ከፌስቡክ ውጭ በአካልና በስልክ የሚደርሱኝ መልዕክቶች(ከአርቲስት አስቴር በዳኔ)

Standard

ሰሞኑን ቤተሰቦቼ፦

አንቺ ልጅ አርፈሽ አትቀመጪም እነዚህ ምስኪን ልጆችሽ አያሳዝኑሽም

አንዳንድ ሰዎች፦

አንቺ ልጅ ማንን ተማምነሽ ነው? አትፈሪም ? መኖር አትፈልጊም በእሳት ትጫወቻለሽ? እነ እንትና ላይ የደረሰውን አልሰማሽም? እየው ነግረንሻል ሴት መሆንሽን አትርሺ…ወይ ከሃገር ውጪ…

ወገኖች ፦

አስቴርዬ በርቺ። በጣም ነው የኮራንብሽ ሰው የለም ብለን ተስፋ ቆርጠን ነበር። አይዞሽ ለሁሉም ቀን አለው ከጎንሽ ነን። እውነት ነፃ ታወጣሻለች እግዚአብሔር ይጠብቅሽ…ብቻ እየተጠነቀቅሽ…

የመንግስት ደጋፊ ነን የሚሉ፦

ስሚ አርፈሽ ተቀመጪ! አጉል ጀግና ለመባል ነው?! በረጅም ገመድ እንደታሰርሽ እወቂያት! ከፈለግን ሳብ ማድረግ ነው። የምን እዩኝ እዩኝ ነው?! አርፈሽ ድራማሽን ስሪ!!!

ጥቂት ከፍተኛ ባለስልጣናት ፦

አንቺኮ ያመንሽበትን ሃሳብ ፊትለፊት በግልፅና በድፍረት መናገር የጀመርሽው ዛሬ አይደለም ። ሃሳብሽን በነፃነት መግለጽ ዲሞክራሳዊ መብትሽ ነው። ወደ አመፅ እስካልሄድሽ ድረስ። እንደውም ጠንከር ብለሽ ለምን የፖለቲካ ፓርቲ አትመሰርቺም። አያያዝሽ ከአርቱ ይልቅ ወደ ፖለቲከኛነቱ እያመዘነ ነው።…

ልጆቼ፦

ኧረ እማ ሰሞኑን አልተቻልሽም በጣም ተቀይረሻል። ግን አይዞሽ አትፍሪ የመሰለሽን አድርጊ …ግን ቢያስሩሽስ? እኛስ እንዴት እንሆናለን?…ግን እግዚአብሔር አለልን…

እኔ ለራሴ፦

አስቴርዬ አይዞሽ ልጆችሽን የሰጠሽ እግዚአብሔር ነው። የነሱን አደራ ለሱ ስጭው። ፍርሃት ቀድሞ የሚገድል በሽታ ነው! እየሞቱ የውሸት ከመኖር እየኖሩ መሞት ይሻላል። በዚህች ምድር ላይ የምትኖሪው አንዴ ነው። ትርጉም ያለው ዘመን አይሽሬ ስራ ሰርተሽ፤ የህዝብን ድምፅ አስተጋብተሽ ለእውነት ብትሰዊም አትከስሪም። ያለሽን ሁሉ ለሀገርሽ ስጭ። በቅንነት ለመታገል ከወሰንሽ መለወጥ የማይቻል ነገር የለም። አንድ ሰው ብዙ ነው። ኢትዮጵያ ላይ ሰላም እስኪሰፍን እንዳትተኚ። ከወገኖችሽ ጎን ቁሚ። እውነትን ግለጪ። ለኔ ሳይሆን ለኛ ከሚሉት ቆራጦች ጎን ቁሚ። ሃሳብሽን በምክንያትና በእውቀት ላይ ተመስርተሽ ማንፀባረቅሽን እንዳታቆሚ። እመኚ እንጂ አትፍሪ ለውጥ ይመጣል ። ኢትዮጵያ መሀን አይደለችም። በፍፁም አትፈራርስም!!!

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.