ጥብቅ ማስጠንቀቂያ በደቡብ አፍሪካ ለምትኖሩ ለኢትዮጵያ ስደተኞች ማሀበር ማህበርሰብ በሙሉ

Standard

በሳውዝ ኣፍሪካ የሚገኘው የህወሃት ኤምባሲ ከጃንዋሪ 27, 2018 ጀምሮ በተከታታይ ባዘጋጀው ዜጎችን የማማለል ስብሰባ ለተለያዩ የማህበረሰባችን ኣባላት ፤ ለሃይማኖት መሪዎችና ባለሃብቶች ጥሪ በማድረግ በሃገሪቱ የተከሰተውን የገንዘብ እጥረት ተከትሎ በሚልዮን የሚቆጠር ዶላሮችን በውጪ ሃገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለመሰብሰብ አልሞና ኣቅዶ መነሳቱ ይታወቃል። ነገር ግን ሃገሪቱ አሁን ላለችበት ከፍተኛ የፖለቲካ ቀውስና የኢኮኖሚ ውድቀት ተጠያቂው አሁን በስልጣን ላይ ያለው የህወሃት ቡድን ፤በሃገሪቱ ውስጥ የነበረውን በቢሊዮን የሚቆጠረውን ዶላር በመዝረፍና በዓለም ላይ ባሉ በተለያዩ ኣገሮች ባንክ ውስጥ ማስቀመጣቸው በማሰረጃ የተረጋገጠ ሃቅና ፀሐይ የሞቀው የአደባባይ ሚስጥር ነው። በዚህም ምክንያት በሃገራችን የሚኖሩ ወገኖቻችን ለከፍተኛ ረሃብና ችግር ተጋልጠዋል። ይህንንም ለመቃወም ወደ ኣደባባይ የወጡ በተለያዩ ክልልሎች የሚገኙ ወገኖቻችንን በህወሃት አጋዚ ቅልብ ወታደሮች ደማቸው በጠራራ ፀሐይ በኣደባባይ እየፈሰሰ ይገኛል በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ወደ አልታወቁ በትግራይና በአፋር በሎቹም በሃገሪቱ በሚገኙ እስር ቤቶች በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ይገኛሉ።

በመሆኑም በዚህ የህወሃት ኤምባሲ የገንዘብ ማሰባሰብ ጥሪ ላይ መዋጮ አንድታደርጉ ጥሪ የተደረገላችሁ የእምነት አባቶች፤ባለ ሃብቶችና ሌሎችም የማህበረሰባችን ኣባላቶች ከዚህ መንግስት ኤምባሲ ጋር ገንኙነት ማድረግና ለሚጠይቀው ማንኛውም የፖለቲካም ሆነ ኢኮኖሚያዊና ማሀበራዊ ጉዳዮች ላይ ተሳትፎ ማድረግና ምላሽ መስጠት በሃገራችን ኢትዮጵያ እየተገደሉ ባሉ ሰዎች ደም መቀለድና ከፋሺስቱና ገዳይ ከሆነው ህወሃት ጋር መተባበር እነደሆነ አውቃችሁ፤ይህ ሊወድቅ የተቃረበውን የወያኔ ስርዓት ከኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ አሽቀንጥሮ ለመጣል መራራ ትግል እያደረገ ካለው ወገናችሁ ጋር ኣብራችሁ እንድትቆሙ የኢትዮጵያ ማህበር ማህበረሰብ በደቡብ ኣፍሪካ ሃገራዊ ጥሪውን እያቀረበ፤ በሳውዝ ኣፍሪካ በስደተኛ ስም እየኖራችሁና የመኖሪያ ፍቃድ ለመንፈሳዊ ኣገልግሎት ብላችሁ ያውጣችሁትን ፈቃድ ይዛችሁ ለፖለቲካ ጥቅም የምታውሉት ከሆነ ማህበሩ የእያንዳዳችሁን ስም ለሳውዝ ኣፍሪካ መንግስት ኣሳልፎ የሚሰጥ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።

የኢትዮጵያ ማህበር ማህበረሰብ በደቡብ ኣፍሪካ

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.