በጂቡቲ የሚደረገው የንግድ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉ ታውቋል

Standard

አብዛኛው ከውጪ የሚመጡት እቃዎች ወደ ሃገር ውስጥ የሚገቡት በጂቡቲ ወደብ ነው። በዚህም ምክንያት የጂቡቲ ወደብ ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚስተናገድበት እንዲሆን አድርጎታል። ከዚህ በፊት ቢያንስ ከ800 ኣስከ 1000 የሚደርሱ ከባድ የጭነት መኪናዎች ከወደቡ ወደ መሃል ሃገር ጭነት ይዘው ያጓጓዙ እንደነበር ይታወቃል።በአሁን ሰአት ያለው የንግድ እንቅስቃሴ 70 በመቶ በሚያህል ቀንሷል። በቀን ከ200-250 ከባድ የጭነት መኪናዎች (Fleet) ብቻ ናቸው እቃ ከወደብ ጭነው ወደ መሃል ሃገር የሚያጓጉዙት። ይህንንም እንቅስቃሴ አብዛኞቹ የኤፈርት ኩባያ የሆኑ መኪናዎች የሚያካሄዱት። አሽከርካሪዎቹም በብዛት የወያኔ ሰዎች እንደሆኑ ይታወቃል።የሚጓጓዙት እቃዎችም በብዛት ለመንግስት ፕሮጄክቶች የሚውሉ ልዩ ልዩ እቃዎች ናቸው።ይህም ሆኖ አብዛኞቹ ሜጋ ፕሮጀክቶች ቆመዋል ወይንም ማለቅ አቅቷቸው እየተሰሩ ነው ለማስባል ብቻ አነስተኛ ስራዎች ብቻ እየተከናወኑባቸው ይገኛል:: አብዛኛዎቹ የስኳር ፕሮጀክቶች ማለቅ ሳይችሉ ባሉበት እንዲቆሙ መደረጉ ይታወሳል። ከጂቡቲ ወደብ የሚመጡ ካርጎ መጠን የቀነሰበት ምክነያት የወደቡ ታሪፍ በእጅጉ በመጨመሩ እንደሆነ ቢገለፅም። የወያኔ አገዛዛ የፖርት ሱዳን እና የበርበራን ወደቦች መጠቀም የጀመሩ ቢሆንም ከእነዚህ ወደቦች የሚራገፈውና ተጭኖ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባው መጠን በተመሳሳይ በጅቡቲ ወደብ እንደተስተዋለው በከፍተኛ መጠን ቀንሷል።ክሬን፣ ፎርክሊፊት የመሳሰሉ መሳሪያዎችን ሲያከራዩ የነበሩ ጅቡቲያኖችም ከቢዝነስ ውጭ የሆኑበት ሁኔታ ተፈጥሯል። የጭነት መኪናዎችን ወደ ነዳጅ ቦቴ በማስቀየር ንግድ ለመስራት የሞከሩ ኢትዮጵያዊያን የግል ነጋዴዎች ስራው በመቀዛቀዙ ምክንያትበዚህ መስክ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለመተው ተገደዋል።ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ የኤፈርት ኩባንያዎች ስር የሚገኙ የትራንስፖርት ኩባያዎች ስራውን በሞኖፖል እንዲይዙት በመደረጉ ሌሎች ባለ ሀብቶች እንዲገፉ ሆኗል።የትራንስፖርት ንግድ ለማድረግ ከባንክ ብድር በመውሰድ የጭነት መኪናዎች የገዙ በርካታ ኢትዮጵያዊያን መኪናዎቻቸውን ለማቆም ወይንም ገዢ ካገኙ ለመሸጥ ተገደዋል።የንግድ ሰዎች ከውጭ እቃዎች ሲያስመጡ በኢትዮጵያ ንግድ መርከብ ድርጅት ከላስጫኑ እቃቸው እንዳይገባላቸው ተደርጓል። የንግድ መርከብ ድርጅትን ሙሉ በሙሉ የህወሃት ሰዎች መቆጣጠራቸው ይታወቃል። እንዲህም ሆኖ እቃዎች በዶላር ተከፍሎ ሞጆ ወደ ሚገኘው ደረቅ ወደብ ድረስ የሚያደርሱት በኤፍርት ስር የሚገኙ የትራንስፖርት ኩባንያ መኪናዎች ናቸው። በአሁን ሰአት አልሲ (ሌተር ኦፍ ክሬዲት) የማግኘት ከፍተኛ ችግር አለ።ይህን የሚያገኙት ለስርአቱ ቅርብ የሆኑት ብቻ ናቸው።ለስርአቱ ቅርበት ላላቸው ነው “ንግድ ውስጥ ግቡ፡ እርሻ ጀምሩ” በሚል ማበረታቻ ያለምንም ኮላተራል ከባንክ ብድር እየወሰዱ እንዲከብሩ የሚደረገው። በአሁን ሰአት በአገሪቱ የተከሰተውን ተቃውሞ ተከትሎየህወሃት አባላት የሆኑ ነጋዴዎች ከሌላው ሰው ጋር መገናኘት ማቆማቸው ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው አካላት ይገልጻሉ።የህወሃት አባላት የሆኑ ነጋዴዎች በየጊዜው ተደጋጋሚ ስብሰባዎችን ሲያደርጉ ተስተውሏል።ለነጋዴዎቹ መሳሪያ የማስታጠቅ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ታውቋል። በሌላ በኩል በውጪ ሃገራት ገንዝብ የማሸሽና ንብረቶችን የመሸጥ ሁኔታ በስፌው እንዳለ በጉዳዩ እየተሳተፉ ያሉ ሰዎች ይጠቁማሉ። ይህም ቢሆን ሌሎች ሰዎች ንብረቶችን የመግዛት ፍላጎት ያለማሳየታቸው የህውሃት አባላት የሆኑ ነጋዴው ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል።
By Arbegnoch ginbot sebat Radio

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.