በአዳማ ናዝሬት በህዝቡና በፌደራል ፖሊስ መካከል ከፍተኛ ግጭት ተቀስቅሷል

Standard

በአዳማ ናዝሬት ከተማ ከመሬት ስርጭትና ምሪት ጋር በተያያዘ ህዝቡ ከፍተኛ ቅሬታ ሲያሰማ እንደነበር ይታወቃል። የመኖሪያ ቤት መስሪያ እጦት ጋር ተያይዞ ዛሬ ድረስ ችግሩ ባለመቀረፉ የተነሳ ነዋሪው የራሱን አማራጭ በመውሰድ በተለምዶ (የጨረቃ) ቤት መሬት ከገበሬ በመግዛት ሰርተው እየኖሩ ይገኛሉ። በጸጥታ ሃይሎች በመታገዝ በተለምዶ ብራዘርስ ብስኩት ፋብሪካ ጀርባ አካባቢ ያሉት ነዋሪዎችን ቤት በሃይል ማፍረስ በጀመሩ ታጣቂዎችና በነዋሪዎች መሀከል በተነሳ ግጭት በርካታ ሰዎች ለጉዳት ተዳርገዋል። ይሄን ተከትሎ አመፁ ተቀጣጥሎ አዳማን መሀል ሰንጥቆ ከሚያልፈው ዋናው አውራ ጎዳና መንገድ ላይ ዓለም ሆቴልና ሀኒ ኬክ ቤት አካባቢ ደርሶ ህዝቡና ፌደራል ፓሊስ ተጋጭተዋል፡፡ በዚህም ግጭት የተጎዱ ሰዎች እናዳሉ ለማወቅ ተችሏል። በርካታ የፌደራል ፖሊስ ወታደሮች ብረስ ለበስ ወታደራዊ መኪና በመያዝ ተቃውሞውን ለመበተን እየጣሩ ይገኛሉ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.