የሰው ስጋ-በሉ የወያኔ ጦር

Standard

የመከላከያ ሰራዊት ለአንዲት ሀገር ዋልታና መከታ እንዲሁም የህዝብ አለኝታ ነው። ይህ ግን በአሁኑ ወቅት ያለውን “የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት” አይመለከትም።በድህረ ደርግ በህወሓት የተዋቀረው የመከላከያ ሰራዊት ከጫካ ጀምሮ የአንድን መንደርተኛ ቡድን ፍላጎት ከማገልገል ያለፈ ፋይዳ የሌለው የሽፍታ ታጣቂ ነው።ይህ ጦር ሀገራዊ ቁመና የሌለው፤ አንድም ቀን ብሔራዊ ተልዕኮ ያልፈፀመና ህዝባዊ ግርማ ሞገስ የራቀው ሰራዊት ነው። መከላከያ ሰራዊት የሚጠበቅበትን ዳር ድንበር የማስከበር ስራ ትቶ እንደማጅራት መቺ ቅያስ ለቅያስ እየዞረ የህፃናትን ደም ሲያፈስ የሚውል እጅግ መንደሬ የሆነ ስብስብ ነው።እዚህ ግባ የሚባል የራሱን ብሔራዊ ገፅታ መገንባት ያልቻለው ይህ የታሪክ አተላ የሀገሪቱ ሲቪል አስተዳደር እንዲህ በበሰበሰበት ወቅት እንኳ ስልጣን ተረክቦ የሽግግር መደላድል የመፍጠር ተቋማዊ አቅምም ሆነ ቅቡልነት የሌለው ወራዳ ጦር ነው።ይህ በተልዕኮው ከአንድ ልክስክስ ውሻ ብዙም የማይለየው ሰራዊት ዛሬ በምስራቁ የሀገራችን ክፍል በህወሓት ሸፍጥ በገዛ ሀገራቸው ተፈናቅለው የመከራ ህይወት እየገፉ የሚገኙ ወገኖቻችንን መናከሱን እያየን ነው።የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ማንኛውንም አይነት ልዩነትህን ወደ ጎን ትተህ ኃይልህን አስተባብረህ ይህን የበሰበሰ ስርዓት ቅበር። ሌላ ምርጫ የለህም።

የዕለቱ መልዕክት ነው!

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.