​የሜድሮክ ወርቅ ማውጫ ፋብሪካ መኪና ለሰዓታት ታገተ

Standard

 በህወሓቱ ሹሞች የሚደገፈው ንብረትነቱ የሺህ አላሙዲ የሆነ የሜድሮክ የወርቅ ማውጫ ቁፋሮ ፋብሪካ መኪና ለሰዓታት ባልታወቁ ሰወች ታግቶ መዋሉ ተነገረ።በቤንሻንጉል ጉሙዝ ቡለን ወረዳ ከሚገኘው የድርጂቱ ላብራቶሪ የተነሳው መኪናው ከተወሰነ ኪሎ ሜትር በኋላ ድባጢ ተብሎ በሚጠራ ከተማ አቅራቢያ መታገቱ ታውቋል። መኪናው ምን እንደጫነ ለማረጋገጥ ባይቻልም በቡለን ወረዳ በሚገኝ 4 የወርቅ ማውጫ የቁፋሮ ቦታወች ለናሙና ምርመራ በማለት በከተማው ከሚገኘው ላቦራቶሪ ወደ ውጭ ሃገር የሚልኩትን ወርቅ ወደ አዲስ አበባ ማዕከል እንደሚያመላልስ ተጠቁሟል ።

መኪናውን ያገቱት ሰወች በሹፌሩ ላይ መጠነኛ የአካል ጉዳት ያደረሱ ሲሆን ከተጫነው ላይ የወሰዱት ነገር ይኑር አይኑር የተረጋገጠ ነገር የለም። አጋቾቹ የወያኔ ስርዓት ሹሞች የጥቅም ተካፋይ ለሆነው ለዚህ ድርጂት የወርቅ ቁፋሮ ይሆን ዘንድ ከመኖሪያ ቀያቸው ያለምንም ካሳ የተፈናቀሉና በባህላዊ መንገድ ወርቅ እየቆፈሩና እያመረቱ ህይወታቸውን ይመሩ የነበሩ በግፍ ከቦታው የተባረሩ ወገኖች ሊሆኑ እንደሚችል ተገምቷል።

በሜድሮክ ኢትዩጲያ እህት ኩባንያ የሆነው የሜድሮክ የወርቅ ማውጫ ፋብሪካ በአካባቢው ነዋሪወች ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳት ቀላል የማይባል ነው ። በአካባቢ የወያኔ ሹሞች ነዋሪውን በማፈን በባህላዊ ዘዴ አምርቶ የሚኖረውን ባገለለ መልኩ የአካባቢውና የወረዳ የክልል ሹሞች ጥቅም በማሰብ ያስከበረ በመሆኑ እና በቀጣይ ወደ ዋና ምርት ሲገባ ሊያስከትለው የሚችል የኬሚካል ዝቃጭ በአካባቢ ስነምህዳር ላይ የሚያስከትለው ጉዳት እንዲሁም ድርጂቱ ወደ ስፍራው ሲገባ ለህዝቡ ቃል የገባውን የመሰረተ ልማት ለመስራት ባለመፈፀሙ በአካባቢው ሹማምንት ካልሆነ በስተቀር በነዋሪው ህዝብ የተጠላ የማይወደድ ድርጂት ለመሆን በቅቷል። በዚህ ሳቢያ ሌላ ጥቃት ሊደርስብን ይችላል በሚል በድርጂቱ በቁፋሮም ይሁን በስፋራው ላብራቶሪ ላይ የሚሰሩ ሰወች የተፈጠረው መረበሽና ውጥረት የጨመረ ሲሆን ጥበቃ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል።

 የአርበኞቹ ልጅ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.