ህወሃትን ማመን ቀብሮ ነው (መስቀሉ አየለ)

Standard

ራስ ስሁለ ሚካኤል የተባለ የትግራይ ገዥ በዘመኑ የነበሩትን የሃማሴን ገዥ በመካከላቸው ስለነበረው ቁርሾ ተነጋግረው ይፈቱት ዘንድ ሽማግሌ ላከባቸው።ሰውየው ሰምተው እንዳልሰሙ ዝም አሉ፤ ባያምኑት ነው። ለሁለተኛ ግዜ ስእለ አድህኖ አስይዞ ቄስ ቢልክባቸው ምስለ ፍቁር ወልዳ ከቤቴ ድረስ መጥታ እንዴት እንቢ እላለሁ ሲሉ ቄሱን ተከትለው ወደ ትግራይ ቢሄዱ እጅና እግራቸውን በእግረ ሙቅ አስሮ ከበረት ወርውሯቸዋል። (ለወያኔ ስእለ ማርያም እቤቴ ድረስ መጥታ እንዴት እምቢኝ እላለሁ ብሎ ማመን ደካማ ጎን ነው።ትናንት የጎንደሩን አመጽ ተከትሎ ለተጋድሎ የወጡትን አርበኞች ታቦት ጭምር እያስያዘ መሳሪያ ካስፈታ ቦሃላ ከተኙበት ከሌሊት እያነቀ ወስዶ የፈጃቸውን ወገኖቻችንን ቤት ይቁጠረው)።ከዛን ግዜ ጀምሮ የትግሬዎች ተረት “ዶሮን በባቄላ ሃማሴንን በመሃላ” የምትል ሆና የምትኖር ቢሆንም ቅሉ የዚህች ተረት ትርጉም ለሻቢያ ሰዎች ሳይቀር ስጋና ደም ገዝታ በአካል ገዝፋ የታየቻቸው ባድመን ምክንያት አድርጎ ከጀርባ በወጋቸው ግዜ ነው። ፈረንጆቹ የጠላትን ክፉ ሲገልጡት “ባክ ስታበር” ይሉታል። ዛሬ ወያኔ ከኳታር እስከ ላቲን አሜሪካዋ ብራዚል፤ ከሃይሌ ገብረ ስላሴ እስከ አውሮፓ ህብረት ሰባ ሁለት ግዜ ያህል ወደ ሻቢያ አስታራቂ ሽምግሌ ቢልክም የሽቢያ መልስ ጆሮ ዳባ ልበስ የሆነው ከዚህች ዘመን የማይሽራት ጠባሳ ታሪክ ተነስቶ ነው። ሁለት ግዜ ስ ህተት ብሎ ነገር የለም።

የቅንጅት መሪዎች ከዚያ ሁሉ አገር አቀፍ ንቅናቄና የፖለቲካና የሞራል የበላይነት በኋላ እግር ተወርች ታስረው ዘብጥያ መውረዳቸው ብቻ ሳይሆን ስንት የእንጨት ለቃሚ ደሃ ልጆችን አናት ያበደ ዝሆን በሚገደልበት እስታይፐር አናታቸውን እንደ ፓፓየ ላፈረጣቸው አጋዚ “ሃላፊነቱ የኛ ነው” ብለው፤ “አይለመደንም” ብለው፤ መቀለጃ ሆነው መውጣታቸው ብቻ እንዲሁም እነርሱ በሰሩት ጥፋት የኢትዮጵያን ፖለቲካ ምን ያህል አመት ወደ ኋላ እንደጎተቱት ዛሬ ላይ ሆነው ሲያስቡት ያማል። ወያኔ ዛሬ ድረስ እድሜ አግኝቶ የአገራችን ፖለቲካ አስፈሪ ወደ ሆነ የጽንፈኝነት ጥግ እንዲደርስ የቅንጅት ሰዎች ሰርተው ያለፉት ታሪካዊ ስህተት የራሱን አሉታዊ ሚና መጫዎቱን መካድ አይቻልም። በእርግጥም ይኽ ወቅት የአገራችን ምሁራን እውቀት በወረቀት ላይ የተንጠለጠለ እንጅ ነባራዊ ከሆነው የአገራችንን ችግር ከመፍታት አንጻር ብዙ እንደሚቀረው ያሳየ እንደነበር ምስኪኑ ህዝብ በወቅቱ ሲሰጥ ከነበረው ማስጠንቀቂያ መረዳት ይቻላል።

ዛሬ የገዱና የለማ መገርሳ መንገድ መስቀለኛ ነጥብ ላይ መቆሙ ሌላው ዙር የታሪክ ሂደት ነው። እንደ ወያኔ ያለ ጭንቅላታቸው ገና ከናታቸው ማህጸን ውስጥ ሳሉ በጨነገፈባቸው ድኩማን የሚዘወር ድርጅት አለም ላይ የተፈጠሩት ኩነቶች አሲረውለትና በሻቢያ ታንክ ታዝሎ አዲስ አበባ መግባቱን እንደራሱ የድል ውጤት በመቁጠር እሾክና ግርምቢጥ ካልሆነ ሌላ ነገር ከማይደማው እርጉም ምድር መምጣቱንም ሆነ በቁጥር ደረጃ እዚህ ግባ የማይባል አናሳ ህዝብ መወከሉን እረስቶት በኢትዮጵያዊነት ካባ ከመድመቅ ይልቅ አገሪቱን በምርኮ እንደተያዘች የንጉስ ሚስት ክብሯን በመገሰስ ላይ ሲዘምት እንዳልኖረ ይኽ ቅጥ ያጣው ብልግናው፣ ውሸቱ፣ እብሪቱ፣ ዘረፋው፣ ድንቁርናው ሁሉ ግዜውን ጠብቆ ግዜ ከፈጠረው እውነታ ( ሪያሊቲ) ጋር ተፋጠጠ። የርሱን ቋንቋ እየተናገሩ ነገር ግን ባርነት በቃን ብለው የጉሮሮ አጥት መሆን የቻሉ ሰዎች ከመሃሉ ጎልምሰው ሲወጡ የሚሸሸግበት ጥግ ማጣቱን፣ የሚቀጥፍበት አማርኛ መንጠፉን ይኽ ገዜ አስይቶናል።

መሳይ መኮንን ዘብሔረ ኢሳት በዝርዝር እንደሄደበት የትግራዩ ገዝ ጉጅሌ ዕከመከላከያ እስከ ደህንነት፣ ቁልፍ ከሆኑ የሚንስትር ቦታዎች እስከ ወልቃትይ ጠገዴ ለድርድር የማላቀርበው ነገር የለም።ብቻ ይኽን ህዝባዊ ማእበል ወደ ሰገባህ ተመለስ በሉልን እንጅ ይኽ አብዮት አባይ ጸሃየንና አዜብ ጎላን በልቶ የሚቆምልን ከሆነ እነርሱንም ጭዳ አድርጎ ለማቀረብ ችግር የለብንምዕ ሲል በእንባ ጭምር ልመና ማቅረቡን ተረድተናል።

ቀጣዩ የ አገሪቱ አቅጣጣ በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ይወሰናል።

፩ኛ ህወሃት ከላይ በምሳሌ እንዳስቀመጥኩት በባህሪው የማይታመን ለመሆኑ ከዘርማንዘሮቹ ታሪክና እስካሁን የተጓዘበትን መንገድ እንደምሳሌ ጠቅሻለሁ። ስለዚህ ቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብም ይሁን እሳቱን ከፊት የተጋፈጠው የገዱ ለማ ጥምረት በምን ያህል መተማመኛ ይቀበለዋል፧፣ አልቀበልም ካለስ ቀጣዩ መውጫ መንገድ ወይንም ኤክሲት ስትራቴጅ ምንድን ነው፧

፪ኛ የገዱ ለማ አካሄድ እንደ ቅንጅት ሰዎች ሁሉ አሁን የያዙት አካሄድ ዕህገ መንግስታዊ መብታችን ስለሆነ ነውዕ ከሚል ጭፍን እምነት ተነስተው ነው ወይንስ ህዝባዊ ማእበሉ የደረሰበትን የእድገት ደረጃ በደንብ ተገንዝበው፣ ወያኔስ ልመናውም ሆነ ማስፈራራቱም አልሳካለት ሲል በመጨረሻ ለሚመዘው ሰይፍ ምን ያህል ተዘጋጅተዋል የሚሉት ቁልፍ ጥያቄዎች ናቸው።

እንደ ማሳሰቢያ

ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንደሚወጡት ፍንጮች ከሆነ የአሜሪካ መንግስት አሁን የደረሰበት የድምዳሜ ደረጃ ወያኔ ይበልጥ እድሜ እያገኘ በሄደ ቁጥር አገሪቱ ይበልጥ ወደ አደገኛ አቅጣጫ እየተገፋች ስለሆነ የሽግግር ሂደቱ አካል ሊሆን አይገባውም የሚል ሲሆን የእንግሊዝ መንግስት ደግሞ በተጻራሪው ወያኔን ራሱን ሪፎርም አድርጎ ማስቀጠሉ የተሻለ ነው የሚል አቋም በመያዙ የገዱ ለማ ጥምረት የውጭ መንግስታትን አካሄድ በሰከነ መንፈስ እንዲመረምር ግድ ይለዋል።

Advertisements

የወያኔ አገዛዝ ካጠመደልን የእርስ በእርስ እልቂት ህዝባችንንና አገራችንን እንታደግ። የአርበኞች ግንቦት7 ርዕስ አንቀፅ

Standard

December 15, 2017

የህወሃት አገዛዝ ለሥልጣን ዕድሜው መራዘም ሲል በአገራችን ያሰፈነው የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ የጋራ ታሪክ ባለቤት የሆነውን ህዝባችንን በባህልና በቋንቋ ሸንሽኖ አንደኛው ከሌላኛው ጋር ምንም የሚያቆራኘው ታሪካዊም ሆነ ወገናዊ ትሥሥር በመካከሉ እንደሌለ በመስበክ እያንዳንዱ በጥላቻና በጥርጣሬ እንዲተያይ የማድረግ ስልታዊ እርምጃ ነው።

ተደጋግሞ እንደተገለጸው ህወሃት የተጠቀመበት ይህ የአንድ አገር ዜጎችን በቋንቋና በባህል ከፋፍሎ የመግዛት ፖሊሲ አውሮፓዊያን አፍሪካን በቅኝ ግዛትነት በተቀራመቱበት ዘመን ከተጠቀሙበት ስልት የተቀዳ መሆኑ ግልጽ ነው። በዚያን ዘመን ቅኝ ግዛት ሥር የወደቁ የአፍሪካ አገሮች የቀድሞ ቅኝ ገዥዎቻቸው ተጠቃለው ከወጡላቸውና በራሳቸው ዜጎች መመራት ከጀመሩ ወዲህ እንኳ ትተውባቸው ከሄዱት የርስ በርስ ክፍፍል መውጣት አቅቶአቸው ላለፉት 50 እና 60 አመታት በመገዳደልና አንዱ ሌላውን እንደጠላት በመቁጠር ሲናቆሩ ከባርነት ቀንበር ነጻ ወጥቻለሁ ላለው ህዝባቸው ኑሮ መሻሻል አንዳችም ፋይዳ ሳያስገኙ በተቃራኒው የመከራ፤ የስቃይና አለመረጋጋት ምንጭ ሆነው ዘልቀዋል ።

በትግራይ ህዝብ ሥም የሚነግደው ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይን የሚመራው የአድዋ መንደርተኞች ስብስብ ይህንን ለጥቁር ህዝቦች ስቃይና መከራ ምንጭ የሆነውን የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ በአገራችን ሲያስተዋውቁ አላማቸው ግልጽ ነበር። “የመንግሥትን ሥልጣን ያለምንም ተቀናቃኝ እስከወዲያኛው በመቆጣጠር የአገር ሃብት እና ገንዘብ መዝረፍ ያስችለናል ፤ በወጣትነት ዕድሜያችን የታገልንለትን የታላቋን ትግራይ ግንባታ ለማሳካት ይረዳናል ፤ ካልሆነም ደግሞ ልጆቻችን በዕውቀትና በኢኮኖሚ የበላይነት ይዘው አገሪቷን ለዘለዓለሙ ለመግዛት የሚችሉበትን እድል ይሰጠናል” በሚሉ ስሌቶች ነው። በእርግጥም ይህ ስሌታቸው ተሳክቶላቸው ባዶ እግራቸውን ሚኒልክ ቤተመንግሥት ድረስ የዘለቁ የቀድሞ ተጋዳላዮች የአገሪቱን ሃብት እንዳሻቸው በቤተሰብ እና በቡድን ተቧድነው ለመበዝበር ችለዋል። ልጆቻቸውን ዋጋቸው እጅግ ውድ ወደ ተባሉ የአውሮፓ፤ የአሜሪካና የኤሲያ ትምህርት ቤቶች በመላክ ከፍተኛ ጥራት ያለው ትምህርት እንዲቀስሙና በተተኪነት ሥልጣን ለመረከብ እንዲችሉ አዘጋጅተዋቸዋል። ጥጋብ በፈጠረው እብሪት ተወጥረው ለድል ካበቃቸው የቀድሞ ወዳጃቸው እና የአሁኑ ጠላታቸው ሻቢያ ጋር በመላተም የታላቋ ትግራይ ግንባታ ህልማቸው ህልም ሆኖ የቀረ ከመሆኑ በቀር ምንም ያላሳኩት ነገር የለም ።

ያ ሁሉ ሆኖ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመላው አገራችን እየተስተዋለ የመጣው ታጋሽና አስተዋይ የሆነው ህዝባችን ለህወሃት ሥልጣን ዕድሜ መራዘም አይነተኛ መሠረት ሆኖ በማገልገል ላይ ያለውን የልዩነትና የጥላቻ ግድግዳ በርግዶ በመውጣት “እኛ አንድ ነን ! አንከፋፈልም ! ” በማለት በዘረኝነትና በአምባገነናዊነት ላይ የተቃውሞ ድምጹን በጋራ ማሰማት ጀምሮአል። በተለይ በመካከላቸው በተዘራው ያልተቋረጠ የጥላቻ ቅሰቀሳና ፕሮፖጋንዳ እስከ ወዲያኛው በጠላትነት እንዲተያዩ የተፈረደባቸው አማራ እና ኦሮሞ ይህንን የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ በመናድ በጋራ ጠላታቸው ህወሃት ላይ በአንድ ድምጽ ተቃውሞ ማሰማት መጀመራቸው የአድዋ ማፊያዎች የቆሙበትን መሬት ያራደባቸው ብቻ ሳይሆን ዙሪያ ጥምጥማቸውን ሊወጡት የማይችሉት ገደል አድርጎባቸዋል። በዚህም የተነሳ ህወሃት በተስፋ መቁረጥ ስሜት የመጨረሻውን የአጥፍቶ መጥፋት እርምጃ ለመውሰድ የሚችለውን ሁሉ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ነው።

ሰሞኑን በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የሚማሩ ወጣት ተማሪዎች ትግሪኛ ተናጋሪ በሆኑ የዕድሜ እኩዮቻቸው ላይ እጅግ አደገኛ የሆነ እርምጃ መውሰድ የጀመሩት ህወሃት ከበስተጀርባ ሆኖ በሚሰራው አንዱን ከሌላው የማጋጨት እኩይ ተግባር እንደሆነ ሁሉም ተገንዝቦታል። አዲግራት ውስጥ ለትምህርት በሄደ የ19 አመት የአማራ ተወላጅ ላይ የተፈጸመው ግድያ የብሄር ግጭት ለመፍጠር ሆን ተብሎ በህወሃት የተሸረበ ሴራ መሆኑ አያጠያይቅም። በዚህ ሴራ ምክንያት በአብዛኞቹ ዩኒቨርሲቲዎች የተቀሰቀሰው የበቀል እርምጃ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ለሁለት የትግራይ ተወላጆች ህይወት ህልፈት እና ለበርካቶች ከያሉበት ዩኒቨርሲቲዎች ግቢ መሸሽ ምክንያት ሆኖአል። በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መካከል የተቀሰቀሰው የብሄር ግጭት ሳያባራ አገዛዙ ጨለንቆ ላይ የአጋዚ ጦር በማዝመት እጅግ የሚሰቀጥጥ ጭፍጨፋ ፈጽሞአል። በጭፍጨፋውም ቁጥራቸው 20 የሚደርስ የኦሮሞ ተወላጆች ህይወት ሲቀጠፍ በርካቶች ለመቁሰል አደጋ መጋለጣቸው ተረጋግጦአል። የኢትዮጵያ ህዝብ “የ27 አመት የህወሃት አፈናና ጭቆና ያብቃ! “ ብሎ በመጠየቁ ጥያቄውን አቅጣጫ ለማስቀየር ህወሃት በየቦታው የለኮሰው የብሄር ግጭት ለማንም የማይበጅ ፤ አገሪቷንና ህዝቧን ብቻ ሳይሆን ህወሃትን ጭምር መልሶ የሚያቃጥል አደጋ ያዘለ መሆኑን ህወሃቶች ልብ ሊሉት የቻሉት አይመስልም።

ከአንድ ወር በላይ በፈጀው የመቀሌው ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባቸው ፍጻሜ ላይ እንደ አዲስ ከሰየሟቸው የአመራር አባላቶች መካከል አብላጫዎቹ ከህወሃት ውልደት ጀምሮ የነበሩና አገራችንና ህዝባችን ላይ እስከ ዛሬ በተፈጸሙ ወንጀሎች ግንባር ቀደም ተዋናይ የሆኑ ግለሰቦች መሆናቸውን እንኳን በስሙ የሚነገደው የትግራይ ህዝብ የተቀረው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ያውቀዋል። ህወሃት እነዚህኑ ወንጀለኞች ቦታ በመቀያየር “ታድሼና ተጠናክሬ” ወጥቻለሁ በማለት ህዝባችን ለነጻነቱ እና ለመብቱ እያካሄ ያለውን ትግል በፈረጠመ ወታደራዊ ጡንቻው ለመጨፍለቅ ወስኖ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ይፋ አድርጎአል። በዚህ የውሳኔ እርምጃው ኦሮሚያ ውስጥ ገብቶ በርካታ ንጹሃንን የመጨፍጨፍ እርምጃ ከመውሰድና በየዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የብሄር ግጭቶችን ከመቀሰቀስ አልፎ ህዝባችን መረጃ የሚያገኝባቸውን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥንና የኦሮሚያ ሚዲያ ኔት ዎርክ ስርጪቶችን በማወክ ከአየር ላይ እንዲወርዱ አድርጎአል። በዩኒቨርስቲዎች ግቢ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ወደ ህብረተሰቡ ውስጥ ሊዛመት ይችላል ብሎ በከፍተኛ ሁኔታ በሰጋባቸው ከተሞችና ዞኖች ውስጥም የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲስተጓጎል እያደረገ ነው።

ህወሃት በተስፋ መቁረጥ ስሜት እየወሰደ ባለው እርምጃ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ቦታዎች በተነሱት የብሄር ግጭቶች ውድ ህይወታቸው እንዲቀጠፍ እና ለአካል ጉዳተኝነት ለተዳረጉት ዜጎች ሁሉ ብቸኛ ተጠያቂ እንደሆነ አርበኞች ግንቦት 7 ያምናል። በእንዲህ አይነት እብሪትና ጥጋብ የህዝብ ተቃውሞን እስከ መጨረሻው መጨፍለቅ እንደማይቻልም በተግባር ለማረጋገጥ ከምንጊዜውም በላይ ተግቶ ይሰራል።

ህዝባችን ውድ ልጆቹን በየጊዜው በአጋዚ ጨካኝ ጦር ጥይት እየተነጠቀ በመጠየቅ ላይ ያለው የመብት ጥያቄ ፤ ይህ አገዛዝ ከሥር መሠረቱ እንዲቀየር እና በሚመርጠው መንግሥት የሚተዳደርበትን የዲሞክራሲ ሥርዓት ለማምጣት እንጂ ለሩብ ከፍለ ዘመን መከራውና ሰቆቃው ተጠያቂ የሆኑ ጥቂት የአደዋ ልጆች በቤተሰብ እና በመንደር ተሰባስበው በተሃድሶና በግምገማ ስም ተጠናክረው የመከራ ዘመኑን እንዲያራዝሙለት አይደለም።

በመሆኑም በዚህ የህወሃት ሥርዓት ውስጥ ተወልደውና አድገው የሥርዓቱን አስከፊነት በመረዳት ለነጻነታቸው እየታገሉ ያሉ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እርስ በርስ በጠላትነት ከመተያየት ወጥተው አፍላ ጉልበታቸውንና ለለውጥ ያላቸውን እምቅ ሃይል የጋራ ጠላታቸው በሆነው ወያኔ ላይ ብቻ በማዋል የአገዛዝ ዘመኑን ለማሳጠር እየተካሄደ ያለውን አገራዊ ትግል እንዲያጠናክሩ አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪውን ያቀርባል። የትግራይ ህዝብንና በህወሃት ውስጥ የተሰባሰቡትን ጸረ ህዝብ ሃይል ለያይቶ መመልከት እጅግ ጠቃሚ ነው። ስለዚህም ህወሃት በአገራችንና በህዝባችን ላይ ሲፈጽም ለኖረው ወንጀሎች የትግራይ ወገኖቻችንን በሙሉ በጅምላ መፈረጅ ሊያስከትለው የሚችለው አደጋ ለአገራችንም ሆነ ለህዝባችን የሚበጅ አይሆንም። ይልቁንም ህወሃት ባጠመደልን የርስ በርስ ግጭት ውስጥ ገብተን አገራችንና ህዝባችንን ከማይወጣበት መከራ ውስጥ እንዳንከት ሁላችንም ጠንከረን በጋራ መንቀሳቀስ ይኖርብናል። የእያንዳንዳችን ዲሞክራሲያዊ እና ሰብአዊ መብት የተከበረባት ፤ የኢኮኖሚ ብልጽግናና ማህበራዊ ፍትህ የሰፈነባት ፤ የእያንዳንዳችን ደህንነትና ጥቅም የሚጠበቅባት አንዲት ሉአላዊት አገር ባለቤት መሆን የምንችለው እጅ ለእጅ ተያይዘን ህወሃት ከደገሰልን የርስ በርስ ግጭት ወጥተን በጋራ የአገዛዝ እድሜውን ማሳጠር ስንችል ብቻ እንደሆነ አርበኞች ግንቦት 7 ያረጋግጣል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ስብሰባ በከፍተኛ ያለመግባባት እየቀጠለ ይገኛል:

Standard

የኢህአዴግ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ በከፍተኛ ጭቅጭቅ መቀጠሉ ታውቋል። ለአለመግባባቱ ዋነኛ ምክንያት የሆነው የወቅታዊ የሃገሪቱን ጉዳይ ላይ በሚነጋገሩበት ወቅት በሃገሪቱ እየተፈጠረው ያለው አለመረጋጋት የብአዴን እና የኦህዴድ እጅ አለበት መባሉ ነው። በዚህም የተነሳ የኦህዴድና እና የብአዴን ባለስልጣናት ከፍተኛ ተቃውሞ አንስተዋል። የኦህዴድ አመራሮች አቶ ሃይለማሪያምንም ወርፈዋል። በኦህዴዱ ሊቀመንበር በአቶ ለማ መገርሳ እና አባይ ጸሃዬ መካከል የተነሳው አለመግባባትም ዞር በል፤ ዞር በል እስከመባባልና ሃይለ ቃል እስከመለዋወጥ ተዳርሰዋል። በሌላ በኩል የኦህዴድ አመራሮች በጸጥታ አካላት ላይ እኩል ውክልና የለም የሚል ጥያቄ ማቅረባቸው የታወቀ ሲሆን ይህን አጀንዳ ገፍተው ውሳኔ ለማስወሰን ያደረጉት ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ስብሰባ የተባለው እንደተጠበቀው የስራ አስፈጻሚ ስብሰባ ሊሆን አልቻለም። በስብሰባው ላይ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ያልሆኑ የየድርጅቶቹ የቀድሞ ባለስልጣናት መካፈላቸው የታወቀ ሲሆን ከመከላከያ እና የደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት ተወክለው የመጡ በርካታ ግለሰቦችም ስብሰባውን እየተካፈሉ ይገኛሉ።

የመረጃና ደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት ቁንጮ የሆነው አቶ ጌታቸው አሰፋ ስራ አስፈጻሚው ሙሉ በሙሉ ሃገሪቷን መምራት የሚችል አቅም ስለሌለው ተበትኖ በሌላ ብቁ አካላት ናቸው በሚባሉ መተካት እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ሰጥቷል። አቶ ጌታቸው አሰፋ ስብሰባውን በአቋሚነት እየተሳፈ አይገኝም። ገባ ወጣ እያለ አስፈላጊ ነው በሚለው ጊዜ ነው እየቀረበ አቅጣጫዎችን ለማመላከት ሲጥር የሚስተዋለው። ከደህንነቱ የመጡ ተወካዮች በአቋሚነት ስብሰባውን እየተካፈሉ ይገኛሉ።

በስብሰባው ላይ ሊያግባባቸው ያልቻለው ሌላው ጉዳይ ብአዴን እና ኦህዴድ እንደ ህወሃት እራሳቸውን ማጽዳት እንዳለባቸው በህወሃት በኩል መገለጹ ነው። የህወሃት አመራሮች በብአዴን እና በኦህዴድ ያሉ የተወሰኑ አመራሮች ከስልጣናቸው መነሳት እንዳለባቸው ያቀረቡት ሃሳብ ከሁለቱ ድርጅቶች ከፍተኛ ተቃውሞ እንዲነሳ ምክንያት ሆኗል። በሌላ በኩል የአለመግባባቱ ሁኔታ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን ተከትሎ ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤን ያካተተ የአሸማጋዮች ቡድን እንዲገቡና ስብሰባውን እንዲካፈሉ የቀረበው ሃሳብ በኦህዴድና በብአዴን አመራሮች ከፍተኛ ተቃውሞ ቀርቦበት ውድቅ ሊደረግ ችሏል።

አቶ ሃይለማሪያም ሃገሪቷን በአግባባቡ እየመራ አይደለም። ስልጣኑን መልቀቅ አለበት የሚል ድምጾች ከኦህዴዶች አመራሮች በከፍተኛ ሁኔታ እየተስተጋባ ይገኛል። ይህን ተከትሎ በመንግስት መዋቅር ውስጥ በከፍተኛ ሃላፊነት የሚገኙ በርካታ ባለስልጣናት ከሃላፊነታቸው እንደሚነሱ እየተነገረ ይገኛል። የደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤትም ቀጣይ በሃላፊነት ቦታ ላይ ሊመደቡ ይገባቸዋል የሚላቸውን የግለሰቦች ስም ዝርዝር ለማቅረብ ዝግጅቱን እንደጨረሰም ታውቋል።

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ስብሰባ የተባለው በአጭር ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደማይጠበቅ ታውቋል። ያለው አለመግባባት መፍትሄ ከማግኘቱ ይልቅ ልዩነቶቹ እየሰፉ መሄዱ በኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ውስጥ አለመረጋጋትን ፈጥሯል። በጨለንቆ ላይ በመከላከያ የተወሰደው ጭፍጨፋ ተከትሎ የኦህዴድ ከፍተኛ አመራሮች ተቃውሟቸውን በስብሰባው ላይ አሰምተዋል። በስብሰባው የሻይ እረፍት ላይ በቡድን ተከፋፍለው የሚጨቃጨቁ አካላት ብዙ እንደሆኑ ተስተውሏል። ስብሰባው ከማለቁ በፊትም የማረጋጊያ መግለጫ ለማውጣት እየተዘጋጀ ይገኛል።

የአየር ሀይል አብራሪዉ መቶ አለቃ ማስረሻ ሠጤ

Standard

መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ፣ የ”ኢትዮጵያ” አየር ኃይል ውስጥ የበረራ አስተማሪና የሄሊኮፍተር አብራሪ ነበር። ከትውልድ ቦታው ብዙው የማይርቀው ባህርዳር ላይ ያዙትና “ግንቦት 7ን ልትቀላቀል እየሄድክ ነው” ብለው አሰሩት። 10 አመት ፈረዱበት።

ከእስረኛው ነጥለው ጨለማ ቤት አሰሩት። ሌላ ዞን ካለ እስረኛ ጋር በማይገናኝበት ሁኔታ ታስሮ ቂሊንጦ ተቃጠለ። የተቃጠለው ዞን2 እና ዞን 3 ነው። መቶ አለቃው ታስሮ የነበረው ከሁለቱ ዞኖች ውጭ ያለ ጨለማ ቤት!

መቶ አለቃ ማስረሻ ባልነበረበት ጉዳይ ሸዋሮቢት ተወስዶ ተሰቃይቷል። ጣራ ላይ ተሰቅሏል። የተሰቀለበትን ገመድ ድንገት በጥሰው መሬት ላይ ጥለውት ለብዙ ጊዜ ወገቡን ታሞ ነበር። ስድቡ፣ ዘለፋና ድብደባው የከፋ ነበር።

በመጨረሻም ባልነበረበት ቦታና ጉዳይ ዋናው አንተ ነህ ተብሎ 1ኛ ተከሳሽ ሆኗል። እስከ ሞት በሚያስቀጣ የሀሰት ክስ!

መቶ አለቃ ማስረሻ ጨለማ ቤት ታስሮ በተፈጠረ ክስተት ተዋናይ ነበር ተብሎ ሲከሰስ የሚጠቀስበት “ማስረጃ” የሚያሳዝን ነው። አንድ ክስ ላይ “ነሃሴ 27/2008 ማታ ማስረሻ ሰጤ ዞን 2 ዱርዬዎቹን ሰብስቦ……” ይላል። ያኔ መቶ አለቃ ማስረሻ ዞን 2 አልነበረም!

ግን ሀሰት የማጥቂያ መሳርያ ሆናለችና፣ በሀሰት ያስራሉ! በሀሰት ይከሳሉ! የሀሰት ማስረጃ ያቀርባሉ! በሀሰት ይፈርዳሉ!

Getachew Shiferaw