የአግ7 አርበኞች ሕዝብን ለመግደል በተንቀሳቀሱ የህወሓት የመከላከያ አባላት ላይ ጥቃት ፈፀሙ

Standard

                 ዛሬ የካቲት 02 ቀን 2010 ዓ/ም ከረፋድ 5:15 ሲሆን በሰሜን ጎንደር ጭልጋ ወረዳ ላዛ ቀበሌ ድብላ ከተባለው ቦታ ላይ በተፈፀመ ጥቃት 2 የህወሓት የመከላከያ አባላት ሲገደሉ 1 በካባድ ሁኔታ ቆስሏል ፡፡ ጥቃቱ የደረሰባቸው የህወሓት የመከላከያ አባላት ከጭልጋ በፓትሮል ተጭነው በላዛ እና አዳኝ አገር ጫቆ የሚኖሩትን ሕዝቦች ለመግደል እና ለማሰር ተልዕኮ የተሰጣቸው ነበሩ ፡ ተልዕኮውን የሰጠው የህወሓቱ የጭልጋ ምድብ አዛዥ የሆነው ኮኒሪል ፍተዌ ሲሆን ትዕዛዙ የተሰጠበት ምክንያት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አብዛኛው የከተማ ነዋሪዎች ፍትሃዌ ያልሆነ የግብር ውሳኔን አንቀበልም ፡ አንከፍልም እንዳሉ ሁሉ ህወሓትም በአርሶአደሮች ላይ ቀደም ሲል ለእርሻ መሬት ይከፍሉት የነበረውን የግብር መጠን ከ180 (ከአንድ መቶ ሰማኒያ ) ብር ወደ 1,500 (አንድ ሽህ አምስት መቶ) ብር ከፍ አድርጎ እንዲከፍሉ ሲጠይቃቸው “ይህን ከአቅም በላይ የሆነ የግብር ክፍያ አንቀበልም” በማለት ተቃውሞ በማሰማታቸው ስርዓቱም ከውይይት ይልቅ በኃይል የሚያምን በመሆኑ በአርሶ አደሮች ላይ ሚኒሻዎችን እና ፀረ ሽምቆችን በመላክ ለማስከፈል ሙከራ ቢያደርግም ሕዝቡ በአንድ ድምፅ ፍቃደኛ ባለመሆኑ እና የተላኩትም ሚኒሻዎች እና ፀረ ሽምቆች ከአቅማችን በላይ ነው በማለታቸው የህወሓት መከላከያ በሕዝብ ላይ ማዝመት በመምረጥ ከላይ ወደ ተጠቀሰው ቦታ ወታደሮች ግዳጅ ተሰጥቷቸው ሲንቀሳቀሱ መረጃው ለአግ7 መረጃ ክፍል በመድረሱ የሕዝብ ልጆች የሆኑ አርበኞች ደፈጣ አድርገው በመጠባበቅ ጥቃቱን አድርሰዋል ።

በዚህም ጥቃት አርሶ አደሮችን ከሞት ከመታደጉም በላይ ሕዝባዊ ወገንተኝነቱን በግልፅ አሳይቷል ፡፡

ጥቃቱን የፈፀሙ የአግ7 አርበኞች በሰላም ወደ ቦታቸው ተመልሰዋል ፡፡

ድል ለሕዝብ !!!

የአግ7 ዘመቻ ነፃ ትውልድ ፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.