በአምቦ ፣ጊንጪ ፣ወሊሶ ፣ ጀልዱ ፤ ዶዶላ …መሰል ዙሪያ አካባቢወች ህዝባዊ አመፁ እና የስራ ማቆም አድማው በስፋት ተጠናክሮ እየተካሄደ ነው

Standard

ትግሉ ተቀጣጥሏል ፤ ህዝባዊ ጥሪ ቀርቧል የአምናው አልበጀንም ፤ ሁሉም በአንድነት ይነሳ !!
በአምቦ ፣ጊንጪ ፣ወሊሶ ፣ ጀልዱ ፤ ዶዶላ …መሰል ዙሪያ አካባቢወች ህዝባዊ አመፁ እና የስራ ማቆም አድማው በስፋት ተጠናክሮ እየተካሄደባቸው ያሉ ከተሞች ናቸው።በኦሮሚያ ትክክለኛ ባልሆነ የግብር ተመና የተነሳው ህዝባዊ አመፅ እና አድማ እየተደረገ ነው ።በአምቦ አውቶብስ መናህሪያ ምንም አይነት እንቅስቃሴ አይታይም ፤ወደ ተለያዩ ቦታወች የሚሄዱ ቢኖሩም ትራንስፓርት ባለመኖሩ እንዲቆዩ ተገደዋል።በጊንጪ ከተማ ላይ ወደ አምቦ ፤ ጀልዱና ግንደበረት የሚወስደው መንገድ ዝግ ነው:: ከጊንጪ ወደ አንቦ ትራንስፓርት የለም። ሱቆች ዝግ ናቸው።ባንኮች በተጨማሪ ልዩ ወታደሮች እየተጠበቁ ነው።ሁሉም ነገር ዝግ ነው ።በከተማዋ ወጣቶች ተሰባስበው ቁጣቸውን እየገለፁ ሲሆን በሌላ በኩል የፌደራል ፖሊሶች ከተማዋን አንዳንድ ቦታወች ይሯሯጣሉ ።ህዝባዊ ጥያቄን በአፈሙዝ ለምልፈን እየተንቀሳቀሰ ያለው እና አንድ እግሩ መቃብር ውስጥ የገባው የህወሓት ቡድን ወጣቶቹን ለማስቆም የሀይል እርምጃ ለመውሰድ አሰፍስፈዋል።በዶዶላ ከተማ በተመሳሳይ ውጥረት አለ። ህዝባዊ ቁጣው ፈንድቷል። የወያኔ ወንበዴ ቡድን በተለያዩ ተሽከርካሪወች ወደ ኦሮሚያ ከተሞች ተጨማሪ ወታደራዊ ሃይል እያስገባ ነው።
ህዝብ ምንጊዜም ያሸንፉል!!

© Asegid Tamene

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.