አዲስ አበባ በትግል ጥሪ ወረቀቶች አብባ አደረች

Standard

የአዲስ አበባ የአርበኞች ግንቦት 7 የማእከላዊ እዝ አባላት በአዲስ አበባ ሰፊ ቦታ ያካለለና በርካታ የትግል ጥሪ የተካተተባቸው በራሪ ወረቀቶችን በዋና ዋና ምንገዶች እና አዉቶብስ መናሀሪያዎች ሲበተኑ አድረዋል፡፡

ትግሉ ወያኔን ሳይቀብር ለአፍታ አይቆምም!!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

Advertisements

በመከላከያና በደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት መካከል ያለው አለመግባባት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ተሰማ

Standard

በአቶ ጌታቸው አሰፋ የሚመራው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያቤት እና በጄነራል ሳሞራ የሚመራው መከላከያ መካከል የተፈጠረው ያለመግባባት በግልጽ የሚታይበት ደረጃ ላይ መድረሱ ታውቋል። በመከላከያ ውስጥ ያሉ ከፍተኛ የጦር አዛዦች የደህንነቱ መስሪያ ቤት የሚያቀርበው መረጃ፤ ታእማኒነት የሌለው ነው በማለት በተደጋጋሚ ሲገልጹ ይሰማል። አቶ ጌታቸው አሰፋ በመከላከያ ውስጥ ያለውን ተሰሚነት ለማስፋት በሚል የሚወስዳቸው እርማጃዎች ቀጥታ ከጄነራል ሳሞራ ጋር እንዳጋጨው መረጃዎች ያመለክታሉ። ጄነራል ሳሞራና የእሱ ደጋፊ የሆኑ የጦር አዛዦችን ለመቆጣጠር በሚል አቶ ጌታቸው አሰፋ በመከላከያ ውስጥ ለሱ የሚታዘዝ መረቦችን ለመዘርጋት ያደረገውን ሙከራ ተከትሎ በሁለቱ የህወሃት ቁንጮዎች መካከል ከፍተኛ የሆነ ያለመግባባት ተፈጥሯል። በመከላከያ ውስጥ ለአቶ ጌታቸው አሰፋ ጥሩ ምልከታ አላቸው የሚባሉ ከፍተኛ የጦር አዛዦች ላይ በመከላከያ የወታደራዊ መረጃ ዋና መምሪያ ስር የሚገኘው በመከላከያ ጸረ መረጃ መምሪያ አማካኝነት ከፍተኛ ክትትል እየተደረገባቸው ይገኛል። በአቶ ጌታቸው አሰፋ እና በጄነራል ሳሞራ መካከል ያለውን አለመግባባት ለመቅረፍ በሚል ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል እና ሌ/ጄነራል ዮሃንስ ገ/መስቀል ለማሸማገል ያደረጉት ሙከራ አለመሳካቱን ከመከላከያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ሌ/ጄነራል ዮሃንስ ገ/መስቀል አቶ ጌታቸው አሰፋ ከሚመራው የደህንነቱ ዋና መስሪያቤት ጋር ጥብቅ ቁርኝት እንዳለው ይታወቃል። ሌ/ጄነራል ዮሃንስ ገ/መስቀል አሁን በመከላከያ የወታደራዊ መረጃ ዋና መምሪያ ሃላፊ ከሆኑት ሜ/ጄነራል ገብሬ ዲላ በፊት በመከላከያ የወታደራዊ መረጃ ዋና መምሪያ ሃላፊ እንደነበሩ ይታወሳል። ሌ/ጄነራል ዮሃንስ ገ/መስቀል ከጄነራል ሳሞራ ጋር ባላቸው አለመግባባት ምክንያት ነው ከዚህ ሃላፊነታቸው እንዲነሱ የተደረገው። ሌ/ጄነራል ዮሃንስ፤ አቶ ጌታቸው አሰፋና ጄነራል ሳሞራን ለማስታረቅ ያደረጉት ሙከራም የከሸፈው መጀመሪያውኑ ሌ/ጄነራል ዮሃንስ ገ/መስቀል እና ጄነራል ሳሞራ የሚግባቡ ባለመሆኑ ነው። አቶ ጌታቸው አሰፋ በመከላከያ ውስጥ የሚኖረውን ተጽኖ ለማስፋት ከሚጠቀምባቸው ሰዎች አንዱ ሌ/ጄነራል ዮሃንስ ገ/መስቀል እንደሆነ ይነገራል። ጄነራል ሳሞራ ሌ/ጄነራል ዮሃንስ ከደህንነቱ ዋና መስሪያቤት ጋር ያላቸውን ቅርርብ ጠንቅቆ እንደሚያውቀው ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ አካላት ይገልጻሉ። ከዚሁ ጋር ተያይዞ አቶ ጌታቸው አሰፋ በመከላከያ ውስጥ ያለውን ተሰሚነት ለማስፋት በሚል ከዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ከደህንነቱ መስሪያ ቤት የተገኘ መረጃ ያመለክታል። አቶ ደብረጺዮን መከላከያው ውስጥ ባለው በጎ ግንኙኑነት የተነሳ፤ አቶ ጌታቸው አሰፋ በዶ/ር ደብረጺዮን በኩል ነው፤ በመከላከያ ውስጥ ያለውን ፍላጎት ለማስጠበቅ የሚንቀሳቀሰው ሲሉ በደህንነት ውስጥ ያሉ አካላት ይገልጻሉ። ዶ/ር ደብረጺዮን በመከላከያ ውስጥ ያለውን ተሰሚነት ምክንያት በማድረግ አቶ ጌታቸው አሰፋን እና ጄነራል ሳሞራን ለማግባባት ያደረገው ሙከራ አለመሳካቱ ታውቋል። ጄነራል ሳሞራ አቶ ጌታቸው አሰፋ መከላከያን ለመቆጣጠር የሚያደርገውን ሙከራ እንዲያቆም በሃይለ ቃል መናገሩ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ አካላት ይገልጻሉ። በተጨማሪም የደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት የሚያቀርበው ሪፖርቶች በአብዛኛው በውሸት የተሞሉ በመሆናቸው ከደህንነቱ መስሪያ ቤት የሚመጣን ማንኛውም ሪፖርት በጥንቃቄ እንዲታይ ጄነራል ሳሞራ ትእዛዝ ማስተላለፉን ተከትሎ አቶ ጌታቸው አሰፋን ያስቆጣ ጉዳይ ሆኗል። በአሁን ሰአት ከፍተኛ የጦር አዛዦች ከደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት የሚመጣን ማንኛውንም የመረጃ ሪፖርት ከመጠቀም ይልቅ በመከላከያ ስር ባለው የወታደራዊ መረጃ ዋና መምሪያ በኩል የሚመጡ መረጃዎች ላይ እምነት እንዲያሳድሩ ሆኗል። በመከላከያ የወታደራዊ መረጃ ዋና መምሪያ፤ የደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት የስራ ክልል በሆነው በሲቪል መረጃ ስራዎች ውስጥ መግባቱ በሁለቱ ተቋማት መካከል ለተፈጠረው ያለመግባባት አንዱ ምክንያት እንደሆነ ይነገራል። በመከላከያና በደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት መካከል ያለውን ያለመግባባት ለመፍታት በሚል ተደጋጋሚ ጥረቶች ቢደረጉም እስካሁን ድረስ በጄነራል ሳሞራና በአቶ ጌታቸው አሰፋ መካከል ያለው ግንኙነት እንደሻከረ ይገኛል።

በአርበኞች ግንቦት ሰባት

ከመከላከያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወታደር እየከዳ መምጣቱ ታወቀ

Standard

ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወታደር መከላከያውን እየከዳ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በመከላከያ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ስጋት ተፈጥሯል። በጄነራል ሳሞራ የኑስ የተመራው ከፍተኛ የጦር አዛዦች የተገኙበት ስብሰባ ላይ ከወታደሮች መክዳት ጋር በተያያዘ ሰፊ ውይይት እንደተደረገ ለማወቅ ተችሏል። በተለያዩ ክፍለ ጦሮች ውስጥ የወታደሩ መክዳት በከፍተኛ ሁኔታ መስተዋሉንና ባሉትም ወታደሮች መሀል የመንፈስ ጥንካሬ መዳከሙ በስብሰባው ላይ በሰፊው ውይይት የተደረገበት ጉዳይ ሆኗል። የክፍለ ጦር አዛዦች የወታደሮችን መክዳት የመከላከል ሃላፊነት የነሱ ድርሻ እንደሆነና ከአሁን በኋላም እድገት የሚሰጠው ወታደሮችን በማቆየት አመርቂ ውጤት ላመጡ አዛዦች እንደሚሆን ጄነራል ሳሞራ ገልጿል። በመከላከያ ውስጥ ከመክዳት ጋር ተያይዞ እየተፈጠረ ያለው ችግር ሃገሪቷ ከገባችበት የፖለቲካ ምስቅልቅል ጋር የተቆራኘ እንደሆነ መከላከያ ውስጥ ያሉ የጦር አዛዦች እርስ በርስ ሲያወሩ የሚገልጹት ቢሆንም በስብሰባው ላይ ደፍሮ የተናገረ እንደሌለ ለማወቅ ተችሏል። እንዲሁም የመከላከያ ሃይል ከምንጊዜም በላይ ጠንካራ እንደሆነ በሳሞራ የኑስ የቀረበው ገለጻ በስብሰባው ላይ የተገኙ አዛዦችን ሊያሳምን እንዳልቻለ ጉዳዩን በቅርብ ሲከታተል የነበረ ወኪላችን ተመልክቷል። በስብሰባው ማጠቃለያ ላይ የጄነራል ሳሞራን ስም እያነሱ ሲያሞጋግሱ ተስተውሏል። ከስብሰባው በኋላ የጦር አዛዦች እንዴት ተኩኖ ነው እየከዳ ያለውን ሰራዊት ማስቆም የሚቻለው፤ ሰራዊቱ ልቡ ከኛ አይደለም፤ በዚህ ሁኔታ መከላከያ አደጋ ውስጥ እየገባ ነው በማለት ጭንቀታቸውን ሲገልጹ ተስተውለዋል። በመከላከያ የተለያዩ ክፍለ ጦሮች ውስጥ የሚገኙ ወታደሮች በከፍተኛ ቁጥር መከላከያውን እየለቀቁ መምጣታቸውን ተከትሎ በአሁኑ ሰአት አንድ ሬጂመንት ጦር መያዝ ከሚገባው 700 የሰራዊት ቁጥር ውስጥ ከ400 በላይ እንዳልሆነ ከመከላከያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Arbegnoch ginbot sebat

Three Tigrians stoned to death in Nekemet,Ethiopia

Standard

Ethnic violence is not showing signs of ease in Ethiopia.On October 30,2017 a local mob stoned to death three Ethnic Tigrians  to death in the western town of Ethiopia Nekemt .  They were killed following a massive demonstration in the city against the Tigray Peoples Liberation Front government. This is for the first time for Tigreans to experience violence of this nature.Ethnic violence is now at a crisis level. This is the third major ethnic violence in a week time. On October 22, dozens of Ethiopians of who are of Amhara ethnic background were killed in Chora and Dega zones in Buno Bedelle, South West Ethiopia.Two days ago, another deadly ethnic violence transpired in Benshangul Gumuz regional state in Western Ethiopia. Again, Ethiopians of Amhara origin were targeted and dozens were brutally killed. However, state media reported it as a conflict between individuals, not an attack against ethnic violence.

ኮንግረሱ በኢትዮጵያ ላይ ረቂቅ ህጉን እንዲያፀድቅ ግፊት እየተደረገ ነው

Standard

የኮሎራዶው የሪፐብሊካኑ ተወካይ ማይክ ኮፍመን በአሜሪካን ምክርቤት ፊት ቀርበው የኢትዮጵያ መንግስት በዜጎች ላይ የሚያድርሰውን ግድያና እስራት አባብሶ መቀጠሉን ተናገሩ። ኮንግረስማኑ የኢትዮጵያ መንግስት ድምፁ ለ30 ቀን ይራዘምልን ብሎ በሎቢስቶቹ አማካኝነት ሲጠይቅ ቢያንስ እድሉን እንደመጠቀም ጭራሽኑ በዜጉች ላይ የሚያደርገውን የሰበአዊ መብት ጥሰት በማጠናከር በርካታ ዜጎች በመንግስት ወታደሮች ተገድለዋል። መንግስት ድርጊቱን ባለማቆሙ ይህ ህግ በአስቸኮይ ወደ ድምፅ ቀርቦ እንዲያልፍ እጠይቃለሁ ሲሉ ጠንከር ያለ ንግግር አድርገዋል። 128 በሪፐቢልካንና በዴሞክራት ድጋፍ ከ 70 በላይ ባለስልጣናት ስፖንሰር ማድረጋቸውንም አያየዘው ለምክርቤቱ አባላት ተናግረዋል።ሙሉ ንግግሩን ይከታተሉ ለዘላቂ ወዳጅነት የሚረዳን ይህን ህግ ስናፀድቅ ነው ያሉት ማይክ ኮፍመን አሜሪካ ለሰው ልጅ ሰበአዊ መብት መከበር የምታደርገው ድጋፍ ማጠናከር ይጠበቅባታል ሲሉ ኢትዮጵያ ደግሞ የሰበአዊ መብት ረገጣ የሚፈፀምባት ሀገር መሆኖ ግልፅ ነው። ስለሆነም የድምፅ አሰጣጥ ስነስራቱ ለቤቱ ይቀርብ ዘንድ ተማፅነዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የአሜሪካን 150ሺ ዶላር በየወሩ ለሎቢስት ካምፓኒ በመክፈል መጥፎ ድርጊታቸው እንዳይወጣባቸው ለማድረግ ጥረት እያደረጉ መሆኑንም አክለው ገልፀዋል።

ኮንግረስ ማን ማይክ ኮፍመን