ምከረው ምከረው እምቢ ካለ መከራ ይምከረው

Standard

በኦሮሚያ ያለው አለመረጋጋት እንደቀጠለ ነው::በኦሮሚያ የተከሰተውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በክልሉ ያለው አለመረጋጋቱ እንደቀጠለ እንደሚገኝ ታወቀ፡፡ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በህዝባዊ ተቃውሞ ተወጥራ የከረመችው ኦሮሚያ፣ በዚህ ሳምንትም በተለያዩ አካባቢዎች የተቃውሞ ሰልፎች እየተካሔዱባት ይገኛል፡፡ በኦሮሚያ ከተሞች ሲካሔድ የቆየው ይኸው ተቃውሞ በአዲሰ አበባ ዙሪያ ባሉ የኦሮሚያ ልዩ ዞኖች ውስጥም እየተዳረሰ እንደሚገኝ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ እንደ ሰበታ፣ ዓለም ገና፣ ካራቆሬ ባሉ የአዲስ ኦሮሚያ አካባቢዎች የተቃውሞ እንቅስቃሴ መታየት መጀመሩ እየተገለጸ ነው፡፡

እንደ አምቦ፣ ነቀምት፣ ወሊሶ፣ ጫንጮ፣ ጭሮ ያሉ ከተሞች አሁንም መረጋጋት እንደማይታይባቸው የሚገልጹት መረጃዎች፣ በየከተሞቹ ያለው ሁኔታም ውጥረት የነገሰበት እንደሆነ መረጃዎቹ ያክላሉ፡፡ በአለመረጋጋቱ የተነሳ፣ ከአሮሚያ ወደ አዲስ አበባ በሚገቡ ዕቃዎች ላይ እጥረት እየተከሰተ እንደሚገኝም ለማወቅ ተችሏል፡፡ በየከተሞቹ ያለውን ተቃውሞ ለማብረድ የስርዓቱ ወታደሮች እንዲሰማሩ ቢደረግም፣ ተቃውሞዉ ከዕለት ወደ ዕለት ሲጨምር እንጂ ሲቀንስ የታየበት ሁኔታ እንደሌለ የዓይን እማኞች ይገልጻሉ፡፡

የህወሓት አገዛዝ እንዲያከትም የሚጠይቁት እነዚሁ የተቃውሞ ትዕይንተ ህዝቦች፣ ገዥውን ስርዓት በይበልጥ እያስደነገጡት መጥተዋል፡፡ ተቃውሞዎችን ተከትሎ የይስሙላ እርምጃዎችን እየወሰደ የሚገኘው ስርዓቱ፣ ባለስልጣናትን ከቦታ ቦታ ማንሳቱን ቀጥሎበታል፡፡ ለአጭር ጊዜ በሚቆይ የፖለቲካ ለውጥ ላይ እንደሚያተኩር የሚነገርለት አገዛዙ፣ መፍትኤ የሚመስሉ ነገር ግን መፍትኤ ያልሆኑ ፖለቲካዊ እርምጃዎችን እየወሰደ ያለው አሁን ከገጠመው ቀውስ ራሱን ለማዳን ሲል ብቻ እንደሆነ ታዛቢዎች ይናገራሉ፡፡

© Activist

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.