የቀጣይ አገር አቀፍ አድማ ማድረጊያ ሁለት ቀናት ታወቁ

Standard

በቀጣይ አመት ማለትም 2010 ከመሥከረም አንድ ጀምሮ የነጻነት የግፍ ማብቂያ የዘረኝነት መጥፊያ የትግል ጫፍ መያዣ የወገን ለወገን መጠባበቂያ የህወአታዊያን መቀበሪያ አመት ነው። በመሆኑም እንቁጣጣሽን በክብር እናከብርና ከመሥከረም 02/2010 እስከ መሥከረም 04/2010 ድረስ ለሁለት ቀናት የሚቆይ የስራ ማቆምና የነጻነት ቀን መጀመሪያ ተደርጓል።

በመሆኑም በመላው ኢትዮጵያ በዘር በቀለም በሀይማኖት በጎሣ ሳንለያይ በመላው ኢትዮጵያ ሁለቱን ቀናት ህወአታዊያንን እጅግ እንደምንጠላቸው መላቀቅ እንደምንፈልግ እጅግ እንደመረረን ነጻነት እንደምንፈልግ። በሰላም አገራችን ካልለቀቁ በየትኛውም አማራጭ ልንፋለማቸው እንደተዘጋጄን የምናሣይባቸው ቀናት ይሆናሉ። በመሆኑም ከመሥከረም 02/2010 እስከ መሥከረም 04/2010 የአገር አቀፍ አድማው ቀናት ሆነው የተመረጡበት ዋናዎቹ ምክንያቶች

1ኛ. አገራዊ ዘመን መለወጫችን መስከረም አንድን በሠላም እናከብራለን ምክንያቱም አገራችንና ህዝባችን በምንም ሳንለያይ የምናከብርና የአገርና ህዝብን የሆነ ሁሉ የምንወድ የምናከብር መሆናችን ለማሣየትና ለህወአታዊያን ለማስተማር ነው።

2ኛ. እኛ ኢትዮጵያዊያን ብዙ ሆነን በአንድነት ጠላቶቻችንን ለመገርሰስ ስንንቀሳቀስ እንደዛሬ ድል ያለ ግብዣ ይደረግ እንደነበር ለማሥታወስ ነው። እኛም ህወአትን ያህል የአገር የህዝብ ጠላት በአዲሡ አመት ለመፋለም መዘጋጀታችን ከመዘጋጄት በላይም በተግባር መጀመራችንን ለማሣየት ነው።

3ኛ. ልብ በሉ መሥከረም አንድ የዘመን መለወጫን በሰላም ማክበራችን 2010ን መልካም የትግል የነጻነት የፍትህ የእኩልነት አመት ይሆንልን ዘንድ ለነጻነት መቁረጣችንን ለየትኛውም ትግል መዘጋጀታችንን እንደአባቶቻችን ለማብሰር የነጻነት አመታችን ርዕሰ መሆኑን ለማሣየት ነው። ልብ በሉ አባቶቻችን ጠላትን ድል ሊመቱ ሲነሡ ነገ ሊነሡ እንደ ዛሬ በዋዜማው ቀኑን ፌሽታ በፌሽታ አድርገውትም አልነበር እኛ ልጆቻቼውም ይህን በቆራጥነት ለመተግበር መዘጋጄታችንን ለማስመልከት ነው።

በመሆኑም ከመሥከረም ሁለት/2010 እ.ኢ.አ ጀምሮ ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ህዝባዊ ትግሏን የምትጀምር ይሆናል። ይህ ተቃውሞ ለሁለት ቀናት ብቻ የሚደረግ ሲሆን መላው ኢትዮጵያዊ ከትግራይ እስከ ሞያሌ ከምዕራብ እስከ ምስራቅ ከአማራ እስከ ኦሮሚያ ከደቡብ እስከ አፋር ከሶማሌ እስከ ጋምቤላ ከቤንሻንጉል እስከ የትኛውም የኢትዮጵያ ጫፍ ከገበሬ እስከ ከተሜ የሚሣተፍበት ነው።

ልብ እንበል በዚህ አገራዊ የሁለት ቀን አድማ አለመሣተፍ ከህወአታዊያን ጎን መሠለፍ ብቻ ሳይሆን ከህወአት በላይ ጠላታችን መሆን ነው። ዋጋም ያስከፍላል። በአዲሡ ዘመን መለወጫ ቀን የጎዳና ተዳዳሪ ወገኖቻችን የኔቢጤን ድሀ ወገኖቻችን የምንችለውን ያህል በመጋበዝ አዲሡን ዘመን የጋራችን ስለመሆኑ በመጋበዝ በማካፈል ለሁለቱ ቀናት እንዳይቸገሩ እናድርግ።

ሙሉውን ጥሪ #ESAT #OMN #ABAYMEDIA #SOCIALMEDIA ላይና በምርጥ ነጻነት ናፋቂ ኢትዮጵያዊያን የሚካሄድ ይሆናል። ይህ ጥሪ አገራዊና ህዝባዊ ጥሪ ነውና መተላለፍ ከፍ ያለ ዋጋ ያሥከፍላል።

Mengistu Welyu
Advertisements

በኦሮሚያ በቀጣዩ ሳምንት አጠቃላይ የስራ ማቆም አድማና ተቃውሞ መጠራቱ ታወቀ (ኢሳት ዜና –ነሐሴ 12/2009)

Standard

በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የሚገኙ ወጣቶች በህቡዕ በመንቀሳቀስ በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች በሚቀጥለው ሳምንት ረቡእ ጀምሮ ለ5ቀናት የሚቆይ አድማ ለማድረግ ዝግጅት ላይ መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።በሌላ በኩል በአማራ ክልል በተለይም ባህርዳርን ጨምሮ በምስራቅና ምዕራብ ጎጃም ሌላ ዙር አድማና የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሊደረግ እንደሚችል እየተነገረ ነው።ለነሃሴ 10 ተራዝሞ በነበረው የግብር መክፈያ ቀነ ገደብ አብዛኛው የንግዱ ማህብረሰብ ባለመክፈሉ በአንዳንድ አካባቢዎች ውጥረት መንገሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።ሱቆች እየታሸጉ ነው። የነጋዴዎች እስርም ቀጥሏል።ከሚቀጥለው ረቡእ ጀምሮ ለ5 ቀናት የሚቆይ አድማ በመላው ኦሮሚያ የተጠራው የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፣በሕዝቡ ላይ ያለአግባብ የተጫነውን ግብር በመቃወምና ከሶማሌ ክልል ጋር በተያያዘ በተነሳው የወሰን ግጭት የተገደሉትን ለማስታውስ ነው።ከዚህ ቀደም የነበሩ አድማዎች በውስን ቦታዎች የሚካሄዱና የተዘበራረቁ ነበሩ።በተለይም በአምቦ በወሊሶና በተወሰኑ የኦሮሚያ አካባቢዎች ከግብርና ከፖለቲካ እስረኞች ጋር በተያያዘ የተካሄዱ አድማዎች መጠነኛ ግጭቶች ከደረሱ በኋላ በአገዛዙ ታጣቂዎች የሃይል እርምጃ ለማፈን ሙከራ ሲካሄድባቸው የነበሩ ናቸው።አሁን ከመጪው ረቡእ ጀምሮ በኦሮሚያ ቄሮዎች ወይም ወጣት ስብስቦች የተጠራው አድማ ግን ለ5 ቀናት በኦሮሚያ እንደሚካሄድ ያወጡት መግለጫ ያመለክታል።በዚሁም ሁሉም የንግድ መደብሮች ተሽከርካሪዎችና የሕዝብ ማመላለሻዎች ከስራ ውጭ እንደሚሆኑ ጥሪ ቀርቧል።የኦሮሚያ ወጣቶች የጠሩት አድማ ዶክተር መረራ ጉዲና፣አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አመራር አባላት ከእስር እንዲፈቱ የሚጠይቅ ነው ተብሏል።በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ አምስት አካባቢዎች በድንበር ይገባኛል ጥያቄ ሰበብ በሕወሃት አገዛዝ ጣልቃገብነት የሚካሄዱ ግጭቶችም ወጣቶቹን እንዳሳሰባቸው ወጣቶቹ ገልጸዋል።እናም በሶማሌ ልዩ ሃይል አባላት የተገደሉ የኦሮሚያ ነዋሪዎችን ለማሰብ ይህ አድማ መጠራቱን ቄሮዎቹ አስታውቀዋል።አድማውን የጠሩት የኦሮሚያ ወጣቶች ክልሉ ይህን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ በሚሞክሩ ማናቸውም ሃይሎች ላይ እርምጃ እንደሚወስዱም አስጠንቅቀዋል።በአድማው ወቅት ተሽከርካሪዎቻቸውን የሚያንቀሳቅሱ ሁሉ ለሚገጥማቸው ችግር ሐላፊነቱን እንደሚወስዱም ነው ያሳሰቡት።ይህ በእንዲህ እንዳለም በአማራ ክልል ከግብር ጋር በተያያዘ ያለው ተቃውሞ ከፍተኛ ውጥረት እየፈጠረ መሆኑ ታውቋል።በአማራ ክልል የግብር መክፈያው ጊዜ ነሐሴ 1/2009 ከተጠናቀቀ በኋላ ግማሾቹ የንግድ መደብሮቻቸውን በመዝጋት ሲጠፉ ሌሎቹ ደግሞ ሳትከፍሉ ቆይታችኋል በሚል ነጋዴዎችን እያንገላቷቸው መሆኑ ታውቋል።በባህር ዳር ያልተጠበቀ ፍተሻና የሰራዊት ከበባ እንደነበርም ተገልጿል።

ሎተሪ በመግዛት ወገንህን ለመግደል የሚውል ጥይት አትግዛ

Standard

ወያኔ ሀገሪጔቷን ሙሉ በሙሉ ከተቆጣጠረ በኋላ አንዳንድ ከወሰዳችው እርምጃዎች ብዙም ያለተሰማ እና ያልታወቀ ነገር ነበር፡፡ ነገር ግን በቅርቡ በመኣዛ ብሩ መድረክ ላይ ለአንድ ነባር ጋዜጤኛ በቀረበለት ቃለ መጠይቅ የተነገረው አንድ የወያኔ እርምጃ ፈንተው ያደረገልን የወያኔ ድርጊት አለ፡፡ ይህ ድርጊት ወያኔ ነገሮችን የሚመለከትበት የሚመዝነብት ጉዳይ መሰረቱ ምን እንደሆነ በጉልህ ያሳያል፡፡ ይህም ወያኔ ድርጊት በብሄራዌ ሎተሪ ስራተኟች ላይ የወሰደው እርምጃ እና እርምጃውን ለመውሰድ ያቀረበው ምክንያት ነው፡፡ ወያኔ አንዳንድ የብሄራዊ ሎተሪ ስራተኞችን ሲያባርር ያቀረበው ምክንያት ወይም ክስ እንዲህ የሚል ነው ፡ ሎተሪ እየሸጣችሁ ደርግ እኛን የሚገልበትን ጥይት ለመግዛት ገንዝብ ታሰባሰቡ ነበር የሚል ነው፡፡ የሚገርም እይታ ነው፡፡የእዚህ አጭር ፅሁፍ ላይ ለማንሳት ወይም ብልጭ ለማድረግ የምፈልገው ቁም ነገር ወያኔ ለምን አባረረ ምክንያቱ ትክክል ነው ወይም ትክክል አይደለም የሚል የመከራከሪያ ነጥብ ለማንሳት አይደለም፡፡ እንዲያውም ወያኔ በሰፈረበት ቁና የሚሰፈርበትን ቁና ሰፋ አድርጌ ለማሳየት ነው፡፡ ልብ ያለው ልብ ይበል ወያኔን በሰፈረበት ቁና ማስፈሪያው አሁን ነው፡፡ እንግዲህ ወያኔ በዘመነ ደረግ የብሄራዊ ሎተሪ ሽያጭ የሚገኝ ገንዘብ ለደርግ ጥይት መግዣ ዋለ ካለ የአሁኑስ የወያኔ መንግስት ከሎተሪ ሽያጭ የሚገኘውን ገንዘብ ወገንን ለመግደል ለጥይት መግዣ ስለ አለማዋሉ ምን ማረጋገጫ አለ? መልሱ ባጭሩ ምንም ማረጋገጫ የለም፡፡ ወያኔ መሳሪያ ገዛበትም አልገዛበትም የተሰበሰበው ገንዝብ ስርአቱን እድሜ ማራዘሚያ እንደ ሚያግልግል መጠራጠር ያለብን ግን አይመስለኝም፡፡በአጠቃላይ ሎተሪ ሁለት ገፅታዎች አሉት  አንደኛው የማይመለከትን ግን በፍቃደኝነት የምንከፍለው ግብር ነው ሁለተኛው ቁማር ነውእዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባን ነገር ቢኖር ሁለቱንም ነገሮች በፍቃደኝነት የምናደርገው መሆኑ ነው፡፡ ማንም ሰው ሎተሪ ባለመግዛቱ አይከሰስም አይታሰረም፡፡ ይህ ስውር ግብር እና ቁማር የምናከናውነው በፍቃድኝነት መሆኑ ነው፡፡ ያ ማለት ምን ማለት ነው ፡፡ያ ማለት በፍቃደኝነት የምንገዛበትን የምንገደልበትን የምንታሰርበትን የምንዘረፍነትን የገንዘብ ምንጭ ለማይወክለን አስተዳደር መገበር ማለት ነው፡፡ ይህ የወያኔ የሰፈረነት ቁና ነው፡፡የወያኔን ስነ ልቦና ተከትለን ከሄድን ዛሬ ማናቸውም ነፃነቱን ፋላጊ ቀናዊ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ሎተሪ መግዛት የለበትም ማለት ነው፡፡ዛሬ ብሔራዊ ሎተሪ ከፍተኛ እና የተለያዩ የሎተሪ አይነቶች በማዘጋጀት ከህዝቡ ላይ ብዛት ያለው ገንዘብ ለመሰብሰብ በመዘጋጀት ላይ ነው ፡፡ ያ ማለት ምን ማለት ነው፡፡ ሎተሪውን ገዛነው ማለት ምን ማለት፡፡

1. ህዝቡ በግፍ በበደል የሚገዛበትን ገንዘብ በፍቃደኝነት መስጠት መገበር ማለት ነው፡፡
2. ህዝቡ በግፍ የሚገደልበትን ጥይት መግዣ ገንዘብ በፍቃደኝነት መገበር ማለት ነው፡፡

3. ህዝቡ ያለ ፍርድ የሚንታሰርበትን እስር ቤት ለማስተዳደር በፍቃደኛነት መገበር ማለት ነው

4. ያለ ፍርድ ሰባዊ መብታችን ተገፎ በእስር ቤት የምንገረፍበትን ገንዝብ ለገራፊዎቻችን በፍቃደኝነት መገበር ማለት ነው

5. ያ ማለት እውነት ተሸፍኖ ሀሰት ለሚነዛው የዜና አውታር ገንዝብ በፍቃደኝነት መገበር ማለት ነው

6. ባአጠቃላይ ሰቆቃ አራሳችን ላይ እንዲረዝም በፍቃደኝነት ማገዝ ማለት ነው

ድንገት አንዳድ ሰዎች ስለ ሎተሪ አዞሪዎች ኑሮ ሁኔታ ወይም ገቢ ሊያሳስባችው ይችሉ ይሆናል፡፡ ነጥቡ ፍትህ ባለበት ሀገር እውነትነት ሊኖረው ይችላል፡፡ ነገር ግን ዛሬ በአዲስ አበባ የሎተሪ አዞሪዋችን ማንነት ልብ ብለን ብንመለከት አንድ ነገር ልብ ልንል እችላለን፡፡ያም የዛሬ ሎተሪ አዞሪዋች የትግራይ ልጆች ሳይሆኑ ከሌላ ብሄረስብ የመጡ ከመደራቸው በድህነት ተፈናቅለው በትምህርት ተኮትኩተው በሚያድጉበት ለጋ እድሜቸው ላይ ሎተሪ አዞሪ እንዲሆኑ የተፈረደባችው የወያኔ የግፍ አገዛዝ በተዘዋዋሪ መንገድ የደረሰባችው የዘመናችን ሰለባዎች ናችው፡፡ስለሆነም ሎተሪ በመግዛት ጭቆናን በደልን እና የግፍ አገዛዝን አናግዝ፡፡ ልጆቻችንም ወደ ትምህርት ገበታችው ይግቡ፡፡ ቁማርም መጫወት በሁለቱም የእምነት ቤቶች ሀጥያት ወይም ሀራም ነው፡፡
ጥይት በራስህ ገንዘብ አትግዛ፡፡

በቀኝ ገዥነት ላይ ንቀትን የደረበው ህወሀት

Standard

ህወሀት ከምስረታው ማግስት ጀምሮ የአጎራባች ህዝቦች መሬቶችን ቀምቼ የታላቋን ትግራይ ሉአላዊ መንግስት እመሰርታለሁ የሚል እቅድ አዘጋጅቶ ወደ ጫካ የገባ ድርጅት እንደሆነ ይታወቃል። ጉልበቱን በመጠቀምም ያለቅድመ ሁኔታ መገንጠል የሚያስችል ያልተለመደ አንቀጽ በህገ መንግስቱ እንዲካተት አድርጎአል። የእቅዱ ቀሪ ክፍል የሆነውን መሬትና ሀብት የማሰባሰብ ስራን ያለከልካይ ከተያያዘው እነሆ 26 አመታት ተቆጥረዋል። ለአለም አቀፍ ንግድ የሚያግዙ መግቢያና መውጫ አማራጮቹን የማስፋት እንዲሁም ለምግብ ምርት ማምረቻ የሚሆኑ የእርሻ መሬቶች ወደ ክልሉ የማጠቃለል ስራዎች በዚህ የእቅዱ ክፍል ውስጥ ይገኛሉ። ትመጣለች ተብላ ለምትጠበቀው ሉአላዊ ትግራይ የኢንዱስትሪ ልማት መሰረት ለመጣል ሲል ገና በልቶ ካልጠገበው የኢትዮጵያ ህዝብ ጉሮሮ ላይ ካፒታልና ጥሬ እቃ ይዘርፋል፤ ይነጥቃልም።። ይህ እኔና አንተ/ቺ በእለት እለት ህይወታችን የምናየውና የሚሰማን ጸሀይ የሞቀው ሀቅ ነው። ማሳዎች ይቅረቡ ለሚል አካል እስኪ ምልከታችንን መረጃ አዘል እናድርገው፡፡


ህወሀት አባሎቹን እያበረታታ ሀብት እንዲያከማቹ ከሚያደርግበት መንገድ መካከል አንዱ ለሌሎች ኢትዮጳውያን የጤፍ ወንፊት የሆነ የመንግስት ባንኮች የብድር አሰጣጥ ስርኣትን ለአባላቶቹ የአሸዋ ወንፊት እንዲሆን መስራቱ አንዱ ነው። ከስምንት ወር በፊት በጋምቤላ ክልል በእርሻ ኢንቨስትመንት ችግሮች መወሳሰብ ተከትሎ መደበቅ የማይቻልበት ደረጃ በመድረሱ በአባላቱ የደረሰ ብክነትና ዘረፋን አምኖ ለመቀበል ተገዶ ነበር። በጉዳዩ ዙሪያ የቀረበው ሪፖርት እንዳመለከተው የህወሀት ካድሬዎችና ጭፍራዎች የክልሉን ለም መሬት የቀኝ ገዥ ወረራ በመሰለ መልኩ ዘምተው ተቀራምተውታል። መሬቱን ለማልማት በሚል ስምም መጠኑ በቢሊዮን ብሮች የሚቆጠር ገንዘብ በኢትዮጵያ ልማት ባንኩ ፕሬዝደንት በህውሃቱ ኢሳያስ ባህረ አመቻችነት በብድር ስም አውጥተው ተከፋፍለውታል። ከዚህ እንደምንረዳው ትንንሽ ሌቦች ላይ ከበሮ የሚያስደልቀው ህወሀት/ኢህአዴግ በቢሊዮን የሚቆጠር ብር በግብርና ልማት ስም ያለ ማስያዣ ወስደው በየከተማው ህንጻ የሚያቆሙ አሊያም የገንዘቡን አድራሻ የሚያጠፉ አባሎቹ እንዲበረታቱ በዝምታ ሲንከባከብ መቆየቱን ይሆናል። በአንድ መሬት ላይ እስከ ሶስት ሰዎች ብድር እንዲወስዱ መደረጉም ማስረጃነቱን ያጠናክረዋል። በቤኒሻንጉል ግሙዝ፣ አፋር እና ደቡብ ኦሞ ያለው የግብርና ኢንቨስትመንት ታሪክ ከዚህ የተለየ እንደማይሆን የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። እንደ አንዳንድ ምንጮች ዘገባም ባለሃብት ተብዬ የትግራይ ተዋላጆች በቤኒሻንጉል ግሙዝ፣ አፋር እና ደቡብ ኦሞ ካለው መሬት ወሳጅ ባለሀብት አንጻር ሲታይ በትንሹ 75% በአንዳንድ ቦታዎች ደግሞ 90% ይደርሳሉ። የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ቤኒሻንጉል ግሙዝ ክልል ሰራተኛ በነበረበት ወቅት የተመለከተውም ሀቅም ነው። ይህም በሀገሩቱ ውስጥ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል የለም የሚለውን ጩሀታችንን ያረጋግጥልናል።

ሌላው ህወሀት ለታላቂቱ የትግራይ መንግስት ምስረታ እየሰራባቸው ከሚገኝበት ዘርፎች መካከል ከአጎራባች ዞኖች መሬት እየነጠቀ አዲስ ካርታ ማተሙ ይሆናል። ከተነጣቂዎቹ ውስጥ ሰሜንና ምህራብ ጎንደር እንዲሁም የሰሜን ወሎ አካባቢዎችን መጥቀስ ይቻላል። ከድርጅቱ ሰዎች አንደበት አዳልጦአቸው ከሚሰሙ መረጃዎች በመነሳት መሬት የማሰባሰቡ ስራ ገና እንዳልተጠናቀቀና ሌሎች ይገባናል የሚሏቸው ቦታዎች እንዳሉም አይተናል። የቅርቡን ብናይ የፍትህ ተሟጋች ነኝ እያሉ ከበሮ ከሚደልቁ ነገር ግን የህወሀት ፈላጭ ቆራጭነት ማብቃት ላይ ሲደርሱ ወገቤን ከሚሉት ጸሃፊያን መካከል አቶ ዳንኤል ብርሀነ በፌስ ቡክ ገጻቸው ያሰፈሩትን መልእክት መመልከት ይቻላል። ጎንደሬ ትግራይነቱን የሚቀበልበት ሁኔታ ይኖር ይሆንን ሲሉ በፈረንጆቹ ኦገስት 11̦ ቀን 2017 በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ጥያቄ አስፍረዋል። ይሄም እስካሁን ከተነጠቁት የአማራና አፋር መሬቶች ውጪ ሌላም ያልረካ ፍላጎት እንዳላቸው ያመለክታል።

መንግስት ይሁን ነጋዴ ባልለየለት መልኩ ከሀገሪቱ ሀብት በመቀማት የንግድ ድርጅቶችን ማስፋት ሌላው የህወሀት ኢህአዴግ ባህርይ ነው። ሲጀመር በዘረፋ ሲቀጥልም በብድር ስም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገንዘብ እየዘረፈ የገነባቸው እነዚህ ግዙፍ የንግድና ኢንደስትሪ ተቋማት ፍትሀዊ ባልሆነ የንግድ ውድድር ተሰማርተው ስለሚገኙ በጥቂት አመታት ውስጥ ከሚሊየርነት ወደ ቢሊየነት ተሸጋግረዋል። በሌላ በኩል የተራ አባላቱን የስነልቦናና የኢኮኖሚ አቅም በማሳደግ ላይ የሰራው ስራም ቀላል የሚባል አይደለም። በሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች የስነልቦናና የኢኮኖሚ ውድቀትና ዋጋ መክፈል ማለታችን ነው። በአንድ በኩል በኩል ለአባላቱ የአዲስ አበባን መሬት እና አነስተኛ ኪራይ የሚከፈልባቸው የመንግስት ቤቶች በማደል መጠመዱን ማንሳት ያስፈልጋል። ለነገዋ ትግራይ የእውቀትና አሰራር ሽግግር እንዲሁም ከጠቅላይነት በሽታው መነሻነት አባላቱ የስራ አመራር እውቀትና ክህሎታቸውን ኣያወደሙ አንዲያሳድጉ በፌደራልና አዲስ አበባ መስተዳድር ተቋማት ውስጥ ሰግስጎአል።

እስቲ በአካባቢዎቻችሁ ያሉ ወይም የነበሩ ልዩ ልዩ የተሻለ ጥቅማ ጥቅም ይገኝባቸዋል ተብሎ የሚታመኑ ተቋማትና አደረጃጀቶችን አስቡ። ማነው እየመራቸውና እየተጠቀመ ያለው? ከእድር ሊቀመንበር ጀምሩ፣ የቤተክርስትያን አስተዳዳሪዎች፡ የሙያ ማህበራት የሴቶችና እና ወጣቶች ማህበራት አመራሮች፣ የአረጋውያን፡ የልማትና ግብረሰናይ ድርጅቶች መሪዎች፣ ወጣት አስመጪና ላኪዎች እና ሌሎች ዘርፎችም በደጋፊዎቹ እንዲዋጡ ቀጥተኛ ባልሆኑ ስልቶች እየሰራ ይገኛል። ነባር አመራሮቹ እንዲለቁ በመግፋት የራሱን አባላት ወደ ቦታው እንዲደርሱ በተቀናጀ መልኩ በመርዳት። በ push and pull እስትራቴጂ ማለት ነው። አየር መንገድ፡ ብሄራዊ ደህንነት፣ መከላከያ ሙሉ በሙሉ፣ የመከላከያ ብረታ ብረት ኮርፖሬሽን፣ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ተቋማት፣ የብሮድካስትና መረጃ ደህንነት መስሪያ ቤቶች፣ የግብር እና ግሙሩክ፣ የወሳኝ ተቋማት የቦርድ ሰብሳቢዎች እነማን ናቸው? ይህ በሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች ዋጋ መክፈል የሚያካሂደውን የቀኝ ገዥነት ተግባር ሳያንሰው ነጻ ወጥታችሁአል፣ በዲሞክራሲ መንገድ ላይ ናችሁ ማለቱ ምን ይሉታል? መልሱ አንድ ነው። የንቀት ጥግ።

በያሬድ አውግቸው

ተሰምቶ የማይታወቅ ሙስና

Standard

ከህውሓት ባለስልጣና ቁጥር አንድ የኢትዮጵያን ንግድ ባንክ ገንዘብ የበዘበዘ ዶ/ር አርከበ እቁባይ ይህ ሰው በፈለገው ጊዜ ወደ ውጭ የሚወጣ ሲሆን ባለ 5 ኮከብ ሆቴል ከመያዙም ባሻገር የህዝብን ገንዘብ ያለ አስፈላጊ የሚበዘብዝ ነው ።ለዚህ ገንዘብ ወጭ ብዝበዛ ተባባሪ ደግሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ በቃሉ ዘለቀ ናቸው ።አቶ በቃሉ ዘለቀ ይህን ለሚያደርገው ከህውሓት ባለስልጣናት ልዩ ጥቅም እንደሚያገኙ ተነግሯል ።በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና ተዋናዮች ፈላጭ ቆራጮች ደግሞ አቶ አባይ ፅሃዬ እና ወንድማቸው አቶ ልዑል ፅሃዬ ናቸው ።ዶ/ር አርከበ እቁባይ በሳምንት 100,000 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ይበዘብዛሉ ።ወደ ውጭ በሚወጡበት ጊዜ በቪዛ ካርድ 100,000 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የሚሞላላቸው ሲሆን ይህም በመዝገብ ላይ እንደማይፃፍ ነው እየተነገር ያለው ።

Source : activist

ነሃሴ ፩ የሰማዕታት ቀን !!

Standard

ህዝቤ ሆይ አምርሯል ፤ ህወሓት/ወያኔም በፍርሃት ተወጥሯል።በመላው ኢትዩጲያ የስልክ መልዕክት SMS እየተላለፈ ይገኛል።” ነገ ሰኞ የሞቱ ስማዕታት ወንድሞቻችንን ከቤት ባለመውጣት እናስባቸው::የሞቱት ስለ እኛ ነው::
ለ 5 ወዳጅወ በመላክ ተቃውሞውን ይቀላቀሉ:: “የሚል መልዕክት የያዘ SMS እየተሰራጨ ይገኛል። መልዕክቱ በእጂ ስልኩ የደረሰው ለ5 ወዳጆቹ በማሰራጨት ለተግባራዊነቱ እየተረባረቡ ይገኛል።የህወሓት/ወያኔ ወንበዴ ቡድን በባህርዳር ከተማ በህዕቡ ቡድን የቦንብ ጥቃት ይደርስብኛል በሚል በፍርሃት ተውጥሮ ከልዩ ሃይል አድማ በታኝ ፣ የፌድራል ፖሊስ ፣ መከላከያ እና የአካባቢ ፖሊሶች ፣ የደህንነት ጆሮ ጠቢወች እርስ በርስ እየተርመሰመሱ ይገኛል።
የባህርዳር ህዝብ እና ዙሪያ አካባቢወች ነገ በስራ ማቆም ከቤት ባለመውጣት በፍፁም ሀዘን ለማክበር ዝግጂቱን አጠናቋል።በነሃሴ 1 /2008 ዓ.ም እና በቀጣይ ቀናት በባህርዳር ኮበል ኢንዱስትሪ ፣ በባህርዳር የተለያዩ ስፍራወች በአጋዚ አልሞ ተኳሾች ሰማዕትነትን የተቀበሉ ወንድሞቻችንን የቀብር ስነስርዓታቸው ከባህርዳር ውጭ በትውልድ ስፍራቸው ለተፈፀሙ ወገኖች የፍትሃት ፀሎት ፣የአንደኛ አመት ሙት አመት ነፍሳቸውን ይማር ለማለት በቤተሰቦቻቸው እና በቅርብ ወዳጃቸው እንዲሁም በመላ ህዝቡ በየቤተክርስቲያኑ የፀሎት ስነስርዓት እንደሚደረግ ታውቋል። በተለይ በባህርዳር ድባንቄ መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን ብዛት ያላቸው ወንድሞቻችን አፀደ ስጋቸው ያረፈበት በመሆኑ ብዛት ያለው ህዝብ ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል። በጢስ አባይ ከተማ ወጣቶቹ እና መላ ህዝብ በፍፁም ሀዘን ወንድሞቻችንን ለማሰብ እንደተዘጋጁ ታውቋል።
ነሃሴ ፩ የሰማዕታት ቀን !!

መቼም አንረሳውም !!

© እንቅዩጳዝዩን የአርበኞቹ ልጂ

መለስ ዜናዊ ለኢትዮጲያ ምንም አልሰራም የምትሉ ተቃዋሚዎች ሁሉ ሳነብ ካገኘሁት የመለስ ዜናው ትልልቅ ስኬቶች ላካፍላችሁ

Standard

1ኛ. ይች ሀገር ከ80 በላይ ብሄር ቤሄረሰቦች ያሉዋት ሲሆን አቶ መለስ የመጡበት ግን ትግራይ ግን ወርቅ ዘር ናት ብለው ማመናቸውም/መናገራቸውም

2ኛ.ከኤርትራ ጋር በተደረገና እስካሁን ድረስ ምክንያቱ ባልታወቀ ጦርነት 70,000 ወጣቶችን እንዲያልቁ በማድረጋቸው

3ኛ. በዘመናት የታሪክ ሂደት ከስም ያልዘለለ ጥቅም አግኝቶ የማያውቀን የአምሀራን ህዝብ እንደ ጨቁዋኝና ገዥ አድርጎ
በማስጠላት በበደኖ በአርባጉጉ በነቀምት በጉራፈርዳ የዘር ፍጅት እንዲደረግበትና እንዲሰደድ በማድረጋቸው

4ኛ የኦሮሞ ፖለቲከኞችን ኦነግ በሚል ስም በመግደልና እስር ቤቱን በኦሮምኛ ተናጋሪ በመሙላታቸው

5ኛ. የሀገሪቱን የትምህርት ፖሊሲ በሀገሪቱ የዘመናዊ ትምህርት ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የማይረባና ትውልድን ገዳይ የሆነ የትምህርት ፖሊሲ እነዲሆን በማድረጋቸው

6ኛ. ኢትዮጵያውያንን በታሪካቸው አይተውት የማያውቁትን ለአረብ አገልጋይ ወይም ገረድ እንዲሆኑ በማድረጋቸው

7ኛ.የሀገሪቱን የመከላለከያ ሰራዊት በተለይም በከፍተኛ ማዕረግ ቦታዎች ላይ ከአምስተኛ ክፍል ያቁዋረጡ ሰዎችን ጀኔራል በማድረጋቸው

8ኛ. በኦርቶዶክስ ቤተክርቲያን ታሪክ ሽጉጥ የሚይዙ እንዲሁም ጠባብና ዘረኛ የሆኑ ፓትርያርክ በመሾማቸው

9ኛ. እስልምናን ለማጥፋት አህባሽ የሚባል አስተምህሮ በማምጣታቸው

10ኛ. ዜጎች በሀገራቸው መሬታቸው እየተነጠቀ ለባዕድ እንዲሰጥ በማድረግ የወጣቶች ተስፋ ስደት ብቻ እንዲሆን
ያደረጉ………….ብቻ የሳቸውን ስኬት ታሪክ ይዘግበው እንጅ ተዘርዝሮ አያልቅም…።

meles carton