በአገሪቱ የሚገኙ ዋና ዋና የደህንት አባላት ድሬዳዋ ውስጥ ለ9 ቀናት የቆየ የማጣሪያና የመለያ ስብሰባ አካሂደዋል

Standard

ግንቦት ፲፭ ( አሥራ አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሚያዚያ ወር መጀመሪያ ላይ በአገሪቱ የሚገኙ ዋና ዋና የደህንት አባላት ድሬዳዋ ውስጥ ለ9 ቀናት የቆየ የማጣሪያና የመለያ ስብሰባ አካሂደዋል። በስብሰባው ላይ የህወሃት አባል ያልሆኑ የሌሎች ብሄር ተወላጆች፣ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የደህንነት አባላትን ለጠላት አጋልጠው በመስጠት ህይወታቸው እንዲያልፍ እያደረጉ ነው በሚል ከፍተኛ ወቀሳ ደርሶባቸዋል። የደህንነት አባላቱ ለስርዓቱ ታማኝ ያልሆኑ ባልደረቦቻቸውን አጋልጠው እንዲሰጡ ማስጠንቀቂያ አዘል ማስፈራሪያ ተሰጥቷቸዋል። የደህንነት አባላት በተለያዩ ምድቦች ተከፋፍለው እርስ በርስ እንዲገማገሙ መደረጉን የገለጹት የኢሳት ምንጮች፣ በተለይም ድሬዳዋ እና ጅጅጋ ላይ ባልታወቀ ምክንያት የተገደሉትን ሁለት የጸረ ሽብር ግብረሃይል የደህንነት አባላትን መረጃ እንዲያወጡ ሲጨናነቁ ሰንብተዋል። ባለፈው አንድ አመት ከ6 ያላነሱ የደህንነት አባላት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣ የደህንነት ባለስልጣናት ግድያውን የሚፈጽሙት የራሳችን የደህንነት አባላት ናቸው ብለው እንደተናገሩና በስብሰባው ላይ የተገኙት የደህንነት አባላቱ የሚጠረጥሩዋቸውን ሰዎች እንዲጠቁሙ ተጠይቀዋል። የኢሳት ምንጮች እንደሚሉት ግን ግድያው በመከላከያ የደህንነት አባላትና በመደበኛው የደህንነት አባላት መካከል ሳይፈጸም እንዳልቀረ ይገልጻሉ። በቅርቡ የተገደሉት ሁለቱ የጸረ ሽብር ግብርሃይል የደህንነት አባላት፣ በመከላከያ የደህንነት አባላት ተገድለዋል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል። አንድ የደህንነት ባለስልጣን በስብሰባው ላይ “እንዲህ አይነቱ ግድያ የሚፈጸመው አስመራ ባሉ ተቃዋሚዎች ሳይሆን በእኛው አባላት ነው” ያሉ ሲሆን፣ እንዲህ አይነቱን ግድያ እና ስርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል ነገር እንዲፈጠር አንፈቅድም በማለት በሃይለቃል መናገራቸውን ምንጮች ገልጸዋል። በአቶ ጌታቸው አሰፋ የሚመራው የደህንነት ተቋም፣ ከመከላከያ የደህንነት ተቋም ጋር የፈጠረው አለመግባባት እርስ በርስ እየተፈራሩ እንዲኖሩ እንዳደረጋቸው ምንጮች ገልጸዋል። የዋናው የደህንነት መስሪያ ቤቱ ስብሰባ ከጠራህ በሁዋላ፣ ስብሰባውን ሳትጨርስ በተለያዩ መንገዶች የምትገደልበት ሁኔታ እየተፈጠረ በመሆኑ፣ በጋራ ሆኖ ስብሰባ ማካሄድ እየቸገረ ነው የሚሉት እነዚህ ምንጮች፣ አብዛኞቹ የሚገደሉት ከዋናው ደህንነት ሰራተኞች በመሆኑ፣ ገዳዮቹ የመከላከያ የደህንነት አባላት ናቸው ብለው እንዲያምኑ እንዳደረጋቸው ይገልጻሉ። “በደህንነት አባላቱ ውስጥ የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ ሙከራ ከማድረግ ይልቅ ችግሩን ከብሄር ጋር አያይዞ ለማቅረብ መሞከር ራስን ማታለል ነው፣ ችግሩ የራሳቸው የውስጥ ችግር በመሆኑ መፍትሄውንም መፈለግ ያለባቸው ራሳቸው ናቸው” ሲሉ ያክላሉ።

Advertisements

​ከ7 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን መራባቸው በተነገረ በሳምንት 200 የሚሆኑ አዳዲስ ታንኮች ኢትዮጵያ መግባታቸውን አነጋገረ

Standard

ሚያዚያ 24 ቀን 2009 ዓም ጠዋት በርካታ ቁጥር ያላቸው አዳዲስ ታንኮችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ሾፌሮች ገልጸዋል። በጅቡቲ ወደብ 200 የሚሆኑ አዳዲስ ታንኮች የተራገፉ መሆኑን የሚገልጹት የአይን እማኞች፣ ከእነዚህ መካከል የተወሰኑትን ታንኮች የጫኑ ሎቤድ መኪኖች ወደ ደብረዘይት ተንቀሳቅሰዋል። ከ7 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን መራባቸው በተነገረ በሳምንት በእርዳታ እህል ፋንታ ይህን ያክል ቁጥር ታንክ ወደ አገር ውስጥ መግባቱ ግርምት እንደፈጠረባቸው ሾፌሮች ገልጸዋል። ገዢው ፓርቲ በአገር ውስጥ ከገባበት የፖለቲካ አጣብቂኝ ለመውጣት ከኤርትራ ጋር ጦርነት ሊያደርግ እንደሚችል የተለያዩ ፍንጮች እየታዩ ነው። ምላሻቸው እጅግ አነስተኛ ቢሆንም፣ የስራዊት ምልመላ ለማድረግ ተደጋጋሚ ማስታወቂያዎች መውጣታቸው እንዲሁም በኤርትራ ላይ አዲስ ፖሊሲ እንከተላለን በመላት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ትግራይ ላይ ተገኝተው ንግግር ማድረጋቸው፣ አገዛዙ የተነሳበትን ህዝባዊ ተቃውሞ ለማስቀየስ ሊጠቀምበት እንደሚችል ሁኔታውን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ይገልጻሉ።

በ በሀይሉ ዳምጤ

ልዩ የተማሪወች ንቅናቄ ተጀመረ 

Standard

       በደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ ተማሪወች የነፃነት ትግል ፅሁፎች በት/ቤት ሰሌዳወች ላይ እየፃፉ ነው፤ የሌሎች ዩኒቨርስቲወች ተማሪወች ሁለገብ የትግል ንቅናቄውን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀርቧል።በት/ቤት ሰሌዳወች ላይ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፣ አርበኞች ግንቦት 7፣ አንድ ኢትዩጲያ የሚሉ ፁሁፎች እየተፃፋ ሲሆን በእነዚህ ፁሁፎች ብቻ አስተማሪወችና የህወሓት ቅጥረኛ ጆሮጠቢወች፣ የት/ቤቱ የህወሓት/ወያኔ አስተዳደር ክፋኛ መረበሻቸው ታውቋል።” የፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ህልም እውን ይሆናል!” “የመሪያችንን ትዕዛዝ ለማስፈፀም ለነፃነት እስከሞት!!” በማለት የነፃነት ትግሉን እያቀጣጠሉ ያሉት ተማሪወች በመላ ኢትዩጲያ ዩኒቨርስቲወች ነፃነት ፈላጊ ተማሪወች የሚቀጣጠል ትግል እንደጀመሩ ይናገራሉ።የወያኔ ሰላዩች እንደሚከታተሉን እኛም በትክክል እየተከታተልናቸው እንገኛለን የህቡዕ ቡድኑን መዋቅር በማስፋት ትግላችን መልኩን እየቀየረ በእብሪት ጥጋብ ልቡን ያሳበጠውን የወያኔ ወንበዴ ቡድን መቆሚያ መቀመጫ በማሳጣትና እንዳይረጋጋ አድርጎ በመረበሽ ለነፃነት እስከህይወት መስዋዕትነት የደረሰ ትግል በአንድነት አድርገን ነፃነታችንን እንቀዳጃለን በማለት ሁሉም በተግባር ለነፃነት እንዲነሳ ጥሪ ያስተላልፈዋል።

በ ከታ ማኛ

በቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኘው ወጣት አባይ ዘውዱ ሕይወቱ አዳጋ ላይ መድረሱ ታወቀ

Standard

  ከሰሜን ጎንደር ታፍኖ በቂሊንጦ የስቃይ ማጎሪያ የሚገኘው የቀድሞ ኣንድነት ፓርቲ ኣመራር ወጣት ኣባይ ዘውዱ በእስር ቤት ሕይወቱ ሊያልፍ እንደሚችል በከፍተኛ ሰጋት ላይ ወድቋል፡፡ ኣባይ ዘውዱ በደረሰበት የጉበት እና ጣፊያ እብጠት ሊፈነዳ ሲሆን በተጨማሪም በቲቪ-በከፍተኛ ደረጃ መታመሙ በደረሰን ጥቆማ ዛሬ 22/08 ቂሊንጦ በመሄድ ከራሱ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ወጣት ኣባይ ዘውዱ በህመሙ ሰውነቱ ኣልቆ በሰው ተደግፎ እያቃሰተ ማየት ያማል፡፡ የተሟላ ህክምና እንደተከለከለ ኣባይ እንባውን እያፈሰሰ ይናገራል፡፡ ይህ ለመላው ኣገር ወዳድ ሕዝብ በዝምታ ተመልክቶ የወጣት ኣባይ ዘውዱ ሕይወት ልናጣው ከቻልን  ሕዝብ ትልቅ ውድቀት ትልቅ ዋጋ እንደሚያስከፍል መገንዘብ ያሻል፡፡ ኣባይ ዘውዱ-ሁለተኛ ድግሪውን ከቅርብ ጊዜ በፊት ያጠናቀቀ ሲሆን በከፍተኛ ትምህርት የቆይታውም ቢሆን ከባሕር ዳር ዩንቨርስቲ የማዕረግ ተመራቂ የነበረ ወጣት ምሁር ነው፡፡ ኣባይ ዘውዱ የቀድሞ ኣንድነት ፓርቲ ከተቀላቀለ በኃላ በነበረው ንቁ ተሳትፎ ከሚሰራበት ቦታ ከማባረር እንስቶ በኣካሉ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሲደርስበት የቆየ ጠንካራ ጓዳችን መሆኑ ይታወቃል፡፡ በተለይ ለሱዳን ሊሰጥ በታሰበው መሬት ዙሪያ ኣባይ ዘውዱ ከጎንደር ኣዲስ አበባ ድረስ በመምጣት በኣንድነት ፅ/ቤት ሰፊ የዳሰሳ ጥናቱን ካቀረበ ወዲህ በወያኔ አይን እንደገባ ይነገራል፡፡ ለዚህ ጀግና ጓዷችን ኣገር ወዳድ ሊደርስለት ይገባል፡፡ ወጣት አክቲቪስቶች የሚዲያ ኣካሎች በሙሉ ወጣት ኣባይ ዘውዱ የተሻለ ህክምና እንዲሰጠው ግፊት ማድረግ ሕይወቱን የመታደግ ግዴታ ኣለበት፡፡ የነቃ ተሳትፎ ያላቸው የኣማራ ተወላጅ የሚደርሰው ዘር የማጥፋት ድርጊት ሊወገዝ ኣምሮ ሊታገሉት የሚገባ ተግባር ነው፡፡ ሁሉም ወገን ወዳድ ለኣባይ ዘዉዱ ድምፁን ይሰማለት፡፡

የአዲስ አበባ የታክሲ ሾፌሮች አመፅ ቀስቃሸ የታክሲ ጥቅሶችን በአስቸኳይ እንዲያነሱ በኮማንድ ፓስቱ ታዘዙ

Standard

 ካለፈው ሳምንት ሚያዚያ 11 ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ስቴዲየም በሚገኘው የመንገዶች ባለሥልጣን አዳራሽ  ከወያኔ ሰዎች ጋር እየተወያዩ የሚገኙት ባለ ኮድ አንድ የታክሲ ሾፌሮች በቁጥር ከ5ሺ ይልቃሉ ተብላል፡፡

ውይይቱ የተዘጋጀው በአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣንና በኮማንድ ፖስቱ ሲሆን አዲስ የወጣውን የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ ደነብ ቁጥር 395/2009 ከሚመለታቸው አካላት ጋር ለማስተዋወቅ የተሰናዳ ነው በሚል ነበር፡፡

ኾኖም መድረኩ ቅሬታና የዓመታት ብሶት ገንፍሎ በወጣባቸው የታክሲ ባለንብረቶችና ሾፌሮች ቁጥጥር ሥር ወድቋል ለማለት ያስደፍራል፡፡

በሰባቱ ቀናት ስብሰባ የመናገር እድል የተሰጣቸው ተወያዮች መንግሥትን ክፉኛ የተቹ ሲሆን የብዙዎቹ አቤቱታ “መንግሥት እኛን እንደተቃዋሚ ፓርቲ እንጂ እንደ አገልግሎት ሰጪ አድርጎ አይመለከተንም” የሚል ነው፡፡
“እኛን ከመክሰሳችሁ በፊት ራሳችሁን ብትፈትሹ ጥሩ ነበር” ያሉ አንድ የታክሲ ባለንብረት “በአገሪቱ ሙስና የተፈለፈለው ከናንተ ቢሮ አይደለምን?” ሲሉ ጉቦ የማይጠይቅ ትራፊክ በአዲስ አበባ በተለይ ደግሞ በኦሮሚያ ፈልጎ ማግኘት እንደማይቻል የ15 ዓመት ልምዳቸውን በመጥቀስ አብራርተዋል፡፡

በየቀኑ ከ10 እስከ 20 የሚሆኑ ታዳሚዎች ሐሳባቸውን እንዲሰጡ በተደረገበት በዚህ ዉይይት ፖለቲካዊ መንፈስ የነበራቸው ድምጾችም ተሰምተዋል፡፡
“በ97 ምርጫ ዋዜማ ለሰልፈኞች ነጻ ትራንስፖርት ሰጥታችኋል ብላችሁ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በበጎ እንደማታዩን ይገባናል፡፡” ያሉ ሌላ ባለንብረት ንግግራቸው በጭብጨባ ከተቀቋረጠ በኋላ ሐሳባቸውን የቀጠሉ ሲሆን ሁሉም ዘርፎችን መንግሥት ባለው አቅም ሁሉ እየደጎመ ታክሲን ቸል ያለበት ምክንያት ከዚሁ የጠላትን ስሜት የመነጨ እንደሆነ እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡

“ለመንግሥት ሠራተኛ በሰበብ አስባቡ ደመወዝ ትጨምራላችሁ፣ የኛን ታሪፍ ለማሻሻል ግን አንድ ቀን እንኳ አስባቸሁ ታውቃለችሁ?” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
በዚህ አስተያየት የተበረታቱ ሌላ የታክሲ ባለንብረት የመናገር እድሉን ያገኙ ሲሆን “እዚህ አገር በሕዝብም በመንግሥትም እየተጠላን፣ ዘላለም እየተረገምን የምንሠራ እኛ ታክሲዎች ነን፡፡” ካሉ በኋላ “ተመስግነን አናውቅ፣ አትርፈን አናውቅ፣ ሕይወታችን ተለውጦ አያውቅ፡፡ እስቲ ከታክሲ ሥራ ተነስቶ እዚህ ደረሰ የተባለ ሰው ንገሩኝ” ሲሉ ታዳሚውን ጠይቀዋል፡፡

“እኔ ንግግሬን በሌላ አትውሰዱብኝና እኛ ታክሲዎች ጧት ተነስተን ባንሠማራ እኮ አገሪቷም ትቆማለች፡፡ መንግሥትም የሚሽመደመድ ይመስለኛል፣ ከናንተ ውስጥ ግን ይህን የሚያስብ ያለ አይመስኝም” ሲሉ ሐሳባቸውን ቋጭተዋል፡፡ ታዳሚውም በጭብጨባ ድጋፉን ገልጾላቸዋል፡፡
” ለመሆኑ የመኪና መለዋወጫ ዋጋን ታውቃላችሁ? ስፔርፓርት ስንት ነው?” በሚል ጥያቄ የሰነዘሩ ሌላ የታክሲ ባለንብረት፣ “ዛሬ አንድ ስፖኪዮ ቢሰበር ስንት ብር እንደሚያስወጣን ብታውቁ ደፍራችሁ እዚህ ባልጠራችሁን ነበር” ሲሉ ጠንከር ያለ ሀሳብ ሰጥተዋል፡፡

“ለነገሩ መንግሥት ሕዝብን መስማት ካቆመ ስለቆየ በናንተ አልፈርድባችሁም፤ እኛ ትዝ የምንላችሁ እኮ አድማ ስንመታ ብቻ ነው፤ ጃንሆይንም ታክሲ ነው ያወረዳቸው፣ ታሪክ ብታውቁ ደፍራችሁ እዚህ አትጠሩንም ነበር” ሲሉ አስተያየት የሰጡ አባት በመድረኩ አስተናባሪዎች ተግሳጽ ደርሶባቸዋል፡፡

” እዚህ መድረክ ስላገኘን ብቻ እንዳመጣልን መናገር ተገቢ አይመስለንም፡፡ ታክሲዎች ለሕዝብ አገልግሎት እንዲሰጡና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ነው፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠር ገቢ ይቅርብኝ ብሎ ያለቀረጥ ከአንድ ሺ በላይ ታክሲዎች ወደ አገር ቤት እንዲገቡ የተደረገውም በዚህ ምክንያት ነው፡፡ የትርፍ ህዳጋችን መጨመር አለበት፣ ሥራው በሚፈለገው መልኩ እያተረፈን አይደለም የሚለው ተገቢ ጥያቄ ነው፡፡ እኛ ካመጽን አገር ትቆማለች ማለት ግን ኃላፊነት የጎደለው ንግግር ነው፤ መንግሥት እናንተ የምታገኙት ትርፍ ወቅቱን ያገናዘበ እንዳልሆነ ይረዳል፡፡ ለዚህም ጥናት እያደረገ ነው፡፡ በዚህ ዓመት የታሪፍ ማሻሻያ ለማድረግ እየሠራ ነው፡፡” የሚል ምላሽ ከመድረክ መሪዎች በአንዱ ተሰጥቷል፡፡

በተለይም መንግሥት እኛን እንደተቃዋሚ ፓርቲ እንጂ እንደ አገልግሎት ሰጪ አድርጎ አይመለከተንም ላላችሁት ግን በየ ታክሲ ውስጥ የተለጠፉ አመፅ ቀስቃሽ ፅሁፎች እንዳለ እናካለን እናም ይህንን አመፅ ቀስቃሽ የሆኑና ህዝብን የሚያበጣብጥ ፅሁፍ ባስቸካይ እንድታስወግዱ መባላቸውን ከተሳታፊዎቹ አንዱ ገልፆልናል።

በአሰግድ ታመነ