“የሚያብረቀርቅ ሁሉ ወርቅ አይደለም”(ጉዱ ካሳ)

Standard

የወያኔ መንፈራገጥ በመጠንም በብዛትም ጨምሯል። የጭንቀት መገለጫው ብዙ ነው። ጭንቀት ሲጨምር ተፈጥሯዊው ራስን የማዳን ክስተቶች ይጨምራሉ። እነዚህም ማምልጥ፥ መጋፈጥ ወይም መፍጠጥ (flight, fight or freeze) የሚባሉት ከሰው ልጅ ግንዛቤ ውጭ በሚደረገውና በሰውነታችን ውስጥ በሚመነጩ ሆርሞኖች የሚከናወኑ ናቸው። ወያኔ እየተጋፈጠም እያፈጠጠም ባለበት ሁኔታ ሌሎች ተጨማሪ የማስመሰያ ዘዴዎችንም ይጠቀማል። “ያዛኝ ቅቤ አንጓች” እንደሚባለው ለኢትዮጵያ ህዝብ ተቆርቋሪ መስለው በየማህበራዊ መገናኛው የተሰገሰጉ ወስላታዎች ቁጥር የመጨመሩ ምክንያት ይሄው የወያኔ የጭንቀት ውጤት መሆኑ ነው። በቅርቡ ለትዝብት ከቀረቡ ማስመሰያዎች ብዙዎቹ በአማራ ስም የተደረደሩ የወያኔ አፈቀላጤዎች ናቸው። አላማቸው ግልፅ ነው። ያሰማራቸውን የወያኔን ወንጀልና የጥፋት ተግባር መሸፋፈን፥ የነፃነት ታጋዮችን ስም ጥላሸት በመቀባት ብዥታን መፍጠር፥ ውሸቶችን በመፈብረክ በበሬ ወለደ ቅጥፈታቸው በነፃነት ታጋዮች ውስጥ ልዩነት ያለ ለማስመሰል መሞከር፥ ሌሎችንም የወረዱ እና የትውልዱን የአስተሳሰብ የእድገት ደረጃ የማይመጥኑ ትርኪብርኪ ፅሁፎችን በመርጨት ወያኔ የጣለባቸውን አደራ መወጣት ነው።
እውነት በጊዜና በሁኔታ አይናወጥም። እውነት ሁሌም እውነት ነው። የወያኔ ስርዓት ሰው በላ ነው። የወያኔ ስርዓት ዘረኝነትን ያስፋፋ፥ የንፁሃንን ህይወት ያጠፋ፥ የሀገርን ልዑዋላዊነት ያስደፈረ፥ የጥቂት ዘረኞችና ጨካኞች ስብስብ ነው። ይህም በመሆኑ ሊወገድ ይገባል። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ለዘመኑ በሚመጥን የአስተዳደር ስርዓት መመራት፥ የሀገራቸውና የቀያቸው ባላቤትነትን የሚያረጋግጥ የራሳቸው ስራ የሆነ ስርዓት ባላቤት ሊሆኑ ግድ ይላል። ይህንን ለማረጋገጥ ነው የነፃነት ሀይሎች እየታገሉ ያሉት። በርግጥ የሀገራችን ጉዳይ ያገባናል የምንል ከሆነ፥ እየወደሞች ያላችው ኢትዮጵያ ካሳሰበችን፥ ያለወንጀላቸው በየማጎሪያ ቤቶቹ ጥፍራቼው እየተነቀለ ያለው ንፁሃን ዜጎች ካስቆጨን፥በርግጥም እንደሰው የማሰባችን ነገር ከ’ኛ ጋር ከሆነ፥ በፍፁም ወያኔን በአንድነት ልንታገለው ይገባል። ግልፅ አቋም ሊኖረን ይገባል። ከነፈሰው መንፈሳችንን ገትተን፥ የሚያብረቀርቁትን ከወርቅ ለይተን፥ ሙሉ ክንዳችንን ወያኔ ላይ ማሳረፍ ይኖርብናል። 
ኢትዮጵያ በተባበረ የልጆቿ ክንድ ነፃ ትወጣለች!

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.