ታዋቂው የፖለቲካ ሰው #አቶ_ቡልቻ_ደመቅሳ በሸገር ታይምስ አማካኝነት አፄ ምኒልክን አስመልክቶ አንድ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር። ጥያቄውም እንዲህ ነበር ያቀረበላቸው።
#ሸገር_ታይምስ፡- አጼ ምኒልክን ለኦሮሞ የተለየ ጥላቻ አንዳላቸው አድርገው የሚያነሱ ሰዎች አሉ ይህ ነገር እንደት ያዩታል?
#አቶ_ቡልቻ፡- በፍጹም ጥላቻ የላቸውም ። አሮሞ የሚባል ስም አልወድም እገላቸዋለሁ ፣ ወላይታን አልወድም እፈጃቸዋለሁ ፣ አደሬን አልወድም ብለው አንድን ህዝብ መርጠው ጠላቴ ነው ብለው አያውቁም ፣ አስበውም አያውቁም ።
አገር እንዲሰለጥን ነው ፣ ህዝብ ሁሉ እንዲሰለጥን ነው የተቻላቸውን ሁሉ ያደረጉት ። ለአንድ ህዝብ የተለየ ጥላቻ ኖሯቸው ይህንን ህዝብ እንውጋው ብለው ይነጋገራሉ ብዬ መገመት እንኳን አልችልም ፡፡ እሳቸው ለአገራቸው ስልጣኔ ነው የለፉት ማንንም አይጠሉም ነበር ። ይህን ሁሉ የሚያደርጉት #ሌሎች ናቸው፡፡
Advertisements