ነሃሴ ፩ የሰማዕታት ቀን !!

Standard

ህዝቤ ሆይ አምርሯል ፤ ህወሓት/ወያኔም በፍርሃት ተወጥሯል።በመላው ኢትዩጲያ የስልክ መልዕክት SMS እየተላለፈ ይገኛል።” ነገ ሰኞ የሞቱ ስማዕታት ወንድሞቻችንን ከቤት ባለመውጣት እናስባቸው::የሞቱት ስለ እኛ ነው::
ለ 5 ወዳጅወ በመላክ ተቃውሞውን ይቀላቀሉ:: “የሚል መልዕክት የያዘ SMS እየተሰራጨ ይገኛል። መልዕክቱ በእጂ ስልኩ የደረሰው ለ5 ወዳጆቹ በማሰራጨት ለተግባራዊነቱ እየተረባረቡ ይገኛል።የህወሓት/ወያኔ ወንበዴ ቡድን በባህርዳር ከተማ በህዕቡ ቡድን የቦንብ ጥቃት ይደርስብኛል በሚል በፍርሃት ተውጥሮ ከልዩ ሃይል አድማ በታኝ ፣ የፌድራል ፖሊስ ፣ መከላከያ እና የአካባቢ ፖሊሶች ፣ የደህንነት ጆሮ ጠቢወች እርስ በርስ እየተርመሰመሱ ይገኛል።
የባህርዳር ህዝብ እና ዙሪያ አካባቢወች ነገ በስራ ማቆም ከቤት ባለመውጣት በፍፁም ሀዘን ለማክበር ዝግጂቱን አጠናቋል።በነሃሴ 1 /2008 ዓ.ም እና በቀጣይ ቀናት በባህርዳር ኮበል ኢንዱስትሪ ፣ በባህርዳር የተለያዩ ስፍራወች በአጋዚ አልሞ ተኳሾች ሰማዕትነትን የተቀበሉ ወንድሞቻችንን የቀብር ስነስርዓታቸው ከባህርዳር ውጭ በትውልድ ስፍራቸው ለተፈፀሙ ወገኖች የፍትሃት ፀሎት ፣የአንደኛ አመት ሙት አመት ነፍሳቸውን ይማር ለማለት በቤተሰቦቻቸው እና በቅርብ ወዳጃቸው እንዲሁም በመላ ህዝቡ በየቤተክርስቲያኑ የፀሎት ስነስርዓት እንደሚደረግ ታውቋል። በተለይ በባህርዳር ድባንቄ መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን ብዛት ያላቸው ወንድሞቻችን አፀደ ስጋቸው ያረፈበት በመሆኑ ብዛት ያለው ህዝብ ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል። በጢስ አባይ ከተማ ወጣቶቹ እና መላ ህዝብ በፍፁም ሀዘን ወንድሞቻችንን ለማሰብ እንደተዘጋጁ ታውቋል።
ነሃሴ ፩ የሰማዕታት ቀን !!

መቼም አንረሳውም !!

© እንቅዩጳዝዩን የአርበኞቹ ልጂ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.