የጎንደርን ህዝብ በጅምላ ለመጉዳት የተደረገ ዘመቻ

Standard

በቅርብ በሚገኘው በዳባት ወረዳ የአጅሬ ጃኖራ ላይ በህፃናት ላይ የደረሰውን እልቂት እናስታውሳለን። በአንድ የክትባት ብልቃጥ ተወጉት አስራ አራት ህፃናት የታመሙ ሲሆን አራቱ ወድያው እንዲሞቱ ሆኗል ቆይቶ አምስተኛው ህፃን የሞተ መሆኑን ካሁን ቀደም መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በወቅቱም ህፃናቱን ህክምና ማድረስ አለመቻሉ ታውቋል።ይባስ ብሎ የዳባት አዲአርቃይ እንዲሁም ደባርቅ በአቶ አየልኝ ሙሉአለም የቀድሞ የአማራ ጤና ቢሮ ሃላፊ የአሁኑ የሠሜን ጎንደር አስተዳዳሪ በተጠነሰሰ ሴራ አማካኝነት የደባርቅ ሆስፒታል አገልግሎት ወደማይሰጥበት ደረጃ እንዲሸጋገር እያደረጉት ይገኛል።ሰራተኛውን በማስፈራራት በአንድ ወር ውስጥ ከሃምሳ በላይ ነባር ባለሙያ ከስራ እንዲለቅ ተደርጓል። ሰራተኞች ሰብአዊ መብታቸው ተገፎ በሃላፊው በኩል የስድብ እንዲሁም አንድ ነርስ ባለሙያ ሃላፊው ቢሮ አስጠርቶ በጥፊ እና በቦክስ ተመትቷል። ባለሙያው ከፍተኛ በሆነ ችግር ውስጥ ይገኛል። ሆስፒታሉ በመዳህኒት እጦት ላይ መሆኑም ታውቋል።ይህ እየሆነ ያለው ሆን ተብሎ አካባቢውን ለመጉዳት እንደ እብድ የሚቆጥሩትን ከጠለምት ወረዳ በሙስና የተባረረ ሃላፊ በመመደብ ነው፡፡ የአካባቢውን ማህበረሰብ ለመጉዳት አዲስ ሃላፊ በማስመጣት በስድስት ወር ውስጥ የተለያዩ ዲፖርትመንቶች እንዲዘጉ ተደርጓል። ከነዚህም ውስጥ የጥርስ ህክምና የአልትራሳውንድ አገልግሎት ዋናዋናወቹ ናቸው፡፡ ደባርቅ ላይ በመዘጋቱ ጎንደር እንዲሄዱ ይገደዳሉ። መሳሪያወቹ ጎንደርም ተሂዶ ተሟልተው ስምማይገኙ መፍትሄ የለም።በየወሩ ከ20 የሚበልጡ ሰራተኞች ደሞዝ ሰበብ እየተፈጠረ እንዲቀጡ እና ተማረው ሃገር እንዲለቁ ይደረጋል። ይህ ደግሞ በነባር ሰራተኞች ላይ ጎልቶ ይታያል፡፡ በሚገርም ሁኔታ በዚህ ሰአት በሆስፒታሉ ምንም አይነት ግላብ የለም። ሰራተኞች ያለ አንዳች መረጃ እንዲታሰሩ ያደርጋል። ለሽልማት እጩ የነበረው ሆስፒታል ወደ ሁዋላ እንዲመለስ የማሻሻያ ስራዎች እንዳይሰሩ እየተደረገ ነው።ወያኔ ጎንደር ውስጥ ህዝቡ አንቅሮ እንደተፋው ግልፅ ነው። ደባርቅ በቅርቡ የተዘጋጀ የሩጫ ውድድር አምሳተፍም ብሎ የግፍ አገዛዝ በቃኝ ማለቱን ዘግበናል።ከቦታው መረጃውን ላደረሱን እናመሰግናለን።

በአሰግድ ታመነ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.