እነ አህመዲን ጀበል የመንግስት የይቅርታ ሰነድ ላይ አንፈርምም አሉ

Standard

BBN የካቲት 3/2010

የህዝበ ሙስሊሙ የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ በመሆንና ህዝባዊን ዉክልናን በመቀበል ለእስርና ለመከራ የተዳረጉት እነ አህመዲን ጀበል መንግስት ይቅርታ እንዲጠይቁ ባቀረበላቸው ሰነድ ላይ አንፈርምም ማለታቸው ታወቀ።

ለኡስታዝ አህመዲን ጀበል፣ለኡስታዝ አህመድ ሙስጠፋ፣ለኡስታዝ መሐመድ አባተ እና ኻሊድ ኢብራሒም ተመሳሳይ ይቅርታ መጠየቂያ ሰነድ ቀርቦላቸው እንደነበር ለማወቅ የተቻለ ሲሆን በይቅርታ ሰነዱም ላይ እነዚህ የህዝብ ወኪሎች «በሽብር ወንጀል ተሰማርተን ነበር፣የኢትዮጵያ መንግስትና ህዝቧን ይቅርታ እንጠይቃለን!» ብለው እንዲፈርሙ መጠያቃቸውን ቢቢኤን ለማወቅ ችሏል።

አራቱ የህዝበ ሙስሊሙ ወኪሎች በምንም አይነት ወንጀል ላይ ያልተሰማሩ መሆናቸውን በጽናት በመግለጽ ለመፈረም ፍቃደኛ አለመሆናቸውን ለመንግስት ባለስልጣናቱ አሳዉቀዋል። ጉዳያቸው በፍርድ ቤት የተያዘ መሆኑን የገለጹት እነ አህመዲን ጀበል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለይግባኝ መቅረቡን በማስረዳት በፍርድ ቤት በኩል ነጻ ሆነው ለመውጣት እየጣሩ መሆኑን አሳዉቀዋል።አራቱን የህዝብ ወኪሎች የማረሚያ ቤቱ ባለስልጣናት ነጣጥለው ቢጠይቋቸውም አራቱም ተመመሳሳይ መልስ ሰጥተዋል።

ህዝበ ሙስሊሙንና ነጻነት ፈላጊ የሆነውን የኢትዮጵያ ህዝብ አንገት ለማስደፋት በመንግስት በኩል የቀረበው የይቅርታ ሰነድ የታቀደለትን ግብ አልመታም ሲሉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ያስረዳሉ። መንግስት 746 እስረኞችን ፈታለሁ ብሎ በመገናኛ ብዙሗን ካወጀና ለህዝብ ተስፋ ከሰጠ በሗላ፤ ነጻ የሆኑ እስረኞችን በረጅም ገመድ አስሮ ለመፍትታት፣የህዝብን የለውጥ ተነሳሽነት ለማኮላሸት የሚጫወተው ፖለቲካዊ ቁማር ዉጤት አያመጣለትም በማለት እነዚሁ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች አጽንኦት ይሰጣሉ።

በ1996 እንደ ኢትዮጲያ እቆጣጠር መንግስት ያወጣው የሽብር ህግ፤ ሽብር ይቅርታ እንደማይጠየቅበት ያትታል። የህዝብ ወኪሎች በነጻ መለቀቅ ሲገባቸው «ይቅርታ» ጠይቁ የሚል ሰነድ መቅረቡ አገዛዙ ለመለወጥ ፍቃደኛ ያልሆነ መሆኑን አመላካች ነው ሲሉ ተንታኞች ያስረዳሉ።

የህዝብን ዉክልና የተቀበሉት እነ አህመዲን ጀበል የይቅርታዉን ሰነድ ላይ አንፈርምም ማለታቸው በሚሊዮን የሚቆጠር የኢትዮጵያን ህዝብ አንገት ቀና የሚያደርግ በመሆኑ «ሁሌም በጀግንነት ሲታወሱ ይኖራሉ!» የሚል ጽኑ እምነት በብዙዎች ዘንድ አለ። እነዚህ የህዝብ ወኪሎች የማእከላዊ ግርፋት ሳይበግራቸው፣የቂሊንጦ እስር ቤት ስቃይ ሳያንበረክካቸው፣የቃሊቲው ምድራዊ ሲኦል አንገት ስሜታቸውን ሳይሰብረው በጀግንነት አንገታቸውን ቀና አድረገው «ይቅርታ አንጠይቅም»ብለዋል።

ቢቢኤን ተጨማሪ መረጃዎችን በቀጣዮቹ ቀናቶች ዉስጥ ያቀርባል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.