አንዳርጋቸው ፅጌ

Standard

ደርግን ለመጣል በወጣትነት እድሜው ወደ በረሀ ወርዷል፡ከእልህ አስጨራሽ ትግል በኋላ ፡ወደ ስልጣን መጡ ፡የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ሀላፊ ሆኖ ሰርቷል። ከ ወያኔ ጋር በቆየባቸው አመታትም ፡የሚሆነውና የሚደረገው ነገር ፡እያሳሰበው መጣ ፡ለመቀየርም ሞገተ ተከራከረ ፡ተፋጨ ፡ተጣላ። ወደ እንግሊዝ ሀገር ተሰደደ ።ባአጠቃላይ የወያኔን ስርአት እንዲህ ሲል ገልጾ መጽሀፍ በ 1997 አሳትሟል” ነጻነትን የማያውቁ ነጻ አውጭወች” ። ግንቦት ሰባትን በ ኤርትራ በረሀ ያቋቋመውና ብዙ ወጣቶችን ወታደራዊ ስልጠና በመስጠት አስመርቋል።አንዲ (አንዳርጋቸው ጽጌ) ማድረግ እንጅ ማውራት የማይወድ ፡የተግባር ሰው፡ቅን ጀግና ፡ደፋር፡እጅግ ሲበዛ እውነተኛ ሰው። ድ/ር ብርሀኑ ነጋ ስለ አንዳርጋቸው ሲናገር እንደዚህ ይላል”የተለየ ስብዕና የተላበሰ” ይለዋለ። ታጋይ አበበ ካሴ ደግሞ “ፍጹም የተግባር ሰው” ይላቸዋል። ወያኔ እጅግ ከሚፈራቸው ሰወች ውስጥ አንዲ ፡ግንባር ቀደሙ ናቸው። በ ወያኔው ጌታቸው አሰፋ የሚመራው ፡የገዳዮች ቡድን፡የ አንዲ እያንዳንዷን እንቅስቃሴ ይከታተል ነበር። በለስ ቀናቸውና በ 3.5 ሚሊዮን ዶላር ወደ ኤርትራ ሲጓዝ የመን ሰንአ ኤርፖርት ውስጥ ትራንዚት ሲያደርግ ተያዘ። ጌታቸው አሰፋን ለማምጣት አንድ የመንገደኛች አውሮፕላን ባስቸኳይ ከአ.አ ወደ ሰንአ እንዲበር ታዘዘ። ዋና አብራሪውና አምስት ሙሉ ሲቢል የለበሱ ፡ጥቁር መነጽር ያደረጉ ሰወችን ይዞ ፡ወደ፡የመን በረረ። ካፒቴኑ ለምን እንደሚበር አያውቅም ነበር ፡የመን ደርሶ ካረፈ በኋሏ ፡አንድ ሰው ሙሉ ፊቱን እንደሚሰቀል ሰው የተሸፈነ በ ሶሥት ሰወች ተይዞ ወደ አውሮፕላን ውስጥ አስገቡት ፡ወዲያውኑ ጉዙ ወደ አዲስ አበባ ተባልሁ ይላል፡ ዋና አብራሪው። እየሆነ ያለው ነገር ምን እንደሆነ ግራ ገባኝ፡ግን ልቤ አንድ ነገር ጠርጥሯል ፡የሆነ እጅግ በጣም የሚፈለግ ሰው እንደሆነ ገብቶኛል። አዲስ አበባ እንደደረስኩ የ አየር መንገዱ ሰርቪስ ሳይሆን ሌላ መኪና መጥቶ ወደዚያ ውስጥ አስገቡት። ቤት ገብቸ ካረፍኩኝ በኋል በ ዜና አንዳርጋቸው ጽጌ መያዙን፡ሰማሁ፡ባለሁበት ደርቄ ቀረሁ ፡ክው አለኩኝ ፡ፍርሀት ተሰማኝ ፡እልክ ያዘኝ፡ግን በቃ ምንም ማድረግ አይቻልም ሲል የነበረውን ሁኔታ ባለንጀራየ ነበር ያጫወተኝ። አሁን አንዲ አብሯቸው በታገሉት የ ወያኔ አጋሰሶች የሞት ፍርድ ተፈርዶበት የት እንደታሰረ እንኳ ለማንም ባልተነገረበት ሁኔታ ውስጥ አጉሮ ፡ያሰቃየዋል። አንዳርጋቸው ጽጌን ኢትዮጵያዊ የሆነ ብቻ ሳይሆን ሰው የሆነ በሙሉ ሊታገሉለት የሚገባ ጀግና ና አርበኛ ነው። አንዲን አለመፍታት ማለት በተለይ በተለይ ለአማራ ያለችሁን ጥላቻ የሚያሳይ ነው። አሁን ጀግና ነኝ የምትል ጀግንነትህ የሚታይበት ወንድነትህ የሚፈተንበት፡ ኢትዮጵያዊነትህን የምታስመሰክርበት ፡ትግል ይጠብቀናል።

አንዳርጋቸውን አለመፍታት ለድርድር አይቀርብም!

ምንጭ Getnet Girmaw

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.