የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ስብሰባ በከፍተኛ ያለመግባባት እየቀጠለ ይገኛል:

Standard

የኢህአዴግ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ በከፍተኛ ጭቅጭቅ መቀጠሉ ታውቋል። ለአለመግባባቱ ዋነኛ ምክንያት የሆነው የወቅታዊ የሃገሪቱን ጉዳይ ላይ በሚነጋገሩበት ወቅት በሃገሪቱ እየተፈጠረው ያለው አለመረጋጋት የብአዴን እና የኦህዴድ እጅ አለበት መባሉ ነው። በዚህም የተነሳ የኦህዴድና እና የብአዴን ባለስልጣናት ከፍተኛ ተቃውሞ አንስተዋል። የኦህዴድ አመራሮች አቶ ሃይለማሪያምንም ወርፈዋል። በኦህዴዱ ሊቀመንበር በአቶ ለማ መገርሳ እና አባይ ጸሃዬ መካከል የተነሳው አለመግባባትም ዞር በል፤ ዞር በል እስከመባባልና ሃይለ ቃል እስከመለዋወጥ ተዳርሰዋል። በሌላ በኩል የኦህዴድ አመራሮች በጸጥታ አካላት ላይ እኩል ውክልና የለም የሚል ጥያቄ ማቅረባቸው የታወቀ ሲሆን ይህን አጀንዳ ገፍተው ውሳኔ ለማስወሰን ያደረጉት ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ስብሰባ የተባለው እንደተጠበቀው የስራ አስፈጻሚ ስብሰባ ሊሆን አልቻለም። በስብሰባው ላይ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ያልሆኑ የየድርጅቶቹ የቀድሞ ባለስልጣናት መካፈላቸው የታወቀ ሲሆን ከመከላከያ እና የደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት ተወክለው የመጡ በርካታ ግለሰቦችም ስብሰባውን እየተካፈሉ ይገኛሉ።

የመረጃና ደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት ቁንጮ የሆነው አቶ ጌታቸው አሰፋ ስራ አስፈጻሚው ሙሉ በሙሉ ሃገሪቷን መምራት የሚችል አቅም ስለሌለው ተበትኖ በሌላ ብቁ አካላት ናቸው በሚባሉ መተካት እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ሰጥቷል። አቶ ጌታቸው አሰፋ ስብሰባውን በአቋሚነት እየተሳፈ አይገኝም። ገባ ወጣ እያለ አስፈላጊ ነው በሚለው ጊዜ ነው እየቀረበ አቅጣጫዎችን ለማመላከት ሲጥር የሚስተዋለው። ከደህንነቱ የመጡ ተወካዮች በአቋሚነት ስብሰባውን እየተካፈሉ ይገኛሉ።

በስብሰባው ላይ ሊያግባባቸው ያልቻለው ሌላው ጉዳይ ብአዴን እና ኦህዴድ እንደ ህወሃት እራሳቸውን ማጽዳት እንዳለባቸው በህወሃት በኩል መገለጹ ነው። የህወሃት አመራሮች በብአዴን እና በኦህዴድ ያሉ የተወሰኑ አመራሮች ከስልጣናቸው መነሳት እንዳለባቸው ያቀረቡት ሃሳብ ከሁለቱ ድርጅቶች ከፍተኛ ተቃውሞ እንዲነሳ ምክንያት ሆኗል። በሌላ በኩል የአለመግባባቱ ሁኔታ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን ተከትሎ ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤን ያካተተ የአሸማጋዮች ቡድን እንዲገቡና ስብሰባውን እንዲካፈሉ የቀረበው ሃሳብ በኦህዴድና በብአዴን አመራሮች ከፍተኛ ተቃውሞ ቀርቦበት ውድቅ ሊደረግ ችሏል።

አቶ ሃይለማሪያም ሃገሪቷን በአግባባቡ እየመራ አይደለም። ስልጣኑን መልቀቅ አለበት የሚል ድምጾች ከኦህዴዶች አመራሮች በከፍተኛ ሁኔታ እየተስተጋባ ይገኛል። ይህን ተከትሎ በመንግስት መዋቅር ውስጥ በከፍተኛ ሃላፊነት የሚገኙ በርካታ ባለስልጣናት ከሃላፊነታቸው እንደሚነሱ እየተነገረ ይገኛል። የደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤትም ቀጣይ በሃላፊነት ቦታ ላይ ሊመደቡ ይገባቸዋል የሚላቸውን የግለሰቦች ስም ዝርዝር ለማቅረብ ዝግጅቱን እንደጨረሰም ታውቋል።

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ስብሰባ የተባለው በአጭር ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደማይጠበቅ ታውቋል። ያለው አለመግባባት መፍትሄ ከማግኘቱ ይልቅ ልዩነቶቹ እየሰፉ መሄዱ በኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ውስጥ አለመረጋጋትን ፈጥሯል። በጨለንቆ ላይ በመከላከያ የተወሰደው ጭፍጨፋ ተከትሎ የኦህዴድ ከፍተኛ አመራሮች ተቃውሟቸውን በስብሰባው ላይ አሰምተዋል። በስብሰባው የሻይ እረፍት ላይ በቡድን ተከፋፍለው የሚጨቃጨቁ አካላት ብዙ እንደሆኑ ተስተውሏል። ስብሰባው ከማለቁ በፊትም የማረጋጊያ መግለጫ ለማውጣት እየተዘጋጀ ይገኛል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.