽሽት ለወደፊቱም ሊከሰት ይችላል ! ድርጅቱ ትግሉን አጠናክሮ ሲቀጥል ወያኔ አንድ ግለሰብ ለማስካድና የድርጅቱን ተአማኒነት ለማሳጣት የማይፈነቅለው ድንጋይ እንደማይኖር የታወቀ ሀቅ ነው ። ይሀ የሊኮፍተር አብራሪ ወደ ነፃነት ሃይሎች ለምሳሌ ከተቀላቀሉት አንዱ ነው ማን ነበር ስሙ ? 

ድል ለጭቁኑ ህዝብ !

ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

Standard

 የስልጣን ዕድሜን ከማራዘምና ከማራዘም ባለፈ ምንም አይነት ህልም የሌላቸው የወያኔው ቡድን ባለስልጣናት የህዝብና የሃገርን ጥቅም ከቶ አይታሰብም።   የህዝቡ የኑሮ መሻሻልና የመልካም አስተዳደር ባለቤትነት አስጨንቋቸው አያውቅም።  የሃገር ሉዓላዊነት፣ የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊመብቶች መከበር ወዘተ ለደቂቃም ቢሆን አሳስቧቸው  አያውቅም። ስልጣናችንን ይጋፋናል ወይም ይነጥቀናል ብለው የሚሰጉት ማናቸውም በተናጥልም ሆነ በግል የሚደረጉ የህዝባዊ ወገንተኝነት እንቅስቃሴዎች ሁሉ ለማዳፈን  የማይቆፍሩት ጉድጓድ የለም። ይገድላሉ፣ያስራሉ፣ለመግለጽ በሚያስቸግር መልኩ ይደበድባሉ፣ያስፈራራሉ …    በአጠቃላይ አገዛዙ ከህዝብ ጋር የማያቆራርጠውና በስልጣን እንዲቀጥል የሚያስችል ቅንጣት ታክል የሞራል ልዕልና የለውም። በተስፋ መቁረጥ ተዘፍቆ  የሚያደርገው ጠፍቶት የሚባዝን ለመሆኑ አንዱ ማሳያ ስርዓቱ ከሚታወቅበት መሰረታዊ አቋሙ ተንሸራቶ የባጥ የቆጡን ሲዘላብድ ለተመለከተው  የዕውር ድንብር ጉዞ ውስጥ እንዳለ ይገነዘባል። አርበኞች ግንቦት ሰባት ከተመሰረተ አንስቶ አገርና ህዝብን እያጠፋ ካለው ወሮበላው የወያኔ ቡድን ጋር ሁለንተናዊ ትግል እያካሄደ ይገኛል። የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለአንድ ሳምንት ባካሄደው ጥልቅ ስብሰባ የንቅናቄውን ስትራቴጂ የፈተሸበትና ወቅታዊ የአገራችንን ሁኔታ በስፋት የታየበት ሙሉ መግባባት ላይ የደረሰበት ነው።በድርጅቱ ውስጥ ያሉ አጠቃላይ ተግዳሮቶችን ነቅሶ በማውጣት ለችግሮቹም የመፍትሄ አቅጣጫ ያስቀመጠበት ነው።  በህዝባችን ላይ በሃይል የተጫነውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንድምታ የተቃኘበትና ከአዋጁ ጋር በተያያዘ መሰራት ያለባቸውን ስራዎች የወሰነበት ነው። በተለይም አገር ውስጥ ባለው የሕዝባዊ አመጽና የሕዝባዊ እምቢተኝነት እንቅስቃሴዎች ላይ አመራሩ ሙሉ አቅሙን አሟጦ በመጠቀም የለውጥ ትግሉ ለማፋጠን በአገራዊ ወኔ ተነሳሽነት መንፈስ የተነሳበት ነው። በአገር ውስጥና በውጭ ያለው የፖለቲካ አሰላለፍ የታየበትና ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ ምስረታ ከወዲሁ እነደ ድርጅት በተናጥልና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በጋራ መደረግ ስለሚገባቸው ጉዳዮች ስምምነት ላይ የተደረሰበት ነው።የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ከንቅናቄው ስትራቴጂ በመነሳት የስራ ቅደም ተከተል በማስቀመጥ ከስራው ጋር በተገናኘ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን በማደላደል በቁርጠኝነት መንፈስና በተናበበ አሰራር የሃገር ውስጥ የለውጥ ትግሉ ከነበረው  የበለጠ አቅም ለመገንባት የወሰነበት ነው።   በአብዛኛው የሃገራችን ኢትዮጵያ ክፍሎች ህዝቡ ያደረገውንና እያደረገ ያለውን ትግል ፖለቲካዊ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ በጭካኔና በጉልበት ለመቀልበስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የወጣ ቢሆንም ዛሬም ሕዝቡ ለመብቱና ለነጻነቱ ያለውን አይበገሬነት ከበፊቱ በተጠናከረና የወያኔን ጥቃት እንዳመጣጡ በመመከት አኩሪ ተጋድሎዎችን እያደረገ ነው።  አርበኞች ግንቦት ሰባት ከህዝቡ ጋር በመሆን በሁለንተናዊ መልኩ የለውጥ ጥረቱን በመደገፍ፣ በማስተባበርና በመምራት ያለ የሌለ ሃይሉን በመጠቀም ለኢትዮጵያ ሕዝብ የቁርጥ ቀን ደራሽነቱን ያረጋግጣል። አምባገነኑ አገዛዝ በህዝባችን ላይ በግፍ እያደረሰ ያለውን ጥቃት ለመታደግና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ መላው የሃገራችን ሕዝብ በህዝባዊ እምቢተኝነት፣ በህዝባዊ አሻጥር ፣በህዝባዊ አመጽና በውጪው ዓለም በሚደረገው ሃገር አድን እንቅስቃሴ ዛሬውኑ በመሳተፍ ሃገራዊ ግዴታውን እንዲወጣና የተቃዋሚ ሃይላት በትናንሽ ልዩነቶች ላይ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ የህዝብን የስልጣን ባለቤትነት ተቀብለውና ህዝቡ ዴሞክራሲያዊ መብቱን ተጎናጽፎ  የፖለቲካ ድርጅት ወይም ድርጅቶችን  ለስልጣን እስከ ሚያወጣ ድረስ ልዩነቶቻቸውን አጥበው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከተጋረጠበት አደጋ ለመታደግ በጋራ እንዲነሱ የአርበኞች ግንቦት ሰባት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ወገናዊ ጥሪውን ያቀርባል።

የስብሰባው ተሳታፊዎች ፡-

1, አርበኛ ታጋይ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ – ሊቀመንበር

 2, አርበኛ ታጋይ መአዛው ጌጡ – ምክትል ሊቀመንበር

3, አርበኛ ታጋይ መንግስቱ ወልደስላሴ – የፖለቲካ መምሪያ ሃላፊና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል

4, አርበኛ ታጋይ ገበየሁ አባጎራው – የመረጃና ደህንነት መምሪያ ሃላፊና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል

 5, አርበኛ ታጋይ ተስፋሁን ተገኘ – የስልጠናና ትምህርት መምሪያ ሃላፊና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል

 6, አርበኛ ታጋይ ታሪኩ ግርማ – የአስተዳደር መምሪያ ሃላፊና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል

 7, አርበኛ ታጋይ ኮማንደር አሰፋ ማሩ – የወታደራዊ መምሪያ ሃላፊና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል

 8, አርበኛ ታጋይ ኑርጀባ አሰፋ – የውጭ ጉዳይ መምሪያ ሃላፊና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል

   አንድነት ሃይል ነው! ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

መጋቢት  16/2009 ዓ/ም የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ

ወያኔ በኤርትራ ላይ

Standard

      አንድ ወቅት ላይ ኮ/ል መንግስቱ ሀይለ ማርያም ወያኔን መሳርያ ብቻ ሳይሆን ሱሪም ያስታጠቀው ሻዕብያ ነው ብሎ ነበር።ኮሎኔሉ  ይህን ሲሉ አልተሳሳቱም  ነበር።ነገር ግን ያዉ ሌባና ሌባ ሲሰርቅ ቢተባበርም በመከፋፈል ላይ ግን አልተስማሙም ነበርና እጅግ ከፍተኛ የሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት ያስከተለ ጦርነት አካሄዱ ።

      ከወደ ሰሞኑም የወያኔ አሻንጉሊት ጠቅላይ ሚኒስተር ሀይለ ማርያም ደሳለኝ በኤርትራ ላይ የሚከተሉትን ፓሊሲ እንደሚቀይሩ አስታውቀዋል ።ዶ/ር ተብዬው ደብረጽዮን ገብረሚካኤልም መከላከያ ሰራዊቱ ዝግጁ እንደሆነና በኤርትራ ላይ እርምጃ እንደሚወስድ በፌስቡክ ገፁ በኩል ደስኩሮ ነበር።

      ይሁን እንጂ በአሁኑ ሰአት ከኤርትራም ይሁን ከኢትዬጵያ በኩል ጦርነት ለመግጠም  ከህዝቡ በኩል ፍላጎቱ የለም ።ሁለቱን ወንድማማች ህዝቦች ከዚህ በፊት ደም ያቃቡት ወያኔና ሻዕቢያ ናቸው።ወያኔም አሁን ላይ ከፍተኛ የሆነ ህዝባዊ ጫና እያረፈበት ነው ።ግብአተ መሬቱ እየተፋጠነ ያለዉ ወያኔ በስተመጨረሻ በስልጣን ሊያቆያዩት የሚችሉትን ካርዶች ሁሉ እየመዘዘ ነው።አሁን ላይ ወያኔ በኤርትራ ላይ ጦርነት ቢጀምር ከዳር እስከዳር ደግሞ የተቀጣጠለዉ ህዝባዊ ዓመጽ እና እምቢተኝነት ይበልጥ ተጠናክሮ ይቀጥላል ።

 ዘ ኦሎምፒያ

አየር ኃይል ውጥረት ውስጥ ገብቷል፤ 11 አብራሪዎች ታስረዋል

Standard
በደብረ ዘይት የሚገኘው የአየር ኃይል ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንደሆነ ምንጮች ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያውያን ፓይለቶች አታበሩም ተብለው ግራንድ ከተደረጉ በኋላ ከምስራቅ አውሮፓ የመጡ ቅጥረኞች ብቻ እንዲያበሩ መወሰኑን ተከትሎ 40 የሚሆኑ አብራሪዎች የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ አስገብተዋል፤ መልቀቂያ ያስቡት አብራሪዎች ግዳጃቸው እስከሚቀጥለው ሐምሌ ወር ድረስ ብቻ እንደሚሆንም ታውቋል፡፡የአገልግሎት ጊዜያቸው ገና በመሆኑ ምክንያት መልቀቅ የማይችሉት አብራሪዎች ሥራቸውን ጥለው እየጠፉ እንደሆነ የሚናገሩት የመረጃ ምንጮች ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ብቻ አራት የዐማራና ሰባት የኦሮሞ ተወላጅ አብራሪዎች ሲጠፉ ተይዘው ታስረዋል ተብሏል፡፡ ከታሰሩት አብራሪዎች መካከል አንድ የዐማራ ተወላጅ አብራሪ የደረሰበት እንደማይታወቅና ከጎንደር የሔዱ ቤተሰቦቹ በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ሊያገኙት እንዳልቻሉ ነው የተነገረው፡፡
Ethiopian-Airforce
ሌላው ለውጥረቱ መንስኤ ነው የተባለው በከፍተኛ ጀነራሎቹና በታችኛው እርከን ላይ ባሉት መካከል ልዩነት መፈጠሩ ነው ያሉት ምንጮች ወታደራዊ እዝና ተዋረድ መተግበር ካቆመ እንደሰነባበተ ገልጸዋል፡፡ ለአየር ኃይል አባላት በየትውልድ ቦታቸው የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ ተፈቅዶላቸው የነበረውን አፈጻጸም ላይ ችግር መኖርም ሌላው የውጥረቱ መንስኤ ነው ብለዋል፡፡ የአየር ኃይል እማኞች እንደሚሉት በአየር ኃይል ግቢ ውስጥ የተፈጠረው ውጥረት ከመቼውም ጊዜ የተለየ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በ ሙሉቀን ተስፋው