ኦሮሞዎች ከሶማሌ ክልል እንዲፈናቀሉ ከፍተኛ ሚና የነበረው ጄኔራል አብርሃ ወ/ማርያም የማዕረግ ዕድገት ተሰጠው።

Standard

ከሱማሌ ክልል የተፈናቀሉ ኦሮሞዎች አንድ ሚሊዮን መድረሱን አለም አቀፍ ተቋማት ገልጸዋል

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ቢሮ (UNOCHA)፣ የብሔራዊ አደጋ አስተዳደር ኮሚሽን (NDRMC) እንዲሁም የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት(IOM) በጋራ ባወጡት መግለጫ አንድ ሚሊየን የሚጠጋ ህዝብ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መፈናቀሉን አስታውቀዋል።

አሁንም በአካባቢው ሰላም እንደሌለና የዜጎች መፈናቀል እንደቀጠለ መግለጫው ያትታል። ተፈናቃዮች በአሁኑ ጊዜ በኦሮሚያ፣ በሐረሪ ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተሞች ያለበቂ የምግብና መጠለያ አቅርቦት በችግር እያሳለፉ እንደሆነ ገልጿል። ድርጅቶቹ በተለያየ ጥናቶች አረጋገጥኩ እንዳሉት፤ ከጥር ወር ጀምሮ 110 ሺህ የሚሆኑ አባውራዎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ጠቅሷል።

አለም አቀፍ ተቋማቱ በጋራ ባወጡት መግለጫ ቢያንስ ከ93 ሽህ በላይ እድማቸው ለትምህርት የደረሱ ህፃናት ከትምህርት ገበታቸው እንደተናጠቡና ከ1500 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከወላጆቻቸው መለየታቸውን ገልጸዋል።

በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች የወሰን አካባቢ በተነሳ ግጭት በርካታ ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ ሚሊዮኖች ደግሞ ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ መደረጉ የሚታወቅ ሲሆን ከጀርባ በመሆን የኦሮሞ ተወላጆችን ከሶማሌ ክልል እንዲወጡ የህወሓት ጄኔራሎች ከፍተኛ ሚና እንደነበራቸው ሲነገር ቆይቷል።

በዛሬው እለት የሙሉ ጀኔራልነት ማዕረግ ካገኙ መኮንኖች መካከል የደቡብ ምስራቅ ዕዝ አዛዥ ሌ/ጄኔራል አብርሀ ወ/ማርያም ይገኝበታል። ይህ ሰው የኦሮሞ ተወላጆች መፈናቀልና በሶማሌ ክልል በየጊዜው በሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ቀዳሚ ተጠያቂ እንደሆነ ይነገራል።

ጄኔራሉ በቀጥታ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ከደረሰው የማይረሳ በደል

ሌላ በከፍተኛ ሙስና የተዘፈቀ ከገቢውና ከደመወዙ እጅግ በራቀ ሁኔታ ውብና ድንቅ ቪላዎችን በሃምሳ ሚሊዮን በሚገመት ገንዘብ ያስገነባ ሰው ነው።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.