​ህወሓት /ብአዴን ለልዩ ሃይል ኮማንደር አዛዦች አድኑኝ ልመና እና የአድማ በታኝ ልዩ ሃይል አባላት የተግባር መልስ

Standard

 ህወሓት/ብአዴንና የፖሊስ መዋቅሩ ከፍተኛ ተቃርኖ ውስጥ ገብተዋል። በአንድ የሚያቆማቸው የመዋቅሩ መሰረት ፈርሷል።በቃ የላይኛው የስልጣን ወንበር በህዝባዊ እምቢተኝነት ሲነዋወጥ መዋቅሩን ጎራ ለይቶ መናከስ ጀምሯል። በተራ ፖሊስ መኮንኖች ከአዛዥ ኮማንደሮች እስከ ተራ ፖሊስ ድረስ እምነት አጦ ፣ ተስፋው ተሟጦ ያለበት ሁኔታ ከፍ ብሏል።የፖሊስ ኮሚሽኑ ከላይ ወደ ታች ተሸርሽሯል። በህወሓት የበላይነት የሚመራው ኮማንድ ፖስት ከተዘረጋ ወዲህ በክልሉ አድማ በታኝ ልዩ ሃይል ፖሊሶች የተፈጠረው መወዛገብ ህይወታቸውን ምስቅልቅሉን አውጥቶታል። ብዙወች የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ አስገብተዋል። በፍፁም መልቀቅ ክልክል ነው የተባሉ ደግሞ ፎርጂድ የህክምና ማስረጃ እስከማሰራት ደርሰዋል። በባህርዳር ጎርደማ ገብርኤል ወደ ሰባታሚት ቀበሌ በሚወስደው ዋና መንገድ የሚገኘው የአድማ በታኞች ካምፕ ውስጥ በአንድ ምሽት የጦር መሳሪያ መሰረቁ ይታወሳል። ከዚህ ጋር ተያይዞ በሰዓቱ ዋርድያ የነበሩ እስካሁን በእስር ይገኛሉ። በዚህ ካምፕ ከሚገኙት ውስጥ በቤተሰብ ጫና ፣ ስርዓቱ በሚያደርሰው በደል መሰል ምክንያቶች የስራ መልቀቂያ ያስገቡት ቁጥር 7 ደርሷል። እነዚህ ፖሊሶች መስራት አንፈልግም በማለት ፎርጂድ የህክምና ማስረጃ በፈለገ ህይወት ሆስፒታል አሰርተው አቅርበዋል። ነገር ግን እስካሁን በተቃርኖ በጥርጣሪ እየታዩ ይገኛል። አሁን ላይ ህወሓት/ ብአዴን እራሷን እየበላች ነው ። በዚህ ተግባሩ ደግሞ ታማኝ አገልጋዩቹን ለማወቅ የድረሱልኝ ጥሪ እያሰማ ነው።

ባንዳው አለምነው መኮንን ከህወሓት ወታደራዊ ጀነራሎች ጋር በመሆን በክልሉ የሚገኙ ልዩ ሃይል ኮማንደሮችን ሰብስቦ ነበር። ህገመንግስቱን ለመጠበቅ ፅናታችሁ አሁን በተግባር ልታሳዩን ይገባል ።የምትል የልመና ቁልምጫ ንግግር አድርጓል።

የአርበኞች ግንቦት 7 ሁለገብ ትግል ውጤቱ በተግባር እየታየ ነው። አሁን ላይ በፖሊሱ መካከል አለመተማመን መንገሱ እና ህዝባዊ አሻጥሩ የስርዓቱን መዋቅር ከስሩ እየቦረቦረ እያፈራረሰው ለመሆኑ ገላጭ ነው።

ትግሉ ይቀጥላል!!


የአርበኞቹ ልጅ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.