ሲ.ፒ.ጄ የህወሃት መራሹን መንግስት ቅድመ ሁናቴ ተቃወመ

Standard

ለጋዜኞች መብት ጥብቅና የሚቆመው ሲ.ፒ.ጄ በህወሃት የሚመራዉ መንግስት ጋዜጠኛ እስክንደር ነጋን ለመፍትታ ያስቀመጠውን ቅድመ ሁናቴ ተቃወመ። ላለፉት 7 አመታት በህወሃት የማሰቃያና የማጎሪያ ካምፕ ዉስጥ በሐስት ተወንጅሎና በካንጋሮው ፍርድ ቤት 18 አመት ጽኑ እስራት ተፈርዶበት የሚሰቃየው ጋዜጠኛ እስክንደር ነጋ በፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ «ምህረት ተደርጎለታል»የሚል ዜና ቢሰራጭም፤ «ምህረት» የሚለው ቃል ተሰርዞ «የግንቦት 7 አባል ነኝ» ብለህ ይቅርታ ጠይቅ መባሉ ሲ.ፒ.ጄን አስቆጥቷል።ሲ.ፒ.ጄ መንግስት ያቀረበው የፍቺ ሰነድ «እስክንደር ያልፈጸመውን ወንጀል እንዲያምን የሚያስገድ ድቅድመ ሁናቴ ነው» ሲል አሳዉቋል።

«ይህ ረብ-የሌሹ የኢትዮጵያ መንግስት አመል፣ ይህንን ንጹህ ሰው በመልቀቅ ሊገኝ ይችል ለነበረው መልካም ነገር ጠንቅ ነው» በማለት የሲ.ፒ.ጄ የአፍሪካ መርሃ ግብር አስተባባሪ አንጀላ ኩይንተል ገልጸዋል። አክለውም«ያለምንም ቅድመ ሁናቴ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት እስክንድር ነጋን ሊፈቱ ይገባል!» ሲሉ አሳስበዋል።

ከጠዋቱ 5 ሰዓት ላይ የእስርቤቱ ባለስልጣናት እስክንድር ነጋን የግንቦት 7 አባል ነኝ ብሎ እንዲፈርም ጠይቀውታል፤ የመንግስትን ጥያቄ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ሳይቀበለው ወደ እስር ቤቱ ተመልሷል ሲል ሲል ሲፒጄ ባለቤቱን ወይዘሮ ሰርካለም ፋሲል ዋቢ አርጎ ገልጿል።

ጋዜጠኛ እስክንደር ነጋ የመጻፍ፣የመናገር መብትን በመተግበሩ ብቻ በህወሃት በሚመራዉ መንግስት ታስሮ 18 አመታት እንደተፈረደበት ይታወቃል። እስክንድር አለም አቀፋዊ እዉቅና ያለው ጋዜጠኛ ሲሆን፣ በሌለበት የተለያዩ ተቋማትን ሽልማት የተቀበለ ጋዜጠኛ ነው። ቀደም ሲልም በህወሃት የሚመራዉ መንግስት እስክንደር ይቅርታ ጠይቆ እንዲፈታ ያቀረበለትን ጥያቄ አልቀበልም ማለቱ ተዘግቧል።

እስክንደር ነጋ ትምርቱን በአሜሪካ ዉስጥ ያጠናቀቀ፣በሙያው በቂ እዉቀትንና ልምድን ያካበተ ኢትዮጵያዊ ነው። አሜሪካ ለመኖር የሚያስችለው ህጋዊ ሰነድ ያለው ሰው ቢሆንም ደሃዉን ያገሬ ህዝብ አገለግላለሁ በማለት ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰ ላገር ለወገን ተቆርቋሪ ነው ሲሉ ብዙዎች ይገልጹታል።

የእስክንደር ነጋ ባለቤት ጋዜጠኛ ሰርካልም ፋሲል ልክ እንደባለቤቷ የእስር ቤት ስቃይን ማሳለፏ በሰፊው የተዘገበ ነው። ነፍሰጡር ሳለች እስር ቤት የገባቸው ሰርካለም ፋሲል የመጀመሪያ ልጇን እስር ቤት ዉስጥ መገላገሏ የህወሃት መራሹ አገዛዝን አስከፊ ገጽታ ማሳያ ነው በማለት የኢትዮጵያ ፕሬስ ጉዳይ የሚከታተሉ ሲ.ፒ.ጄን የመሰሉ አለም አቀፍ ተቋማት ይዘግባሉ።ሰርካለም ፋሲል ከልጇ ናፍቆት እስክንድር ጋር በስደት አሜሪካ ዉስጥ የምትገኝ ሲሆን፤ ለዉድ ባለቤቷ ነጻነት ተግታ የምትታገል ታልቅ ሴት ሲሉ ብዙዎች ይገልጿታል።

የህወሃት የምህረት ዜና በቀናት ዉስጥ ተቀልብሷል። ሲ.ፒ.ጄም ፖለቲካዊ ድራማዉን አውግዞታል። ህወሃት እፈታለሁ ያላቸውን 746 እስረኞች ይፈታ ይሁን? በቀናት ዉስጥ የሚታይ ይሆናል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.