አስገራሚ 3 የእስር ቤት ታሪኮች

Standard

1. አንድ ከውቅሮ ለኤርትራ መንግስት ይሰልላሉ ተብለው የተያዙ ሽማግሌ ነበሩ:: ግንቦት 7 ስለሚባል ድርጅት በሕይወታቸው ሰምተው አያውቁም:: እነ አጅሬ ደግሞ አስረው “አገሪቱና ሕዝቧን በሽብር ለመበጥበጥ የሚሰራው የግንቦት 7 አባልና አመራር በመሆን …” ብለው ይከሷቸዋል:: አራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀርበው ዳኛዋ ክሳቸውን እንደተፃፈው ታነብላቸዋለች:: ሽማግሌው ግራ ተጋብተው:

“ክቡር ፍርድ ቤት እኔ የተያዝኩት ግንቦት አስር ነው፣ የግንቦት ሥላሴ እለት እርሻ ቦታ ነበርኩ” አሉ::

2. አንድ ዘውዴ የሚባል የበርታ/ቤኒሻንጉል ልጅ ደሞ ነበር:: ከአሶሳ ይይዙና ያመጡታል:: ማዕከላዊ እንደገባ ምን ቋንቋ ተናጋሪ እንደሆነ ይጠይቁታል:: አብዛኞቹ የአሶሳ ልጆች ኦሮምኛና አማርኛ ከእራሳቸው ሩጣና ቋንቋ በተጨማሪ አቀላጥፈው ይናገራሉ:: ዘውዴም ኦሮምኛ እንደሚናገር ገና እንደተናገረ መዝግበው ያስገቡትና ለሁለት ወራት “አገሪቱና ሕዝቧን በሽብር ለመበጥበጥ የሚሰራው የኦነግ አባልና አመራር በመሆን …” ብለው ቀጠሮ እየጠየቁ ያቆዩታል:: ከሁለት ወር በኇላ ሌሎች የበርታ ልጆች ታስረው ማዕከላዊ ይገባሉ:: አንዴ አንድ መርማሪ ዘውዴ ከሌሎች የበርታ ልጆች ጋር በሩጣና ቋንቋ ሲያወራ ያየውና አስጠርቶ ሲጠይቀው ዘውዴ ለካ ኦሮሞ ሳይሆን በርታ ነው:: በመጨረሻም:

“አገሪቱና ሕዝቧን በሽብር ለመበጥበጥ የሚሰራው የቤህነን (ቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ) አባልና አመራር በመሆን …” የሚል ክስ አቅርበው ቂሊንጦ ላኩት::

3. አንድ ደሳለኝ (ከሁለት ዓመታት እስር በዃላ የተፈታ) የሚባል የባህርዳር ዙሪያ ገበሬን ደግሞ ይይዙትና በግንቦት 7 ይከሱታል:: ልጁ ግንቦት 7ን አይደለም ኢሕአዴግ ምን እንደሆነ አንኳን በቅጡ አያውቅም:: የያዙት ደህንነቶቹ መሬት ላይ አስቀምጠው “እስኪ ስለ ግንቦት 7 ንገረን?” አሉት:: ግራ የተጋባው ደሳለኝ “ስለ ግንቦት ልደታ ማለታቸሁ ነው ወንድሞቼ?” ይላቸዋል:: በቅፅበት:

“በመልሴ የተበሳጨ ደህንነት እንዴት እንደመታኝ ባላስታውስም የግራ መንጋጋዬ ወልቆ ደም ስተፋ ነው ትዝ የሚለኝ” ይላል ደሳለኝ::

ዘላለም ክብረት

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.