የግብር ጭማሪውን ተከትሎ የተነሳው የተቃውሞ አድማ አድማሱን በማስፋ እየቀጠለ መሁኑ ታወቀ

Standard

ከፍተኛ የግብር ጭማሪን ተከትሎ የተጠራው የተቃውሞ አድማ በበርካታ የኦሮሚያ አካባቢዎች እንደቀጠለ ነው። በሻሸመኔ፡ መንዲ፡ ሆለታ፡ባሌ እና በሌሎች የኦሮሚያ አካባቢዎች የአድማ ተቃውሞ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የንግድ ተቋማት ዝግ ሲሆኑ የትራንስፖርት አገልግሎትም ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል። የአድማ ተቃውሞ አድማሱን እያሰፋ በተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች እንደቀጠለ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ኮልፌ፡ ዘነበወርቅና ሳሪስ የሚገኙ ሱቆች አድማውን ተቀላቅለው ሊዘጉ ችለዋል፡፡ ከፍተኛ የግብር ጭማሪን ተከትሎ የተቀሰቀሰው የአድማ ተቃውሞ ወደ ሌላ አይነት የአመጽ ተቃውሞ ሊያመራ ይችላል በሚል እየተነገረ ይገኛል። ወያኔም ይሄን ተቃውሞ በመፍራቱና በመደናገጡ በሻሸመኔና በመንዲ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የመከላከያ ሰራዊት በከተሞች ውስጥ ማሰማራቱን ተከትሎ ከፍተኛ ውጥረት እንዳለ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች አድማው ላይ በተሳተፉ የንግድ ሱቆች ላይ የማሸግ ተግባር እየተፈጸመ እንደሆነ ታውቋል። ይህንን ተከትሎ የአድማው እንቅስቃሴ ወደ አመጽ ሊያመራ ይችላል በማለት መረጃውን የሚያደርሱን ምንጮቻችን ገልፀዋል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.