አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ

Standard

“በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ኢፈርት 3ቢሊዮን ብር ለኢትዮጵያ አበድሯል” ስዬ አብርሃ በ1992ዓም.ከ1987 ጀምሮ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በሞኖፖሊ እንዲቆጣጠር ታልሞ ሀብታችንን ማግበስበስ የጀመረው ይህ ኢፈርት/ትእምት የተሰኘው የህወሃት የኢኮኖሚ ዘራፊ ክፍል-ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በመለስ ቀጭን የማዘዣ ትእዛዝ  ያለምንም እፍረት 3 ቢሊዮን ብር ተበደርኩ ብሎ አይን ያወጣ ዘረፋ ፈጸመ።በብድር ስም የወሰደውን ሳንቲም ሳይመልስ “አበዳሪ” ሆኖ ከካዝናችን አጋበሰ። አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ!!!!

*******

የትልማ ዘራፊነት!!!!

በ1951 ዓ.ም የጸደቀው የኢትዮጵያ ፍትሃብሒር ሕግ እና በ2001ዓ.ም ተሻሽሎ የጸደቀው የማህበራት መተዳደሪያ ሕግ-በጎ አድራጊ የግልና መንግስታዊ ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ከታክስ ግብር ቀረጥ እና ቫት መሰል የአገር ውስጥ ገቢ ነጻ ያደርጋቸዋል። ሆኖም ሁሉቱም ሕግ በጎ አድራጊ ማህበራቱ ከአትራፊ የንግድ ስራ ላይ መሰማራትን በጥብቅ ያግዳል- ግን ትልማ/ትግራይ ልማት ማህበር/ በዚሁ ሕግ ደንብ መሰረት እንደ በጎ አድራጊ ማህበር ተመዝግቦ የተቋቋመ መሆኑን ከራሱ ከማህበሩ ድህረ ገጽ ላይ Tigeray Development Assosiation (TDA)ላይ ማየት ይቻላል። ሆኖም ትልም ከበጎ አድራጎት ስራው በተጨማሪ አገሪትዋን የሚበዘብዝበት ትልቁ መሳሪያው ንግድና ኢንቨስትመንት እንደሆነ እናያለን።እንደ ሰላም ባስ በ600ሚሊዮን ብር ካፒታል የሚንቀሳቀሱ ግብር ታክስና ቀረጥ የሚከፍሉትን ባለሀብቶች የሚገልበትን ዘራፊ የንግድ ተቋሞችን ያሰማራ ተቋም ነው። ግብርና ታክስ ላለመክፈል “እኔም በጎ አድራጊ ማህበር ነኝ” እያለ ሕጉን ይጠቅሳል ግን አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ እንዳሉ የታክስ፣ግብር ግዴታውን ደግሞ እኔ የህወሃት ነኝ ምን ታመጣላችሁ በሚል ዘረፋውን ያጣጡፋል።

ይህች ናት እንግዲህ ህወሃት መራሹ ስር ያለችው ኢትዮጵያ!!!!

***

የትልማ አስገድዶ ዘራፊነት!!!

ትልም/ትግራይ ልማት ማሕበር/ በድፍን ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የከፈተ የህወሃት ድብቁ የመንግስት አካል ነው። በመላ አገሪቱ ያሉ ነጋዲዎች ለትልማ ማህበር ዓመታዊ የገንዘብ ድጋፍ አድርገው የማህበሩን ሰርተፊኪት ያላገኙ ጸረ ልማት ነጋዴ፣ነፍጠኛ ነጋዴ፣ጠባብ ነጋዴ፣ አሸባሪ ነጋዴ  ተብለው በተለያየ የኢኮኖሚ ጥቃቶች ከገበያው እንዲወጡ ይደረጋሉ። በዚህም ምክንያት ነጋዴው ህብረተሰብ ክፍል ግብር፣ታክስ፣ቀረጥና ቫት ከመክፈል ይልቅ የቱንም ያህል ቢበዛ ለትልማ መዋጮ መክፈል የህልውና ዋስትና የሚያሰጥ ስለሆነ ላለመሞት እያሉ እየተሽቀዳደሙ በቅድሚያ የሚከፍሉት መንግስታዊውን ግዴታቸውን ሳይሆን የህወሃት መዝረፊያ ማሽን ለሆነው ትልማ ለመሆን ችሎዋል።

በ አሚር አቦከር

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.