የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጅ እስክንድር ነጋ

Standard

የወያኔ ካድሬዎች የእስክንድርና አንዱአለም ይፈታሉ መባሉን ተከትሎ ዘረኛ የሆነ የመርዝ ተቃውሟቸውን እየረጩ ይገኛሉ። የወያኔ የእግር አሳት የሆኑት እነ እስክንድር የግንቦት ሰባት አባል ነን ብላቹ ፈርሙ ቢባሉ ያልሆነውን ነን ብለን አንፈርምም ማለታቸው ለወያኔ ሌላኛው አዲስ አጣብቂኝ ሆኖባታል። በተደጋጋሚ የቀረበላቸውን ወያኔያዊ የይቅርታ ወረቀት አንፈርምም በማለት የሕዝብ ልጅነታቸውን በተግባር ያሳዩት የፖለቲካ እስረኞቹ ወያኔ ለፖለቲካ ፍጆታ እና ለካድሬዎቹ ማጭበርበሪያ ያሰበው ደብዳቤ መክሸፉ አስደንግጦታል። ለአሜሪካ ኮንግረስ የቀረበው የውሳኔ ሰነድ ያስደነበራቸው ወያኔዎች የቀረበላቸውን እድል ተጠቅመው የፖለቲካ እስረኞቹን መፍታት ይጠበቅባቸዋል። በበታችነት የሚሰቃዩት ካድሬዎቻቸው እንደ ውሻ እየጮኹ ይገኛሉ። ይህ የፖለቲካ ዱብዳባ ሕዝብን አዘናግቼ የስልጣን እድሜዬን አስረዝማለሁ ባለው የወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ላይ ግልጽ የሆነ ክፋት የሚታይበት ሲሆን እነ እስክንድርን በሐሰት ክስ እያንገላታ መሆኑን የሚሰራው ደባ ምስክር ነው። እስክንድርም ሆነ አንዱአለም እንዲሁም ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች የወያኔን እባብነት ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ለወያኔ የሸምቀቆ ደባ ራሱን እንዲያንቅበት ሰጥተውታል። ጀግኖች መሆናቸውን በተደጋጋሚ ያሳዩ የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው።

#MinilikSalsawi

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.