የህዝብን ጥያቄ በጠብመንጃ ኃይል ጨፍልቆና አድበስብሶ ማለፍ አይቻልም

Standard

         ደደቢት በረሀ ላይ እንደ አሸን የተፈለፈለው የህወሀት አገዛዝ በህገ-አራዊት እየተመራ የኢትዮጵያን ህዝብ ላለፉት 26 ዓመታት በመግደል፣ በማሰር፣ እንዲሁም የሀገርን ሀብት በመዝረፍ አስነዋሪ ወንጀል በመስራት ህዝቡንም በብሄርና በቋንቋ በመከፋፈል ሀገርን በክልልና በጎጥ በመሸንሸን ህብረተሰቡ ያለውን ሀይል እንዳይጠቀም በማድረግ ሰጥ ለጥ ብሎ እንዲገዛና አረመኔያዊ ስርዓት መውደቅ አለበት ብሎ በአደባባይ ወጥቶ በገሀድ እንዳይቃወም አንገቱን አስደፍቶ እንዲኖር መፍረዱ ሳያንሰው በተለያ ጊዜ እራሱ በሚቆጣጠረውና እንደፈለገ በሚያሽከረክረው የፕሮፓጋንዳ መለፍለፊያ ጣቢያው ሀገራችን በእድገት ጎዳና ላይ በመገስገስ ላይ ትገኛለች፤ ህዝቡም የመብቱ ተጠቃሚ ሆኗል እያለ በተደጋጋሚ ጊዜ ሲዋሽ የቆየው ሽፍታው ወያኔ ምናልባትም የህወሀት ባለስልጣናት እና የእነሱ አጫፋሪ የሆኑ ጥቂት ግለሰቦችን ያካተተ ካልሆነ በስተቀር የኢትዮጵያ ህዝብ በአሁኑ ሰዓት የኑሮ ውድነት አንገሽግሾት የዴሞክራሲ እጦት አንገብግቦት ስርዓቱን በመቃወም በየአቅጣጫው ብሶቱን በማሰማት ላይ ይገኛል፡፡
እነዚህ የንጹሀን ደም ያሰከራቸውና ገና ወደፊትም በርካታ የንጹሀንን ደም ለመጠጣት በዝግጅት ላይ ያሉት የህወሀት ባለስልጣናት በተለያየ ጊዜ እነሱ እራሳቸው የስልጣን እድሜያቸውን ለማርዘም ሲሉ ብቻ ከህዝቡ የነጠቁትን ሰላም፣ ዴሞክራሲና ነፃነት ለማስመለስ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚደረጉ ህዝባዊ ተቃውሞዎችንም ሆነ ይህ ስርዓት ያንገፈገፋቸው የህዝብ ብሶት የወለዳቸው የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች የሚያደርጉትን የትጥቅ ትግል ለማኮላሸትና ከህዝብ ለመነጠል ያልቆፈሩት ጉድጓድ ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም፡፡ታዲያ የኢትዮጵያ ህዝብ አሁን በሚገኝበት ደረጃ ላይ ለመድረስ በወያኔዎችና በተላላኪዎች አማካኝነት ለበርካታ አመታት የሚያሰራጩለትን የሀሰት ወሬ አሜን ብሎ ሳይቀበለው ውስጥ ውስጡን በመደራጀትና የወያኔን እንቅስቃሴ በንቃት በመከታተል መብቱ ሲረገጥ፤ መሬቱ ሲነጠቅና የመኖር ህልውናው ሲጠፋ ዝም ብሎ ከማየት ይልቅ እስከ አፍንጫው የታጠቀውን የህወሀት ወያኔን አገዛዝ በትጥቅ ትግል በማንበርከክና ህዝቡንም የስልጣን ባለቤት ለማድረግ በሀገራችንም ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም ዴሞክራሲያዊ የሆነ ስርዓት በመገንባት ወያኔ የከፋፈላትን ኢትዮጵያ ሳይሆን አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለመገንባት ዱር ቤቴ ብለው ርሀብ፣ ውሀ ጥም፣ ሀሩርና ቁሩ ሳይበግራቸው ለዚህ ለተቀደሰ አላማ ይህን አንባ ገነን ሽፍታ ወያኔን የሚታገሉ ሀይሎችን በመደገፍ እና በመቀላቀል ለነጻነቱ በሚችለው አቅሙ ይነሳ ።

አንድነት ሀይል ነው 


ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንቦት 7 !!

Advertisements

ህዝባዊ አመፁ ተጠንክሮ ቀጥሏል 

Standard

ህዝባዊ አመጹ ወደ አደገኛ ተቃውሞ ተቀይሯል ወልቂጤ ከፍተኛ አድማ ላይ መሆናቸው ትራንስፖርት መዘጋቱ ከአካባቢው በወጣ መረጃ ተሰምቷል የመርካቶ ሱቆች ለምን ዘጋችሁ በሚል ወደ አመጽ ተለውጦል የፌደራል ፖሊስ ልዩ ኃይል መርካቶን እየከበባት ነው ምዕራብ ታይዋን ቦምብ ተራ በዚህ ሰዓት አስፈሪ ግርግር ይታያል ነጋዴው አድማውን እየተቀላቀለ እንደሚገኝ በመርካቶ በርካታ ሱቆች ዝግ መሆናቸው የስርዓቱ ልሳኖችም ጭምር በዜና ሽፋን እየመሰከሩ ነው ። በተመሳሳይ በጎጃም አድማው እየበረታ ወደ ሞጣ ተሻግሯል ሞጣ ተቃውሞውን ተቀላቅላለች፡፡ ይህ ቁጣ ወደ አገር አቀፍ ትግል እየተለወጠ ይመስላል፡፡

ድል ለጭቁን ህዝብ ግፋ በለው!

ስንታየሁ ቸኮል

​አማራን የማያወቀው መብራት ሀይል

Standard

 ህወሃት አይደለም ለፋብሪካ መገንቢያ መብራት ለአማራ ክልል ሊሰጥ ነዋሪዉ እንኳን ባግባቡ መብራት አያገኙም፡፡ በተቃራኒዉ ትግራይ ዉስጥ 167 መካከለኛና ከፍተኛ ፍብሪካዎች እንደፈለጉ ክፍያ እንኳን ሳይከፍሉ መብራት 24 ሰአት ያገኛሉ፡፡ በትግራይ ከተሞች መብራት ጠፍቶ አያዉቅም፡፡ በዚህ ሁለት ቀን ደግሞ ብሶበታል፡፡ ባህርዳር ነበርኩ መብራት ከ 18 ሰአት በሁዋላ ነበር ያገኘሁት፡፡ ለማንኛዉም በባለፉት ሁለት ምርጫዎች መብራት ሊገባላችሁ ተብለዉ ፖል ቆሞ ገመድ ተዘርግቶ ንብረቱ ከጥቅም ዉጪ ሆነዉ የቀሩትን የተወሰኑትን ማየት ይቻላል፡፡ በዚህ መስሪያ ቤት ለምትሰሩ የአማራ ልጆች እናመሰግናለን መረጃዉን ስላካፈላችሁን፡፡

1. አማራ ክልል፡ ሰሃላ ሰየምት ወረዳ ከ 7 አመት በፊት የመብራት ፖል ተክለዉ የምሰሶ እንጨቱም እያረጀ የወደቀ

2. በአማራ ክልል፡ ባንጃ ወረዳ ጉበላ አካባቢ ፖል ከተተከለ 6 አመት የሞላዉ ፖሎችም ስራ ሳይሰሩ አርጅተዉ ወዳድቀዋል
3. አማራ ክልል፡ ከጎንደር ላይ አርማጭሆ ወደ ሮቢት የሚሄድ የገጠር ከተሞች ፖል ከተተከለ 11 አመት ሆነዉ
4. አመራ ክልል፡ ደጀን አካባቢ ያሉ ቀበሌዎች የመብራት እንጨት ተተክሎ እየበሰበሰ ካለ 11 አመቱ
5. አማራ ክልል ፡ ከደሴ ተነስቶ በዙሪያዉ ላሉ የገጠር ከተሞች ፖል ከተዘረጋላቸዉ 5 አመቱ
6. አማራ ክልል፡፡ ከደብረታቦር ወደ ፋርጣ ቀበሌዎች  ፖል ከተተከለ 6 አመት ያለፈዉ 
7. አማራ ክልል፡ ደቡብ ጎንደር ደራ ወረዳ ከአንበሳሜ ከተማ -ሰኔማርያም ቀበሌ እና ጎሃ ቀበሌ እንዲሁም ደወል ቀበሌ መጀመሪያ የተተከለው ፖል ኤሌክትሪክ ሳይለቀቅበት በማርጀቱ ሁለተኛ ዙር አዲስ ፖል ተተክቶ እስካሁን የኤሌክትሪክ ሀይል ያልተለቀቀበት
8. አማራ ክልል፡ ከ ከላላ አቤት ወሃ(ደቡብ ወሎ) ፖል ከተተከለ 4 አመት 
9. አማራ ክልል፡ ሰሜን ሸዋ ካሉት ውረዳዎች ውስጥ አጣዬ/ኢፍራታ እና ግድም ወረዳ አላላ ይምለዋ ቀበሌ ከዛሬ 26 አምት በፊት በጄኔሬተር መብራት ተጠቃሜ እና ደረጃውን የጠብቀ አስባልት መንገድ የነበርው አካባቢ 1983 ዓም ወዲህ መንገዱም ፍርስርሱ ወቷል፤መብራቱም ክነጄኔሬተሩ ድምጥማጡ ከጠፋ 26 አምት አለፈው።ከዛሬ 7 አመት በፊት ፖል ተተክሎ የአካባቢው ሰው የምብራት ብር አዋቶ ለመንግስት ግቢ አድርጎ ይህው በመጠባበቅ 7 አመት ሞላው።
10. አማራ ክልል፡ በጎንጅ ቆለላ ወረዳ የመብራት ፖልና ገመድ ከተዘረጋ ወደ 6 ዓመት ሁኖታል ሁኖም ግን መብራት የለዉም  ፖሎቹ ወዳድቀው ከጥቅም ዉጪ ሆነዋል፡፡

11. አማራ ክልል፡ በሰሜን ሸዋ ዞን አንፆኪያ ገምዛ ወረዳ ሀርቡ ወልዴ ቀበሌ ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ ፖልና ገመድ ተዘርግቶ ነገር ግን አገልግሎት የማይሰጥ፡፡ 
12. አማራ ክልል፡ ሚስራቅ ጎጃም በጎንቻ ሲሶ ወረዳ ግነደወይን ከተማ የዛሬ 7 አመት የቆመዉ ፖልና ገመድ እንጅ መብራት ተለቆበት የማያቅ
13. አማራ ክልል፡ ጎንደር ከተማንና አካባቢዉን ይጠቅም የነበረ ጣሊያን የተከለዉን ትልቅ ጄኔረተር ሳይቀር ነቅለዉ ወስደዉ ለትግራይ ህዝብ/አዲግራት አካባቢ በመትከል ጎንደርን ይሄዉ ለ26 አመት በጨለማ አስቀምጠዋታል፡፡
14. አማራ ክልል፡ በባለፈዉ ክረምት ደግሞ ደርግ የሰራዉን የዳበትን ማከፋፈያ ጣቢያ ትግሬዎች ፈታተዉ እቃወቹን በመኪና ሲጭኑ የአካባቢዉ ማህበረሰብ አስቀርቶታል፡፡ በዚህም እልክ የተጋባዉ ትግሬ የዳባትና ደባርቀ አካባቢ መብራት እነዳያገኝ አድርገዋል፡፡
15. አማራ ክልል፡ ደቡብ ጎንደር ደራ ወረዳ አካባቢ የተዘረጉ የኤሌክትሪክ ምሰሶወችና ገመዶች ያለጥቅም ተበላሽተዋል፡፡
 16. አማራ ክልል፡ ደ/ጓንደር ከእስቴ ወደ ቆማ የተተከለው ፖል ምርጫ ሊደርስ ሲል እንቅስቃሴ ይጀምሩና ምርጫው ሲያልፍ ይተውታል ይኸው 7 ዓመት ሞላው ፖሉ እየወደቀ ነው።

Miky Amhara

​የስራ ማቆም አድማ ጥሪ ለአማራ ክልል

Standard

ከሀምሌ 18-20 ለሦስት ቀናት የሚቆይ የሥራ ማቆምና ቤት ያለመውጣት አድማ ይካሄዳል።በአማራ ክልል ሁለተኛው ዙር የስራ ማቆምና አድማ ጥሪ እየተላለፈ መሆኑና ህዝቡም በንቃት ለመሣተፍ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው። በመላው አማራ ክልልል በህወአታዊያን እየደረሰ ያለው ግፍ ሳያንስ የኢኮኖሚው ዋልታና ማገር የሆነው ነጋዴው ማእበረሰብ ላይ ሌቦቹ ህወአታዊያን አንድ ጠብ የሚል ነገር ሳይሠሩ እየበሉ ጨርሰው ባዶ ያስቀሩትን ካዝና ለመሙላት እጅግ ያልተጠበቀ ግብር በእያንዳንዱ ከሊስትሮ እስከ ሚሊየነሮች ድረስ ማዥንጣቸውን የቆረጠ ግብር ተጥሏል። ህዝቡም ከዚህ የከፋ የለም በቃን ቨማለት ከፈቃድ መመለሥ እስከ ሸቀጦቹ ላይ ዋጋ በመጨመር ግብሩን መወጣት በተቻለ። ነገር ግን ነጋዴው ይህን አድርጎ ደሀውን ወገኑን ከማሠቃየት ይልቅ በሁለት ደረጃ የተቃውሞ ድምጹን ለማሠማት ቀን እየተቆረጠለት ነው።

1ኛው

ለሦስት ቀን ማለትም ከሀምሌ18/2009 ጀምሮ እስከ ሀምሌ 20/2009 የሚቆይ ምንም ያለመስራትና ቤት የመዋል አድማ በማድረግ የህወአታዊያኑን ያልተወለደ አንጀት ግፍ መቃወማችን መግለጽ

2ኛ

1ኛው ማሣያና አድማ መልእክት ሆኖት ህወአታዊው መንግስት በሚዲያ በቀጥታ ቀርበው የገቢ ግብሩ ፍትሀዊ አይደለም ተሰርዟል ካላሉ አድማው መልኩን ቀይሮ የትኛውም ነጋዴ የስራ ፈቃዱን ይመልሳል።

3ኛው
ከላይ የተጠቀሱት እየተተገበሩ ምላሽ ካልተሠጠ ወደፊት ወደሚገለጹ ወደ ሁለንተናዊ ትግል የሚገባ ይሆናል።በመሆኑም ከሀምሌ 18-20 ለሦስት ቀናት የሚቆይ የሥራ ማቆምና ቤት ያለመውጣት አድማ ይካሄዳል።መሰጃውን እናሠራጭ።

ማንም ይህን ህግ የጣሰ ከህዝብ ሳይሆን ከህወአታዊያን ነው።

​የህወሓት/ወያኔ አምባገነን ስርዓት አዳዲስ ወታደራዊ ተሽከርካሪወችን እያሰራጨ ነው

Standard

በኢትዩጲያ 8 ሚሊየን ህዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልገዋል።የተምች መሳይ ወረርሽኝ ከበቆሎ ሰብል በተጨማሪ በጤፍ እና በዳጉሳ ሰብል ላይ ተከስቷል በህወሓቱ መስፍን እንጂነሪንግ አካላቸው የተገጣጠሙ አዳዲስ የፈሳሽ መጫኛ ወታደራዊ ተሽከርካሪወች ከመቀሌ ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ገብተዋል። የህወሓት አምባገነን ስርዓት ለወታደራዊ ግዳጂ ለነዳጂ አቅርቦት እንዲሁም ለካምፕ የውሃ አቅርቦት የሚውሉ እኒህን የፈሳሽ መጫኛ ተሽከርካሪወች ጨምሮ በተለያየ ጊዜ ትልልቅ መሳሪያወች እና ወታደራዊ ተሽከርካሪወችን ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ ሲያስገባ ቆይቷል።ይህን በሚያደርገው ፦

• ከ8 ሚሊየን ህዝብ በላይ በረሃብ አለንጋ እየተገረፈ እና የተለያዩ እረጂ ድርጂቶች ከፍተኛ የረሀብ አደጋ በኢትዩጲያ መጋረጡን እያሳወቁ ባለበት ፣ የሚላስ የሚቀመስ አጠው በድርቅ የተጎዱ አካባቢወች ለህወሓት ሰረሽ እረሃብ እና ወረርሽኝ በሽታ ተጋልጠው እጃቸውን ለምፅዋት በዘረጉበት፣ ከ70 የላነሰ ሰው በአንድ ሰሞን በሞተበት ሰዓት ነው።

• በአብዛኛው የአርሷደሩ አካባቢወች የተምች ወረርሽኝ ሰብላቸውን እያወደመባቸው መፍትሄ አጠው ባሉበት ከበቆሎ ሰብል በተጨማሪ ሌሎች እንደጤፍ ፣ዳጉሳ ያሉ ሰብሎችን እያወደመ ባለበት ፣የማጥፊያ መድሀኒት አጠው በእጃቸው እየለቀሙ ባለበት ሰዓት ነው።

ህዝባዊ ጥያቄን በሃይል እና በተለያዩ የህግ ሽፋኖች እያለበሰ ብዙወችን በተለያዩ ማጎሪያወች እያሰቃየ ያለው የህወሓት ዘረኛ ስርዓት በዜጎች ላይ አግባብ ያልሆነ ከካፒታላቸው በላይ ግብር እየጫነ ነጋዴውን በማማረር ህዝቡን በከፍተኛ የኑሮው ውድነት ውስጥ አፍኖ ለመግዛት እየታተረ ባለበት በዚህ ወቅት የተለያዩ ወታደራዊ ቁሶች ግዥወችን ከውጭም ከሀገር ውስጥም ሲፈፅም ይስተዋላል።

@ የአርበኞቹ ልጂ

የነጋዴዎቹ  አድማ ተጠናክሮ ቀጥሏል

Standard

(ኢሳት ዜና – July 21, 2017)

— በኢትዮጵያ የነጋዴዎች አድማ መላ ሀገሪቱን እየሸፈነ ነው። በምስራቅ ሐረርጌ የተጀመረው የነጋዴዎች አድማ በአምቦ፣ ወሊሶ፣ ደምቢዶሎ፣ ነቀምት፣ ወለታ፣ ጊንጪ፣ ሱሉልታ፣ ሻሸመኔ፣ ዶዶላ… ተጠናክሮ ሲካሄድ ከሰነበተ በኋላ ወደ መዲናዋ አዲስ አበባ ተሸጋግሯል። አድማው ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያሳስቡ ወረቀቶች በመበተን ላይ ናቸው።

— በአዲስ አበባ ሳሪስ፣ በኮልፌ አጠና ተራ፣ ታይዋን ሰፈር፣ ዘነበወርቅ፣ አዲስ ጎማ፣ አቦ ወርቁ፣ ንፋስ ስልክ እና ሌሎችም ቦታዎች የንግድ ቤቶች እየተዘጉ ተቃውሞው በመካሄድ ላይ ነው።

— ዛሬ ሀምሌ 14 ቀን 2009 ዓ.ም ደግሞ ተቃውሞው አባይን በመሻገር በምስራቅ ጎጃሟ ሸበል በረንታ ወረዳ በዱሀ ከተማ አድማው ተጠናክሮ በመካሄድ ላይ ሲሆን ዱሀ አድማውን በመለኮስ የመጀመሪያዋ የአማራ ክልል ከተማ ሆናለች።

— ተመላሽ ወታደሮች እኛን ያየ ይቀጣ እያሉ ነው።

በአዲስ አበባ በሰላም ባስ ማቆሚያ የቦንብ ጥቃት ተፈፀመ

Standard

በአዲስ አበባ ከተማ ጎተራ አካባቢ ካለው ከቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት የሚገኘው እና ንብረትነቱ የሕውሀት የሆነው የሰላም ባስ ማቆሚያ ላይ ዛሬ እኩለ ለሊት አካባቢ የቦንብ ጥቃት መድረሱን 

ምንጮቻችን ከስፍራው ዘግበውልናል።በቦታው የነበሩ የአይን እማኞች ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለጱት ከሆነ፡ ፍንዳታውን ተከትሎ የጥይት ተኩስ እሩምታም እንደነበረ ገልጸውልናል።ወኪሎቻችን ተጨማሪ ማስረጃ እናዳደረሱን ዝርዝሩን ይዘን እንቀርባለን።