በራያ ያለው ሁኔታ በአሁኑ ሰዓት:

Standard

 ራያ ቆቦና አካባቢው የተረጋጋ ቢመስልም ከጥንት ጀምሮ ክፉነቷን የተረዳው የራያ ህዝብ ሁሉን በጥርጣሬ እየተመለከለተ በጥንቃቄ በመጠባበቅ ላይ ነው :: እየሆነ ያለውን በሰከነ መንገድ ከመፍታት ተሓህቶች ግራ የገባው ሆነው ወጣቱን የደበደቡበትም አጋጣሚ እንደነበር ተስተውሏል :: ራያን በአውሮፕላን እየቃኟት ይገኛል :: ዋጃ ውሃ አካባቢ (ወደ ትግራይ ካጠቃለሉት የራያ ክፍል “የትግራይ ድንበር” ብለው የሚጠሩት) የውሃ አመላላሽ ቦቲዎች ተሰድረው ይገኛሉ:: ትላንት በተለይም ከጥዋት ጀምሮ እስከ 11:30 ጨርጨር፣መሆኒ እና አላማጣ ስልክ ተዘግቶ ነበር:: ከአለማጣ እስከ ጮቢ በር ድረስ መኪና መሄድ ይችላል ከዚያ በኋላ ግን ማለፍ አይቻልም ። ህዝቡ ግን ለምንድን ነው ቆቦ መሄድ የተከለከልነው እያለ ነው። ምን ሊሆን እንደሚችል ገና አልታወቀም!

በኛ በኩል ያለን ትንታኔ:

 ያውሮኘላኑ ጉዳይ ከወታደራዊ ፅንሰ ሃሳብ አንፃር መቃኘት እንደሚያስፈልግ በማመን ምናልባት የጅፒኤስ coordinate ለመለካትና ከቀሪው የራያ ክፍል የተወሰነውን ወይም በጠቅላላ ወደ ትግራይ ለማስገባት አስበው ሊሆን ይችላል። ለዚህ ሃሳብ መነሻችን የራያ ፍሬሽ (በራያ ቆቦ ጎለሻ ቀበሌ የሚገኘውን) የፍራፍሬ ውጤቱን ሲያስተዋውቁ ቦታው የሚገኘው በአማራ ክልል ሆኖ እያለ ትግራይ ውስጥ እንደሚገኝ promote እያደሚያደርጉ መረጃ አለን። ሌላው መላምት የህዝቡ አንዴ ከተነሳ ቆራጥነቱን ስለሚያውቁ ተረብሸው ምን ያክል ሃይል በእንቅስቃሴ እንዳለ ለማወቅ የሚያደርጉት ቅኝት ሊሆን ይችላል::

 የውሃ አመላላሽ ቦቲዎች መከሰት ቃጠሎ ከተነሳ ለማጥፋት እንደሆነ ተገምቷል።

 የስልክ መቋረጡና ህዝቡን ወደ ቆቦ እንዳይሄድ እገዳ የመጣላቸው ምክኒያት ሁለቱ ራያዎች ከተገኛኙ የሃይል አሰላለፋን ስለሚለውጠው በሁለቱ ክልል የሚገኘው ወንድማማች ህዝብ እንዳይገናኝ ለማድረግ የሚባክኑበት ጊዜዊ የከሰረ እቅድ ከመሆን የዘለለ ሊሆን አይችልም። ሲጠቃለል ትግራይ አካባቢ ጉዳት እንዳይደርስ ራያን የጦርነት “buffer zone ” ለማድረግ ማለማቸው ግልጽ ሆኖልናል።መፍትሄ: በሌሎች የአማራ አካባቢዎች፣ በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያና በሌሎችም የሃገራችን ክፍሎች የህዝብ አጋርነት እንቅስቃሴ እንዲኖር ያገባኛል የሚል ሁሉ አበክሮ መስራት።

 በማናምነው ብአዴን ውስጥ የሚገኙና እየሆነ ያለው ጉዳይ የገባቸው አካላት የህቡዕ እንቅስቃሲያቸውን በሚገባ መስራትና ተንኮለኞቹ የሚወጥኑትን እኩይ ተግባር ለማክሸፍ ህዝቡን መርዳት።

Mengesha Retie

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.