ሎተሪ በመግዛት ወገንህን ለመግደል የሚውል ጥይት አትግዛ

Standard

ወያኔ ሀገሪጔቷን ሙሉ በሙሉ ከተቆጣጠረ በኋላ አንዳንድ ከወሰዳችው እርምጃዎች ብዙም ያለተሰማ እና ያልታወቀ ነገር ነበር፡፡ ነገር ግን በቅርቡ በመኣዛ ብሩ መድረክ ላይ ለአንድ ነባር ጋዜጤኛ በቀረበለት ቃለ መጠይቅ የተነገረው አንድ የወያኔ እርምጃ ፈንተው ያደረገልን የወያኔ ድርጊት አለ፡፡ ይህ ድርጊት ወያኔ ነገሮችን የሚመለከትበት የሚመዝነብት ጉዳይ መሰረቱ ምን እንደሆነ በጉልህ ያሳያል፡፡ ይህም ወያኔ ድርጊት በብሄራዌ ሎተሪ ስራተኟች ላይ የወሰደው እርምጃ እና እርምጃውን ለመውሰድ ያቀረበው ምክንያት ነው፡፡ ወያኔ አንዳንድ የብሄራዊ ሎተሪ ስራተኞችን ሲያባርር ያቀረበው ምክንያት ወይም ክስ እንዲህ የሚል ነው ፡ ሎተሪ እየሸጣችሁ ደርግ እኛን የሚገልበትን ጥይት ለመግዛት ገንዝብ ታሰባሰቡ ነበር የሚል ነው፡፡ የሚገርም እይታ ነው፡፡የእዚህ አጭር ፅሁፍ ላይ ለማንሳት ወይም ብልጭ ለማድረግ የምፈልገው ቁም ነገር ወያኔ ለምን አባረረ ምክንያቱ ትክክል ነው ወይም ትክክል አይደለም የሚል የመከራከሪያ ነጥብ ለማንሳት አይደለም፡፡ እንዲያውም ወያኔ በሰፈረበት ቁና የሚሰፈርበትን ቁና ሰፋ አድርጌ ለማሳየት ነው፡፡ ልብ ያለው ልብ ይበል ወያኔን በሰፈረበት ቁና ማስፈሪያው አሁን ነው፡፡ እንግዲህ ወያኔ በዘመነ ደረግ የብሄራዊ ሎተሪ ሽያጭ የሚገኝ ገንዘብ ለደርግ ጥይት መግዣ ዋለ ካለ የአሁኑስ የወያኔ መንግስት ከሎተሪ ሽያጭ የሚገኘውን ገንዘብ ወገንን ለመግደል ለጥይት መግዣ ስለ አለማዋሉ ምን ማረጋገጫ አለ? መልሱ ባጭሩ ምንም ማረጋገጫ የለም፡፡ ወያኔ መሳሪያ ገዛበትም አልገዛበትም የተሰበሰበው ገንዝብ ስርአቱን እድሜ ማራዘሚያ እንደ ሚያግልግል መጠራጠር ያለብን ግን አይመስለኝም፡፡በአጠቃላይ ሎተሪ ሁለት ገፅታዎች አሉት  አንደኛው የማይመለከትን ግን በፍቃደኝነት የምንከፍለው ግብር ነው ሁለተኛው ቁማር ነውእዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባን ነገር ቢኖር ሁለቱንም ነገሮች በፍቃደኝነት የምናደርገው መሆኑ ነው፡፡ ማንም ሰው ሎተሪ ባለመግዛቱ አይከሰስም አይታሰረም፡፡ ይህ ስውር ግብር እና ቁማር የምናከናውነው በፍቃድኝነት መሆኑ ነው፡፡ ያ ማለት ምን ማለት ነው ፡፡ያ ማለት በፍቃደኝነት የምንገዛበትን የምንገደልበትን የምንታሰርበትን የምንዘረፍነትን የገንዘብ ምንጭ ለማይወክለን አስተዳደር መገበር ማለት ነው፡፡ ይህ የወያኔ የሰፈረነት ቁና ነው፡፡የወያኔን ስነ ልቦና ተከትለን ከሄድን ዛሬ ማናቸውም ነፃነቱን ፋላጊ ቀናዊ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ሎተሪ መግዛት የለበትም ማለት ነው፡፡ዛሬ ብሔራዊ ሎተሪ ከፍተኛ እና የተለያዩ የሎተሪ አይነቶች በማዘጋጀት ከህዝቡ ላይ ብዛት ያለው ገንዘብ ለመሰብሰብ በመዘጋጀት ላይ ነው ፡፡ ያ ማለት ምን ማለት ነው፡፡ ሎተሪውን ገዛነው ማለት ምን ማለት፡፡

1. ህዝቡ በግፍ በበደል የሚገዛበትን ገንዘብ በፍቃደኝነት መስጠት መገበር ማለት ነው፡፡
2. ህዝቡ በግፍ የሚገደልበትን ጥይት መግዣ ገንዘብ በፍቃደኝነት መገበር ማለት ነው፡፡

3. ህዝቡ ያለ ፍርድ የሚንታሰርበትን እስር ቤት ለማስተዳደር በፍቃደኛነት መገበር ማለት ነው

4. ያለ ፍርድ ሰባዊ መብታችን ተገፎ በእስር ቤት የምንገረፍበትን ገንዝብ ለገራፊዎቻችን በፍቃደኝነት መገበር ማለት ነው

5. ያ ማለት እውነት ተሸፍኖ ሀሰት ለሚነዛው የዜና አውታር ገንዝብ በፍቃደኝነት መገበር ማለት ነው

6. ባአጠቃላይ ሰቆቃ አራሳችን ላይ እንዲረዝም በፍቃደኝነት ማገዝ ማለት ነው

ድንገት አንዳድ ሰዎች ስለ ሎተሪ አዞሪዎች ኑሮ ሁኔታ ወይም ገቢ ሊያሳስባችው ይችሉ ይሆናል፡፡ ነጥቡ ፍትህ ባለበት ሀገር እውነትነት ሊኖረው ይችላል፡፡ ነገር ግን ዛሬ በአዲስ አበባ የሎተሪ አዞሪዋችን ማንነት ልብ ብለን ብንመለከት አንድ ነገር ልብ ልንል እችላለን፡፡ያም የዛሬ ሎተሪ አዞሪዋች የትግራይ ልጆች ሳይሆኑ ከሌላ ብሄረስብ የመጡ ከመደራቸው በድህነት ተፈናቅለው በትምህርት ተኮትኩተው በሚያድጉበት ለጋ እድሜቸው ላይ ሎተሪ አዞሪ እንዲሆኑ የተፈረደባችው የወያኔ የግፍ አገዛዝ በተዘዋዋሪ መንገድ የደረሰባችው የዘመናችን ሰለባዎች ናችው፡፡ስለሆነም ሎተሪ በመግዛት ጭቆናን በደልን እና የግፍ አገዛዝን አናግዝ፡፡ ልጆቻችንም ወደ ትምህርት ገበታችው ይግቡ፡፡ ቁማርም መጫወት በሁለቱም የእምነት ቤቶች ሀጥያት ወይም ሀራም ነው፡፡
ጥይት በራስህ ገንዘብ አትግዛ፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.